Get Mystery Box with random crypto!

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconhenokhaile — የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconhenokhaile — የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @deaconhenokhaile
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 63.97K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ፈቃድ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው::
@deaconhenokhaile
"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን"
2ኛ ቆሮ. 2:14

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-08-30 23:23:10
14.4K views , 20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-30 21:46:25 + ድንገት የተበጠሰ ገመድ +

የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል::

የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ)

በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት::

ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል::

በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም::  የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ::
ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም
13.4K views , 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-27 13:13:56 ‹‹መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሌሊት የተቀደደ ቀሚስ ለብሶ ታየኝ ፤ እኔም ‹ጌታዬ ሆይ ልብስህን ማን ቀደደው?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ‹አርዮስ ልብሴን ቀደደው ፤ ከባሕርይ አባቴ (ከአብ) ለይቶኛልና ፤ እንዳትቀበለው ተጠንቀቅ› አለኝ›› አላቸው፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በእኔ ደም መፍሰስ የክርስቲያኖች ደም እንደጎርፍ መፍሰሱ ይቁም ብሎ ተስሎ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ጌታችን ‹ልብሴን ቀደደው› ብሎ ለዚህ ፓትርያርክ እንደነገረው የጌታችን የባሕርይ አምላክነት ላይ የክህደት ቃልን የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ ሮማውያን ወታደሮች ያልቀደዱትን የክርስቶስን ቀሚስ እንደቀደዱ ይቆጠራል፡፡

ሊቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ደግሞ የጌታችንን ልብስ አለመቀደድ ቤተ ክርስቲያንን ለሚከፋፍሉ ሰዎች ማስተማሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እንደ ሊቁ ትምህርት ያልተቀደደችውና ከላይ ጀምሮ ወጥ የሆነችው ቀሚስ ከዚህ ዓለም ያልሆነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ለአራት የተከፈለው ደግሞ የምታስተምረው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ሊከፋፈልና ለዓለም ሁሉ ሊዳረስ ይችላል፡፡ ወንጌል በዘር በቋንቋ በሀገር አይገደብምና የክርስቶስ ወታደሮች የሆኑ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ተከፋፍለው ለዓለም ማከፋፈል አለባቸው፡፡

አብያተ ክርስቲያናት በየሀገራቱ ቢቋቋሙ ፣ አህጉረ ስብከቶች ቢስፋፉ ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሊቃውንት ፣ ሰባክያን በቁጥር በዝተው ፣ በቦታም ተከፋፍለው ቢያገለግሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሁሉ ጎዳና … ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል›› እንዳለ የመምህራን መብዛት የወንጌል መስፋፋት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ (ፊል. ፩፥፲፰)

ቀሚሱ የተባለችን ቤተ ክርስቲያንን ከተቃደዷት ግን አደጋ አለው ፤ ‹የሐዋርያት በሆነች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን› ብለን የምንናገርላት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቀሚሱ ናት፡፡ በሰው እጅ ያልተሰፋች ፣ ማንምም ሊሠፋት የማይችል ቀሚስ ናት ፤ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆና በመሠራቷም አትከፋፈልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍሏት የሚፈልጉ ሰዎችን ሊቁ አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ሮማውያን እንኳን ያልቀደዱትን የክርስቶስን ልብስ እናንተ ስለምን ትቀድዱታላችሁ?››

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
deaconhenokhaile@gmail.com
14.1K views , 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-26 12:37:27 +++ አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ +++

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው " ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት" ቅዱስ አውግስጢኖስ

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም
(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ )
Deacon Henok Haile
15.3K views , 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-21 22:19:42

18.7K views , 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-19 10:53:10 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
20.3K views , 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-19 10:53:10 + የሐዲስ ኪዳን ደብረ ሲና +

አይሁድ ‘እኛ የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደተናገረው እኛ እናውቃለን ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው ክርስቶስን ሊያቃልሉ ሞክረው ነበር፡፡

ዛሬ በደብረ ታቦር የተከናወነውን ቢያውቁ ምን ይሉ ይሆን? እነርሱ ሕጉን እንጠብቃለን ብለው የሚመኩበትና የእርሱን ሕግ እየጠቀሱ ክርስቶስን ሊነቅፉ የሚሞክሩበት ሙሴ ዛሬ በታቦር ተራራ ከጌታ ፊት በፍርሃት ቆመ፡፡ አይሁድ ይህንን ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን? ፈሪሳውያን ሆይ ወደ ደብረ ታቦር ብቅ ብትሉ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ነን ብላችሁ የምትመኩበት ሙሴን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ የሕግ ፍጻሜ ክርስቶስ የሕጉን ተቀባይ ሙሴን ጠርቶ እያነጋገረው ነው፡፡ ሙሴም በሲና ተራራ በዛፍ ላይ ሲነድ ካየው እሳት ጋር እየተነጋገረ ነው፡፡

አይሁድ ሆይ በጌታ ፊት በትሕትና ብትቀርቡ ኖሮ የት እንደተቀበረ እንኳን የማታውቁትን ሙሴ ለማየት በታደላችሁ ነበር፡፡ የሙሴን መጻሕፍት በቃላችሁ የምታውቁ ሕግ አዋቂዎች ሆይ እናንተ ቁጭ ብላችሁ ክርስቶስ ለሦስት ትሑታን ዓሣ አጥማጆች ሙሴን እያሳያቸው ነው፡፡ ‘ኤልያስ ይመጣል’ የምትሉ ጻፎች ሆይ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ብትሆኑ ኖሮ ኤልያስን በታቦር ተራራ ባያችሁት ነበር፡፡ ደብረ ታቦር ብትገኙና ኤልያስን ብታዩት ኖሮ መስቀሉ ሥር ቆማችሁ ኤሎሔ ሲል ስትሰሙ ‘ኤልያስን ይጠራል ያድነው ከሆነ እናያለን’ ብላችሁ ባልሰማ ጆሮአችሁ ከፈጣሪ ጋር አትጣሉም ነበር፡፡

ደብረ ታቦር የሐዲስ ኪዳን ደብረ ሲና ሆነች፡፡ ሙሴ ሕዝቡን ከተራራ በታች ትቶ ከኢያሱና ከወንድማማቾቹ አብዩድና ናዳብ ጋር ወደ ሲና ተራራ ይወጣ እንደነበር ክርስቶስም ከጴጥሮስና ከወንድማማቾቹ ያዕቆብና ዮሐንስ ጋር ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ ሙሴ በሲና በደመና መካከል የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደሰማ በታቦርም የአብ ቃል ተሰማ፡፡ የታቦር ድምፅ ግን እንደ ሲና ‘ባሪያዬ ሙሴ’ የሚል ሳይሆን ‘የምወደው ልጄ’ የሚል ነበር፡፡ ሙሴ በሲና ተራራ ባየው የእግዚአብሔር ክብር ምክንያት ፊቱ እስራኤል ተሸፈንልን እስኪሉት ድረስ አበራ፡፡ የታቦር ተራራው ግን የተለየ ነበር ፤ ብርሃኑ ከውስጡ የፈለቀው ጌታ ፊቱ ከሙሴ ይልቅ አበራ በልብሱ እንዳይሸፍነው ልብሱም ብርሃን ነበረና ተማሪዎቹ ወደቁ፡፡

ታቦር እንዴት ያለች ‘እግዚአብሔር የወደዳት’ ተራራ ናት? [ደብር ዘሠምሮ እንዲል] ሐዋርያትና ነቢያት በአንድነት ቆመው የሚተያዩባት ፤ ብሉይና ሐዲስ የተዋወቁባት ፤ ጥላና አካል የተጋጠሙባት ይህች ተራራ እንዴት የተመረጠች ናት? ‘ታቦርና አርሞናዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል’ እንደተባለ ነቢያትና ሐዋርያትን በግራ በቀኙ አድርጎ በሰማያዊ አባቱ ‘የምወደው ልጄ’ ተብሎ ሲጠራ ስሙን ሰምታ ታቦር ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት አጣን እንጂ ነቅለን ወደ ሀገራችን ከምናስገባቸው ተራሮች አንዱ ታቦር በሆነ ነበር፡፡

በታቦር ተራራ ሐዋርያትና ነቢያት በአንድ ወንበር ከሊቀ ሊቃውንት ክርስቶስ ትምህርት ተምረው ተመለሱ፡፡ ሐዋርያቱ የነቢያት ጌታ መሆኑን ሲማሩ ነቢያቱ ደግሞ የሐዋርያት አምላክ መሆኑን አወቁ፡፡ ነቢያት ደክመው የዘሩትን ከሚያጭዱ አጫጆች ሐዋርያት ጋር ተዋወቁ፡፡
ነቢያት አምላክነቱን ያውቃሉ ፤ ሐዋርያት ደግሞ ሰውነቱን ያውቃሉ፡፡ በታቦር ተራራ ግን አዲስ ትምህርት ተማሩ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ፦ ‘‘ነቢያቱ አይተውት የማያውቁትን ሰውነቱን አይተው ተደሰቱ ፤ ሐዋርያቱ አምላክነቱን አይተው ተደሰቱ’’

ሐዋርያት ደነገጡ ፤ እነርሱ ባልነበሩበት በዮርዳኖስ የተናገረውን የእግዚአብሔር አብን ድምፅ በታቦር ተራራ ሰሙ ፤ ጴጥሮስ ‘አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ’ ያለው በሰማይ ያለው አብ ገልጦለት ነበረ ፤ አሁን በልቡ ያንን ቃል ያስቀመጠውን የአብን ድምፅ ሰምቶ ዓለቱ ስምዖን በፍርሃት ወደቀ፡፡ የጌታን ፊት አብርቶ ሲያይ ሳያይ ያመነውን አምላክነቱን አወቀ፡፡ ‘ሐዋርያት በአንድ ቀን ሁለት ፀሐይ ወጥቶ አዩ ፤ አንደኛው የተለመደችው ፀሐይ ስትሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚያበራው የጌታ ፊት ነበር’ ይላል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡ እውነትም ስሙን ለሚፈሩ ሐዋርያት የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ላይ ወጣላቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም በታቦር ተራራ ነቢያትና ሐዋርያት መገናኘታቸውን እንዲህ ሲል ያደንቃል ፦
‘የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ኤልያስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!’

ሐዋርያት ወድቀው ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት’ የሚል ቃል ከሰሙ በኋላ ሲነሡ ከክርስቶስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡ በእርግጥም ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው’ ተብለው ማሳሰቢያ ከተሠጣቸው በኋላ ቀና ሲሉ ማግኘት ያለባቸው ‘የሚወደው ልጁን’ ክርስቶስን ብቻ ካልሆነ አዋጁ ስለማን እንደሆነ ግራ ይገባቸው ነበር ይላል ማር ኤፍሬም፡፡

ሐዋርያት ቀና ሲሉ ሙሴ የለም ፤ ኤልያስም የለም፡፡ ለነገሩ ከሙሴም ከኤልያስም የሚልቀው ጌታ ከእነርሱ ጋር ካለ ምን ይፈልጋሉ? ባልወለደው ፈርኦን የልጅ ልጅ ተብሎ ከተጠራው ሙሴ ይልቅ ባልወለደው ዮሴፍ የዮሴፍ ልጅ ተብሎ የተጠራው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ከፈርኦን ሰይፍ ተርፎ እስራኤልን ነጻ ካወጣው ሙሴ የሚበልጠው ከሔሮድስ ሰይፍ ተርፎ ዓለምን ነጻ ያወጣው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር አለ፡፡ እናቱ ሞግዚቱ ሆና ካሳደገችው ሙሴ በላይ ‘እናትና ገረድ ማርያም ደስ’ ብሏት ያሳደገችው ክርስቶስ አይሻላቸውም? ግብፃዊውን ገድሎ ለማንም አትናገሩ ከሚለው ሙሴ ይልቅ ዕውራንን አብርቶ ለምፃምን አንጽቶ ፊቱ እንደ ፀሐይ አብርቶ ለማንም አትናገሩብኝ የሚለው ክርስቶስ አብሮአቸው ካለ ምን ይፈልጋሉ፡፡ ‘የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ’ ተብሎ ከተነገረው ሙሴ ይልቅ ‘የጌታ እግር በሚቆምበት እንሰግዳለን’ ‘የጫማህን ጠፍር እንኳን ልፈታ አይገባኝም’ እየተባለ የተዘመረለት ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነውና ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የሙሴ መሔድ አላስደነቃቸውም፡፡

ኤልያስንም ስላላዩ አላዘኑም ፤ በእሳት ሰረገላ ከሔደው ኤልያስ በላይ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት የሆነው አምላክ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ኤልያስ ለደቀ መዝሙሩ ወደ ሰማይ ሲሔድ መጎናጸፊያውን ትቶለት ሔዶ ነበር፡፡ የሐዋርያት መምህር ክርስቶስ ግን ሲያርግ ልብሱን አልወረወረላቸውም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለ እርሱ ሲያርግ ለደቀ መዛሙርቱ የተወላቸው ልብሱን ሳይሆን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ነው፡፡ ስለዚህ ኤልያስ ቢሔድ ሙሴም ቢሰወር ደቀ መዛሙርቱ ጌታችንን ከብበው ከታቦር ተራራ በደስታ ወረዱ፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 13 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ

ፎቶ : ጴጥሮስ "ሦስት ዳስ እንሥራ" ያለበት ምኞቱ ቆይቶ ተሳክቶ በአሁኑ ሰዓት በታቦር ተራራ ሦስት ቤተ መቅደሶች ያሉ ሲሆን የመካከለኛው የጌታ ግራና ቀኙ ደግሞ የሙሴና የኤልያስ ናቸው:: የምትመለከቱት ፎቶ ከሦስቱ ዳስ በአንዱ በሙሴ ዳስ ውስጥ የተነሣሁት ነው::
18.6K views , 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-15 12:50:38 + ማርያማዊ ደስታ +

ድንግል ማርያም ‘መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል’ አለች፡፡ የድንግሊቱን ጥበብ ተመልከቱ፡፡ ‘በመልአክ በመመስገኔ ደስ ይለኛል ፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመባሌ ደስ ይለኛል ፣ አምላክን ለመውለድ በመመረጤ ደስ ይለኛል’ አላለችም፡፡ የእርስዋ የደስታ ምንጭ ከእግዚአብሔር የተሠጣት ነገር ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡

እግዚአብሔር የደስታህ ምንጭ ከሆነ በሕይወትህ ምንም ነገር ቢከሰት ደስታህን አይነካብህም፡፡ ድንግሊቱ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመሆንዋ ደስ ያላት ብትሆን ኖሮ ከዚያ በኋላ ከሴቶች ሁሉ የተንከራተተች ፣ ከሴቶች ሁሉ ያዘነች ፣ ከሴቶች ሁሉ በዲያብሎስና ጭፍሮቹ የተጠላች ፣ በሔሮድስ በአይሁድ የተነቀፈች መሆንዋን ስታይ ደስታዋ በጠፋ ነበር፡፡

እርስዋ ግን ደስታዋ የመነጨው ከአምላክዋ ብቻ ነበር፡፡ ፍጹም የሆነ ውስጣዊ ደስታን ማግኘት የሰው ልጅ ትልቅ ምኞቱ ነው፡፡ ሰዎች ደስታን ፍለጋ ብዙ ይደክማሉ፡፡ ድንግሊቱ ግን የደስታ ሁሉ ምንጭ የሆነው አምላክ ከእርስዋ ጋር ነውና በፍጹም ደስታ ደስ ይላታል፡፡ የድንግል ማርያም ደስታ ልጅዋ ‘ደስታችሁን የሚወስድባችሁ የለም’ ያለው ዓይነት ደስታ ነበር፡፡ ዮሐ. ፲፮፥፳፪

‘ተፈሥሒ ፍስሕት’ (ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ) ፤ ሙኃዘ
ፍሥሓ (የደስታ መፍሰሻ ሆይ) ብለን የምናመሰግናት እመቤታችን ከማንም የሚበልጥ ደስታ በእርስዋ ዘንድ ነበረ፡፡ ደስተኛ የነበረችው በምድር በነበራት ቆይታ የሚያስደስት ኑሮ ስለነበራት አይደለም፡፡ እንደ እርስዋ የተሰደደ ፣ ያለቀሰ ፣ የተጨነቀ ፍጡር የለም፡፡ እንደ ክርስቶስ መከራ የተቀበለ እንደሌለ እንደ ድንግል ማርያምም ያዘነ የለም፡፡ እርስዋ ግን ለሌሎች የሚተርፍ ወደ ኤልሳቤጥ የሚሸጋገር ፣ ሆድ ውስጥ ወዳለ
ፅንስ የሚጋባ ጥልቅ ደስታ ነበራት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‘ተፈሢሓ በነፍሳ ፆረቶ በከርሣ’ ‘በነፍስዋ ደስ ተሰኝታ በሆድዋ ተሸከመችው’ እንዳለ እርስዋ የተደሰተችው ሥጋዊ ደስታን አልነበረም፡፡ (ድጓ ዘቅዱስ ገብርኤል )ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች አንዱ ደስታ ነውና ቅድስቲቱ ማንም ጋር ያልነበረ ደስታ ነበራት፡፡ ገላ. ፭፥፳፪

በእርግጥም ደስታን ወልዳ ደስ ባይላት ይደንቅ ነበር፡፡ እርስዋ የወለደችው ‘የመላእክት ተድላ ደስታቸው’ ነው ፤ እርስዋ የወለደችው መወለዱ ‘ለሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች’ የሚሆን ልጅን አይደለምን?

እግዚአብሔር አብ ‘በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው’ ያለውን አንድያ ልጁን ልጅዋ እንዲሆን ሠጥቶአታልና እርስዋም በምትወደው በልጅዋ ደስ ይላታል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ካለ እግዚአብሔር የዘጠኝ ወር ቤቱ አድርጎ ያደረባት ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? መወለዱ ሰውና መላእክትን በደስታ እንዲዘምሩ ካደረገ የወለደችው ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?

ጌታ ለሐዋርያቱ ‘ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ’ ካላቸው እግዚአብሔር ሁለተኛ ሰማዩ አድርጎ ዙፋን ያደረጋት በምድር ያለች የጠፈር ባልንጀራ ፣ የአርያም እኅት ማርያም ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?

እመቤታችን ሆይ እባክሽን በአንቺ ላይ ከፈሰሰው ደስታ ቀድተሽ ወደ እኛ ወደ ኀዘንተኞቹ አፍስሺ፡፡ ኖኅ እንደ ላካት ርግብ የመከራችን ውኃ ጎደለ ብለሽ ታበሥሪን ዘንድ ወደ እኛ ነይ ‘ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ኀዘነ ልብየ’ ‘ርግቤ ሆይ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ’ እንዳለ ሊቁ፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 7 2015 ዓ.ም.
ለበዓለ ጽንሰታ ዝክር
ከብርሃን እናት ገጾች የተቆረሰ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
22.9K views , 09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-15 04:57:35 + ማርያማዊ ብሶት +

"ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?"

ድንግል ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ የተናገረችው የብሶት ንግግር ይኼ ብቻ ነው:: "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?"

ድንግሊቱ እንዲህ ያለችው ምን ቢደርስባት ነው?

ጌዴዎን እስራኤል መከራ ሲጸናባቸው "ጌታዬ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን?" ብሎ ነበር:: መሳ. 6:13

ኢያሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ :- ዋይ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ በአሞራውያን እጅ አሳልፈህ ትሰጠን ታጠፋንም ዘንድ ይህን ሕዝብ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? ብሎ በብሶት አልቅሶ ነበር:: ኢያሱ 7:7

ሙሴም የሕዝቡ አመፅ ሲያስጨንቀው ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፦ ለምን በባሪያህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ የዚህን ሕዝብ ሁሉ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ? ብሎ ተማርሮ ነበር:: ዘኍ. 11:11

ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ብላ የብሶት ቃል የተናገረችው ግን መከራ ሲደርስባት አልነበረም::

ወደ ግብፅ ስደት እንድትወጣ ሲነገራት "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም:: ግርፋቱንና ሕማሙን ስታይም ኀዘንዋን ዋጥ አድርጋ ቆመች እንጂ "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" አላለችም::

ድንግል ማርያም "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህብን?" ያለችው ልጅዋ ለሦስት ቀናት ከዓይንዋ በራቀበት ወቅት ነበረ:: "እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን፡ አለችው" ሉቃ. 2:48

ድንግሊቱ ለምን እንዲህ አደረግህብኝ ያለችው ስለ ሌላው መከራዋ ጊዜ ሳይሆን ክርስቶስ ከእርስዋ ዘንድ ስላልነበረባቸው ቀናት ነበር:: እንደርስዋ መንፈሳዊ ስትሆን "ጌታ ሆይ ለምን አስጨነቅኸኝ?" የምትለው እርሱ ከአንተ የራቀ መሆኑ ሲሰማህ ብቻ ነው:: "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ" "አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ?" እያልክ የምትጮኸው እግዚአብሔር ከአንተ የራቀ ሲመስልህና የተቀደሰው ማርያማዊ ብሶት ሲሰማህ ነው:: መዝ. 21:1፤10:1

እርሱ ከአንተ ጋር ከሆነ "በሞት ጥላ መካከል እንኩዋን ብትሔድ ክፉውን አትፈራም" ከአንተ የተለየ ሲመስልህ ግን "ጌታ ሆይ ምን አደረግህብኝ" ብለህ በማርያማዊ ብሶት ትጮኻለህ::

ከእርሱ ጋር ሆነህ መከራን መቀበል አይከብድህም:: መሰደድም አያስጨንቅህም:: እርሱ ከአንተ ዘንድ ከጠፋ ግን ብርሃንህ ምርኩዝህ ኃይልህ ጉልበትህ ሁሉ ከአንተ ዘንድ የሉምና ልትጸና አትችልም::

ዝምተኛዋን ድንግል ማርያም በብሶት ማናገር የቻለ አንዳች መከራ አልነበረም:: በበረሃ ከልጅዋ ጋር ከተንከራተተችበት ጊዜ ይልቅ ግን ያለ ልጅዋ ያሳለፈቻቸው ሦስት ቀናት "ልጄ ሆይ ለምን ይሄን አደረግህብኝ" ብላ እንድትጮህ አደረጓት::

ድንግል ሆይ ከአንቺ ዘንድ ለሦስት ቀን የተሰወረው ጌታ ከእኔ ሕይወት ከራቀ ዓመታት እንዳለፉ እያየሽ ይሆን? "ልጄ ሆይ ለምን እንዲህ አደረግህበት? ነፍሱ ተጨንቃ እየፈለገችህ አይደለምን?" የማትይው ስለምንድን ነው?

ለሌላው መከራዬ የምጮኸውን ያህል ከልጅሽ መለየቴ ተሰምቶኝ በማርያማዊ ብሶት እንዳልጮህ በኃጢአት ብርድ ተይዤ መንፈሳዊ ሙቀት በእኔ ዘንድ የለም:: የምበላው የምለብሰው ሲጎድል እንጂ አምላኬን ሳጣ የሚሰማኝ ሰው አይደለሁም:: እኔ ባልጠይቅሽ እንኳን እንደ ቃና ሙሽሮች ጉድለቴን አይተሽ የማትለምኚልኝ ለምንድን ነው? ልጅሽ ወደ ወይን እንዲለውጠው ከእኔ ሕይወት በላይ ውኃ ውኃ ያለ ነገር ከወዴት ሊመጣ? ከልቤስ በላይ የድንጋይ ጋን ከየት ይገኛል?

"ንዒ ማርያም ለዕውር ብርሃኑ
ወንዒ ድንግል ለጽሙዕ አንቅዕተ ወይኑ
ኦ ኦ ትኃድግኒኑ ኦ ኦ ትመንንኒኑ
ኀዘነ ልብየ እነግር ለመኑ"
"የዕውር ብርሃኑ ማርያም ሆይ ነይ
ለተጠማው ወይን የምታፈልቂለት ማርያም ሆይ ነይ
ወዮ ትተዪኝ ይሆንን? ወዮ ትንቂኝ ይሆንን?
የልቤን ኀዘን ለማን እነግራለሁ? (መልክአ ኤዶም)

ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ነሐሴ 7 2015 ዓ.ም.
20.5K views , 01:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-13 01:43:34 እዚህ ላይ የሚያስደንቀው የማርያም ዝምታ ነው፡፡ ማርታ ስትከስሳት ጌታችን መልስ ሠጠላት እንጂ ማርያም አንድም ቃል አልተነፈሰችም፡፡ ‹ቃሉን መስማት ይበልጣል ብዬ ነው!› ብላም አልተመጻደቀችም፡፡ ዝም አለች፡፡ በእርግጥ እኅትዋ ስትከስሳት ምን ተሰምቷት ይሆን? በአፍዋ ዝም ብላ በልብዋ እየተሳደበች ይሆን እንዴ? አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ‹የለም በውስጥዋም ክፉ ሃሳብ አልነበረም› ይላል፡፡ ‹እንግዲህ እንደ ማርያም አርምሞና ትዕግሥትን ገንዘብ እናድርግ› (ናጥሪ እንከ አርምሞ ወትዕግሥተ ከመ ማርያም) በማለት በአፍዋ አርምሞን (ዝምታን) ብቻ ሳይሆን በልብዋም ትዕግሥትን ገንዘብ አድርጋ እንደነበር ይመሰክራል፡፡

ያስደንቃል! እጅግ በምታከብረው ጌታ ፊት የገዛ እኅትዋ ስትከስሳት ማርያም እንዴት አልተበሳጨችም? ቢያንስ በልቧ እንኳን እንዴት አላጉረመረመችም? መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ማርያም ሌላ ዓለም ውስጥ ስለነበረች ነው፡፡ ከጌታችን አንደበት የሚወጣውን አምላካዊ ቃል ሰምታ ልቧ ተሰውሯል ፤ አካልዋ በቤት ውስጥ ቢሆንም ኅሊናዋ ወደ ሰማያት ከፍ ብሏል፡፡ በጌታችን ቃል ልቡ የተሰበረ ሰው ደግሞ እንኳን ቢሰድቡት ቢደበድቡትም አይሰማውም፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ መወገሩ ገለባ የመሰለው ጌታችንን እያየ ስለነበር ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ የአፄ ገብረ መስቀል ጦር እግሩ ላይ ተሰክቶ ምንም ያልታወቀው በእግዚአብሔር ቃል ልቡ ስለተመሠጠ ነው፡፡ ማርያምም ልቧ በቃሉ ስለተመሰጠ በእኅቷ ንግግር ምንም አልተሰማትም፡፡

★ ★ ★

ከብዙ ወራት በኋላ ጌታችን ዳግመኛ ወደነማርታ ሀገር ወደ ቢታንያ ተመልሶ መጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን እንግዳ ሆኖ የሔደው ወደነማርታ ቤት ሳይሆን ወደ ለምጻሙ ስምዖን ቤት ነበር፡፡ የቢታንያው ስምዖን ለጌታችን የራት ግብዣ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ ዕለት ታዲያ የቢታንያ ነዋሪዎች እንደመሆናቸው ማርታ ፣ ማርያምና አልዓዛርም በስምዖን ቤት ተገኝተው ነበር፡፡

ማርያም ጌታችን ባስተማራት ትምህርት ልቧ ተሰብሮ ፣ የምትኖርበትን የኃጢአት ኑሮ ተጸይፋ ነበር፡፡ ስለዚህ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባስጥሮስ ሽቱ ገዝታ ወደ ስምዖን ቤት ገሰገሰች፡፡ ከጌታችን እግር ሥር ተደፍታም በዕንባዋ አጠበችው ፣ በፍጹም ጸጸት ወደ ፈጣሪዋ ተመለሰች፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ‹ይህ ጥፋት ምንድር ነው?› ብሎ ለሽቱው ብክነት ተቆጨ ‹ለድሆች ቢሠጥ ይጠቅም ነበር› የሚል የውሸት ምክንያትም አቀረበ፡፡ ማርያም ፈተናዋ ብዙ ነው ፤ ቃሉን ስትማር እኅትዋ ተቸቻት ፤ ንስሓ ስትገባ ደግሞ ይሁዳ ተነሣባት፡፡ ማርታ ቃሉን ከመስማት ይልቅ ‹ለምግብ ሥራ ቅድሚያ እንሥጥ› ብላ እንደነበር ይሁዳም ‹ለነዳያን አገልግሎት ቅድሚያ ይሠጥ› አለ፡፡ (ይሁዳ ጌታችን ሲያስተምር ‹እናትህና ወንድሞችህ መጥተዋል እያለ ትምህርት እንዲቋረጥ የሚታገል ሰው እንደነበር ልብ ይሏል› ማቴ.12፡46 ትርጓሜ)

ይሁዳ ሲናገር ማርያም እንደ ልማዷ ዝም አለች ፤ ጌታችንም እንደ ልማዱ መልስ ሠጠላት፡፡ እርስዋንም ‹ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል› ብሎም አሰናበታት፡፡ ማርያም በተማረችው ቃል የንስሓ ፍሬ አፈራች ፤ የኃጥኡን መመለስ ለሚወደው ጌታ ዕንባዋ አቀርባ ከማርታ በላይ አስተናገደችው፡፡ መስተንግዶዋም ከማርታ ብቻ ሳይሆን ታላቅ ግብዣ ካደረገለት ከለምጻሙ ስምዖንም የበለጠ ሆነ፡፡ ጌታችንም ለለምጻሙ ስምዖን ከእርሱ መስተንግዶ የእርስዋ መስተንግዶ ምን ያህል የበለጠ እንደሆነ አነጻጽሮ ነግሮታል፡፡ (ሉቃ. 7፡44-46)

ከላይ እንደተገለጸው ማርያም እንዲህ ስትጸጸትና ኃጢአትዋ ሲሰረይላት ማርታ በለምጻሙ ስምዖን ቤት ውስጥ በእንግድነት ተገኝታ ነበር፡፡ ምን እያደረገች ይሆን? የእኅትዋን መመለስ በመገረም እያየች ይሆን? ወይስ በቤትዋ ያመለጣትን ትምህርት ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብላ እየሰማች ይሆን? ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ መልሱን እንዲህ ሲል ጽፎልናል፡፡ ‹‹በዚያም እራት አደረጉለት፤ ማርታም ታገለግል ነበር›› (ዮሐ. 12፡2)

ለማመን ያስቸግር ይሆናል፡፡ አዎን ማርታ በሰው ቤትም እንኳን አላረፈችም፡፡ በቤትዋ እንዳደረገችው በስምኦን ቤትም በአገልግሎት ላይ ነበረች፡፡ እኅትዋ ስትማር ጓዳ የነበረችው የዋኋ ማርታ ምንም እንኳን ጌታችን አገልግሎቷን ሳይነቅፍ የሚበልጠው ከእግሩ ሥር መገኘት እንደሆነ የነገራት ቢሆንምም አሁንም መልካሙን ዕድል አልመረጠችም፡፡ እኅትዋ ስትማር ታገለግል እንደነበረች ፣ የእኅትዋ ኃጢአት ሲሰረይም እስዋ አገልግሎት ላይ ናት፡፡ ማገልገል መልካም ነው ፤ እኛ በአገልግሎት ስንባክን ፣ ሌሎች ወደ እግዚአብሔር ሲቀርቡ ኖረዋል፡፡

ንስሓ ገብተው ወደ ሥጋ ወደሙ ሲቀርቡም እኛ አገልግሎት ላይ ከሆንን እንደ ማርታ ዕድላችንን ያልተጠቀምን ምስኪኖች ነን፡፡ የሚያሳዝነው ማርታ አላወቀችም እንጂ የስምዖን ቤት ግብዣ ከጌታ እግር ስር ለመቀመጥ የመጨረሻ ዕድሏ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ከዚያች ቀን በኋላ በጥቂት ቀናት ልዩነት ተሰቅሎ ሞቶአል፡፡ ከዚያም ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ በአርባኛው ቀን አርጓል፡፡ ማርያም የመጀመሪያ ዕድሏን ለመማር ፣ የመጨረሻ ዕድሏን ደግሞ ለንስሓ ተጠቀመችበት፡፡ ማርታ ግን ‹ታገለግል ነበር›፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 7 / 2008 ዓ.ም
አዲስ አበባ
20.3K views , 22:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ