Get Mystery Box with random crypto!

#የሐጅ ቀናት 6 ናቸው። የመጀመሪያው ዛሬ ነው። የተርዊያ ዕለት ይባላል። ሐጀር አልዓስቀላኒይ | ቢስሚከ ነሕያ✿⁠ ⁠♡

#የሐጅ ቀናት 6 ናቸው።

የመጀመሪያው ዛሬ ነው። የተርዊያ ዕለት ይባላል። ሐጀር አልዓስቀላኒይ እንደሚሉት በዚህ ዕለት ሑጃጆች ራሳቸውንም ያላቸውን እንስሳዎች በደንብ አጥግበው ነገ ወደ ዐረፋ ለመሔድ ይሰነቃሉ።

ሁለተኛው ዕለት የነገው ዕለት ታላቁ #ዐረፋ ነው። ዐረፋ በዘጠነኛው ዕለት ሑጃጆች በዐረፋ ተራራ ጌታቸውን የሚለምኑበትና የሚማጸኑበት ነው።

ሦስተኛው የዕርዱ የመጀመሪያ ቀን ሲኾን ዒል አልድሐ የሚበርበትም ዕለት ነው።

አራተኛው ሚና ላይ የሚረጉበት ዕለት ነው።

አምስተኛው ሑጃጆች ከሚና የሚበተኑበት የመጀመሪያ ዕለት ነው።

ስድስተኛው ሑጃጆች ከሚና የሚበተኑበት ሁለተኛ ቀን ነው።

የተርዊያን ዕለት በምናብ ከሑጃጆች ጋር ነገ ወደ ዐረፋ ተራራ ልንሔድ እንዘጋጅ። ይህ ዕለት አላህ እንደ ለይለቱል ቀድር የደበቀው ሳይኾን ለባሮቹ የገለጸው ነው። ከእዝነቱ ከፍቅሩ ጋር ያገናኘን ዘንድ ልብን በማንጻት እንቀበለው። አምልኮዎች ለዚህ ተግባር ያግዙናል። ከአምልኮዎች ሁሉ በላጩ ጾም ነው። የጾም ግብ የአላህ ፍራቻ ነው። አላህን ሳናስበው ቸል ብለን የምንሰራቸውን መጥፎ ተግባራት ሁሉ የሚገታ ነፍስ ይሰጠናል። አንድ ሰው እየጾመ ሌሎች ፈርድ አምልኮዎቹን ቢያጎድል፣ የተለመዱ ውሸቶችና ክፉ አመሎች የማይቆሙ ከሆነ ዓላማውን መምታት አይችልም።

አላህ የውስጥ ንቃት ይለግሰን

ኸሚስ ወ ለይለቱል ዓረፋ

@ቤስት ከሪም