Get Mystery Box with random crypto!

«አልሃምዱሊላህ፣ አስተግፊሩላህ» በክር ኢብኑ ዐብዲላህ ማዚኒ ይባላሉ። ከመጀመሪያዎቹ ታቢዒዎች ይ | ቢስሚከ ነሕያ✿⁠ ⁠♡

«አልሃምዱሊላህ፣ አስተግፊሩላህ»

በክር ኢብኑ ዐብዲላህ ማዚኒ ይባላሉ። ከመጀመሪያዎቹ ታቢዒዎች ይመደባሉ። በክር የዘመናቸው ወደር የሌሽ ሊቅ ናቸው። ከዕለታት በአንዱ ቀን መንገድ ሲጓዙ አንድ እንጨት ለቃሚ ከፊት ፊታቸው ይሄዳል። ይሄ ሰው ደጋግሞ «አልሃምዱሊላህ፣ አስተግግፊሩላህ» ይላል። በክርም ሲበዛባቸው፦ ከዚህ ሌላ የለህም? ብትቀይረው? አሉት። ያ እንጨት ለቃሚ ለበክር ትልቅ ትምህርት ሰጣቸው።እንዲህ አላቸው፦ «እንዴታ! አገኛለሁ። ቁርዓንም ሸምድጃለሁ ሌላ ብዙን ነገር አውቃለሁ፤ ነገርግን ሰው በነፍሱ ወንጀልና በአላህ ጸጋ መካከል ከመመላስ አይወገድም። እኔ ስለወንጀሌ ኢስቲግፋር አደርጋለሁ፣ ስለ አላህ ጸጋ ደግሞ አመሰግናለሁ »
«በክር ሳተ (ተሳሳተ) እንጨት ለቃሚው አወቀ» በማለት አድናቆት ቸሩት።

ስለተሰጠን፣ ስለተደረገልን አልሃምዱሊላህ!
ስላጠፋነው፣ ስላበላሸነው አስተግፊሩላህ!

Aj sultan