Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 16 .........እጄን ጎትቶ ከንፈሬን ሳመኝ ...... በጣም ደስ አለኝ፡፡ ምንም | Campus love ❤ Stories

ክፍል 16

.........እጄን ጎትቶ ከንፈሬን ሳመኝ ...... በጣም ደስ አለኝ፡፡ ምንም ማለት አልቻልኩም ደርቄ ቀረሁኝ፡፡ ፀጉሬን እየነካካ " ሰላሜ በጣም አፈቅርሻለው" አለኝ፡፡ "ግን እኮ..." ስለው አፌን በእጆቹ አረነው በድጋሚም ሳመኝ፡፡ "...ተቀበይኛለሽ" አለን፡፡ በአእምሮዬ ብዙ ሀሳቦች ተመላለሱ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ ጠፋኝ፡፡ ትንሽ ካሰብኩኝ በኀላ "አይ ብሩክ የማይሆን ነገር ነው " አልኩትና መንገዴን ቀጠልኩኝ፡፡

ድምፁን ጮክ አድርጎ" ትዝ ይልሻል ያኔ የመጀመሪያ የተገናኘንበት ቀን አንቺ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ያየሽኝ እኔ ግን ሁሌም አይሽ ነበር!፡፡ ት/ት ቤት ስትሄጂ የትም ስትሄጂ አይሽ ነበር፡፡ ምክንያቱም በጣም አፈቅርሽ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁ ሆቴል ውስጥ ነበር፡፡ ከቤተሰቦችሽ ጋር እራት ስትበይ ነበር፡፡ እኔም ከነ ማም ጋር እራት እየበላሁ ነበር የዛን ቀን ነበር ያየሁሽ ......ልቤን የሰረቅሽው የዛን ቀን ነው፡፡ እስከዛሬ ስንቴ ልነግርሽ ወስኜ እየፈራሁ ትቼዋለው ከአሁን በኀላ ግን አልችል በቃ የኔ ብቻ እንድትሆኚ ነው የምፈልገው" አለኝ፡፡ ምንም ማለት አልቻልኩም ደርቄ ቀረሁ፡፡ እንባዎቼ ወረድ ጠጋ እያለኝ እንባዬን በእጆቹ ጠረገልኝ፡፡ "ሰላሜ ላገባሽ እፈልጋለው በጣም ነው የማፈቅርሽ" አለኝ ፡፡ እንደዚህ ሲለኝ በጣም ደስ አለኝ ተጠመጠምኩበት እጁንም ያዝኩት "ሰሊ እናንተ እዚህ ቤት ከሌላቹ እኔም አልኖርም ስለዚህ አብሬያቹ ነው የምሄደው" አለኝ፡፡ "አይሆንም ....." ስለው፡፡ "ግድ የለውም ሰላሜ ከአንቺ ጋር እንደምንም ሆኜ ነው መኖር የምፈልገው "አለኝ፡፡ የብሩኬ ሀሳብ ጥሩ እንዳልሆነ ገባኝ ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም በሱ ሀሳብ ተስማማሁኝ፡፡

እጄን ይዞ ወደ ሳሎን ሄደ፡፡ " ማም እነሰላም እዚህ ይኖራሉ ካልኖሩ እኔም እዚህ ቤት አልኖርም "አላት፡፡ ነገር ግን ዝም አለችው እኔም አንገቴን አቀርቅሬ መልሷን እጠብቃለው ግን ዝም አለች፡፡ ብሩኬ ወደ ክፍሉ ይዞኝ ሄደና ልብሱን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ " በይ ሰላሜ እንሂድ "አለኝ፡፡ እውነት ለመናገር ብሩኬ ለኛ ብሎ ከቤት እንዲወጣ አልፈለኩም ነበር ነገር ግን ብሩኬ ከገገመ ገገመ ነው ስለዚህ ስለዚህ ዝም አልኩት፡፡

የግቢውን በር ሊከፍተው ሲል "ብሩክ ከዚ ግቢ እንዳትወጣ ከወጣህ ግን ....." ስትለው "ማም እንደማትፈልጊኝ አውቄያለው እሄዳለው " ብሎ በሩን ከፈተው እየሮጠች መጥታ አቀፈችው " እንዴት አልፈልግህም አንድ ልጄ ነህ እኮ አትወደኝም እንዴ " ብላ እንባዋን አነባች ቦርሳውን ጣል አድርጎ "ማም በጣም ነው የምወድሽ ግን ሰላምንና አቤልን ብቻቸውን መተው አልችልም ፡፡ ዞር ብላ በሚያስጠላ አስተያየት አየችኝ፡፡ እኔም አንገቴን አቀረቀርኩኝ፡፡ እንባዋን እየጠራረገች እና እየገለማመጠችኝ "እሺ ልጄ እዚህ ይኑሩ አንተን ማጣት አልችልም እሺ እዚህ እንዲኖሩ ፈቅጃለው " አለችው፡፡ከዛ የብሩኬን ቦርሳ ይዛው ወደቤት ገባች፡፡ ብሩኬም የኔና የአቤልን ሻንጣ ይዞ ወደቤት ገባ፡፡እኔ እዛ ቤት መቆየት አልፈለኩም ግን አቤልን አሰብኩት .... ብሩኬም እጄን ይዞ ወደቤት አስገባኝ......

ክፍል 17 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ