Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል 15 .....የያዘው ቢራ እላዬ ላይ ማፍሰስ ጀመረ..... እኔም መጮኄንና ማልቀሴን ቀ | Campus love ❤ Stories

ክፍል 15

.....የያዘው ቢራ እላዬ ላይ ማፍሰስ ጀመረ..... እኔም መጮኄንና ማልቀሴን ቀጥያለው ፡፡ ያደረኩትን ሱሪ ሙሉ ለሙሉ አወለቀው፡፡ ወንድነቱን እና ጉልበቱን ተጠቅሞ ሊደፍረኝ ሞከረ፡፡በድንገት ዞር ስል ብሩክ ክፍሌ በር ላይ ቆሟል፡፡ አይኖቹ እንባ አቅርረው በንዴት ደርቆ ቆሞል፡፡ እያለቀስኩኝ "ብሩክ አድነኝ! አድነኝ" አልኩት፡፡ ቶሎ ብሎ ይልማን ከላዬ ላይ አነሳው በቦክስም ደጋግሞ መታው ይልማም ሰነዘረበት እዛው ድብድ ጀመሩ፡፡ እኔም ቶሎ ብዬ ሱሪ ለበስኩኝ፡፡ ለብሼ ዞር ስል ብሩክን አስተኝቶ አየመታው ነበር፡፡ በድንጋጤ በቢራ ጠርሙሱ አንገቱን መታሁት፡፡ እራሱን ስቶ ወደቀ፡፡ ጠርሙሱን መሬት ላይ ጥዬው ማልቀስ ጀመረኩኝ፡፡ብሩኬም አቅፎኝ ያባብለኝ ጀመር፡፡ ወድያው አቤል መጣ.. ብሩኬም በፍጥነት ወደታች እንዲወርድ ጠየቀው እሱም ደንግጦ በፍጥነት ወረደ፡፡ "ብሩኬ ሊደፍረኝ ነበር እኮ .......ሊያበላሸኝ " እያልኩኝ ማልቀሴን ቀጠልኩኝ ደረቱ ላይ አስተኝቶኝ ማባበሉን ቀጠለ፡፡

ከትንሽ ደቂቃ በኀላ ወ/ሮ ኤልሳ መጣች፡፡ ወንድሟ ደም በደም ሆኖ መሬት ላይ ስታየው አበደች የምትይዘው የምትጨብጠው ነገር ጠፋት፡፡ ዞር ስትል ብሩኬም ፊቱ ደምቷል፡፡ "ምን ሆነው ነው ማነው እንደዚ ያደረጋቸው ወይኔ ኤልሳ!"ብላ ማልቀስ ያዘች፡፡ ወዲያውኑ ታክሲ ጠርታ ወደ ሀኪም ቤት ይልማንም ብሩኬንም ይዛቸው ሄደኝ፡፡ እኔም ለብሩኬ ብዬ አብሬያቸው ሄድኩኝ፡፡

ሆስፒታል እንደደረስን ይልማ ነቃ፡፡ እኔ እንደዚ እንዳደረኩትና ብሩክም እንዲመታው እንዳደረኩኝ ነገራት፡፡ የዛን ቀን የወይዘሮ ኤልሳ አይኖች በጣም ያስፈሩ ነበር፡፡ ተኮሰታትራ "በይ እቤት ሄደሽ ጠብቂኝ "አለችኝ፡፡ ብሩኬም "ይኘው የኔም ቁስል ስለታሸገልኝ ከሷ ጋር አብሬ እሄዳለው" አላት፡፡ እኔና ብሩኬ ወደቤት ሄድን፡፡ ከ 2 ሰዐታት በኀላ ወ/ሮ ኤልሳ መጣች፡፡ ወገብዋን ይዛ "አንቺ የማትረቢ ማን ስለሆንሽ ነው ወንድሜን እንደዛ ያደረግሽው ሁሉን ነገር ስናሟላልሽ ምነው ወጥ ረገጥሽ" አለችኝ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ "ይኘውልሽ" ብዬ ወሬ ልጀምር ስል "በቃሽ ያ ወንድምሽን ይዘሽልኝ ከቤቴ ውልቅ በይ" አለችኝ፡፡ እንባዏቼ ወረድ የምናገረው ነገር ጠፋኝ ደርቄ ቀረሁኝ፡፡ "በያ ቶሎ በይ ከቤቴ ውጪ" አለችኝ፡፡ ይሄን ሁሉ ስትናገረኝ ብሩኬ ክፍሉ እቃ ሊያመጣ ሄዶ ነበር፡፡

አቤልን ጠርቼው ልብሳችንን መሰብሰብ ጀመርን፡፡ ከቤት ልንወጣ ስንል ብሩኬ ወዴት ነው አለኝ፡፡ ወ/ሮ ኤልሳም ሁሉንም ነገር ነገረችው፡፡ እጄን ይዞኝ "ማም እነሱ ከዚ ከሄድ እኔም እዚህ አልኖርም" አላት፡፡ "ብሩኬ አንተ እዚህ ነገር ውስጥ አትግባ ወደክፍልህ ሂድ" አለችው፡፡ "ማም አትፈልጊኝም!" አላት፡፡"እንዴት ነው የማልፈልግ" አለችው፡፡"እንግዲያውስ እኔ እዚህ ቤት እንድቆይ እነሱም እዚህ መሆን አለባቸው" አላት፡፡ "አይሆንም እነሱ እዚህ ቤት አንድም ቀን አያድሩም" አለችው፡፡ ከብሩክ እጅ ላይ እጄን መንጭቄ አቤልን ይዤ ከሳሎን ወጣን፡፡ ብሩክም ተከትሎን ወጣ፡፡ " አንዴ ላናግርሽ " አለኝ እኔም "እሺ አልኩት፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ በመስታወት እያየችን ነበር፡፡ ብሩክ ወደ ጓሮ ሄደን እንድናወራ ጋበዘኝ፡፡ ወደ ጓሮ ሄድን፡፡ "ምንድን ነው ብሩክ" አልኩት፡፡ "የትም አትሄዱም እዚሁ ትኖራላችሁ" አለኝ፡፡ ፈገግ እያልኩኝ "አይሆንም ከዚህ በኀላ እንድናስቸግራቹ አንፈልግም " ብዬ ጥዬው ልሄድ ስል እጄን ጎትቶ ከንፈሬን ሳመኝ..........

ክፍል 16 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ

CONTACT US ....