Get Mystery Box with random crypto!

......... የሀዘኔ መጨረሻ ........ ክፍል 17 .......እጄን ይዞ ወ | Campus love ❤ Stories

......... የሀዘኔ መጨረሻ ........

ክፍል 17

.......እጄን ይዞ ወደቤት አስገባኝ........ከዛን ቀን ጀምሮ ወ/ሮ ኤልሳ ለኔና ለአቤል ጥሩ ፊት አሳይታን አታውቅም፡፡ አቤልን ዝም ብላ ትቆጣዋለች እኔን ደግሞ ዝም ብላ ትገላምጠኛለች፡፡ እኔ ግን ባልሰማ ባላየ እላታለው፡፡እኔና ብሩኬ ቅልጥ ያለ ፍቅር ውስጥ ገባን፡፡ ወራቶች ተቆጠሩ ብሩኬም ወደ ዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና የሚወስድበት ቀን ደረሰ፡፡ ብሩኬ የማትሪክ ፈተናውን ካለፈ ወደሚደርሰው ዩንቨርስቲ እንደሚሄድ ሳስብ በጣም ይጨንቀኝ ጀመር፡፡ ብሩኬም በጣም ጨንቆታል፡፡ የፈተናው ቀንም ደረሰ፡፡ ብሩኬ በንፁህ ልቡ ፈተናውን እንዲሰራውና በጣም እንደምወደው ነግሬው ሸኘሁት፡፡

ፈተናውንም ተፈትኖ ወጣ፡፡ ፊቱ ላይ ፍርሀት ይታይበት ነበር፡፡ "ምነው ብሩኬ ፈተና ይከብድ ነበር እንዴ" አልኩት በጋ እያለኝ "ፈተናው በጣም ቆንጆ ነበር ግን ሰላሜ ፈተናውን ካለፍኩኝ የምለይሽ መስሎኝ በጣም ጨንቆኛል" ከለኝ፡፡ እቅፍ አድርጌው "ፈጣሪ ያለው ነው የሚሆነው አትጨነቅ" አልኩት፡፡ የፈተናውም ውጤት የሚለጠፍበት ቀን ደረሰ፡፡ እኔና ብሩኬ አብረን ሄደን ውጤቱን አየነው፡፡ ብሩኬ በጥሩ ውጤት አልፉል፡፡ ብሩኬ በጣም ደስ አለኝ ፡፡ ወድያው ወደ ቤት ተመለስን አቶ ሄኖክና ወ/ሮ ኤልሳ ውጤቱን ለመስማት ጓጉተው ነበር፡፡ እንደገባን ብሩኬ ውጤቱን ነገራቸው፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ቤቱን በእልልታ አቀለጠችው አቶ ሄኖክም በኩራት ወደ ብሩኬ ጠጋ ብለው ግንባሩን ሳሙት፡፡

ለምን ብሩኬ ፊት ላይ ደስታ እንደማይታይ ጠየቁት፡፡ እሱም " ማም ዳድ ማትሪክን በጥሩ ውጤት አልፌያለው እናንተም ይሄን ቀን ስትጠብቁት ነበር ......ግን እኔ ሌላ ሀገር መሄድ አልፈልግም እዚሁ መማር ነው የምፈልገው እባካቹ ወደ ሌላ ሀገር ሂድ እንዳትሉኝ "አላቸው፡፡ አቶ ሄኖክ ሳቃቸውን ገታ አድርገው ሶፋው ላይ ቁጭ አሉ፡፡

በድንገት ከሶፋው ላይ ተነስተው "ችግር የለውም ልጄ እዚሁ አለ የተባለ ኮሌጅ ውስጥ አስገባሀለው " አሉት ፡፡ ወ/ሮ ኤልሳም ፈገግ ብላ "አው ልጄ ከዚህ እንድትርቅ አልፈልግም አባትህ እንዳለው እዚሁ ትማራለህ " አለችው፡፡ ብሩኬም ዞር ብሎ የፊቱን ፈገግታ አሳየኝ እኔም ሳቅ አልኩኝ፡፡ ምሳችነነ መብላት ቀጠልን

ከትንሽ ሳምንታት በኀላ አቶ ሄኖክ ክፍሌ መጡ፡፡ በሩንም ከፈትኩላቸው በጣም ተናደው ነበር በጣም ደንግጬ " ምነው" አልኳቸው፡፡ ወሬውን ትቼ ወደ ክፍሌ እንድገባ ነገሩኝ ........

ክፍል 18 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ