Get Mystery Box with random crypto!

..የሀዘኔ መጨረሻ...... ክፍል 13 ሄድን፡፡ ይመስለኛል ........አቶ ሄ | Campus love ❤ Stories

..የሀዘኔ መጨረሻ......

ክፍል 13

ሄድን፡፡ ይመስለኛል ........አቶ ሄኖክ እና ወ/ሮ ኤልሳ ስለ ህይወታችን ነበር ሲያወሩ የነበረው፡፡ እኔና ወ/ሮ ኤልሳ አቶ ሄኖክ አስገብተውኝ ወደነበረው ክፍል አስገባችኝ ፡፡ ቅድም ደንግጬ ስለነበር የክፍሉን ውበት አላየሁትም ነበር ግን አሁን ሳደው በጣም ያምራል፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ፍልቅልቅ እያለች " የምታርፊበት ክፍል ይሄ ነው የወንድምሽም ክፍል ከጎንሽ ያለው ክፍል ነው ማለቴ በስተግራ ያለው< ብላ በእጅዋ ጠቆመችልኝ፡፡ ወድያው ከክፍሉ ወጣች፡፡ ተመልሳ መጥታ "የብሩኬ ክፍል በቀኝ በኩል ያለው ነው የሚቸግርሽ ነገር ካለ ጠይቂው" ብላኝ ሄደች፡፡ በጣም ደስ አለኝ ፈጣሪ ከላይ ሆኖ እንዳየኝ ተሰማኝ፡፡

በሩን ዘጋ አድርጌ አልጋው ላይ ጋደም አልኩኝ፡፡ ትንሽ የሰላም እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ከክፍሉ ልወጣ ስል ብርቄ ሻንጣዬን ይዛልኝ መጣች፡፡ ቶሎ ብዬ ከሻንጣው ውስጥ የቤዚን እና የሙሌን ፎቶ አውጥቼ በፈገግታ መመልከት ጀመርኩኝ፡፡ ወደላይ ቀና ብዬ" ፈጣሪዬ እንደዛ እንዳላዘንኩኝ አሁን ደስታው በተራው ተፈራረቀብኝ ተመስገን" አልኩት፡፡ ምግብ ክፍሌ ድረስ መጣልኝ እሱን በልቼ ሰሀኑን ለመመለስ ወደ ኩሽና አመራሁ ሳላስበው ከብሩክ ጋር ተጋጭተን ወደቅኩኝ " ውይ አላየሁሽም ነበር በጣም ይቅርታ "ብሎ አነሳኝ፡፡ እኔም ቆፍጠን ብዬ "ምንም አይደል " አልኩት፡፡ መንገዴንም ቀጠልኩኝ፡፡ እጄን ያዘኝ ዞር አልኩኝ፡፡ አይኖቹ በጣም ያምራሉ አፈጠጥኩባቸው "ስለ ቤተሰቦችሽ ስለ ሁሉም ነገር ዳድ ነግሮኛል አይዞሽ" አለኝ፡፡ አይኔን ከአይኖቹ መንጭቄ "አመሰግናለው " አልኩት፡፡ ፊልም አብረን እንድናይ ጋበዘኝ እኔም ትንሽ ከተግደረደርኩኝ በኀላ ግብዣውን ተቀበልኩኝ፡፡

ወደ ኩሽና ሄዶ ቺብስ ይዞ መጣ መብራቱን አጠፋፍተን ማየት ጀመርን፡፡ አጠገብ ለአጠገብ ነበር የተቀመጥነው እውነት ለመናገር ፊልሙን አየው ማለት አይቻልም እሱም ያየ አይመስለኝም፡፡ሁለታችንም እየሰረቅን ስንተያይ በልባችን ደግሞ ስናወራ ነበር፡፡ ፊልሙ አለቀ አቤልም ከት/ቤት ተመልሶ መጣ ፡፡ አቶ ሄኖክ እና ወ/ሮ ኤልሳ ያደረጉልንን ሲመለከት በጣም ደስ አለው፡፡ እሱ ስለተደሰተ የኔ ደስታ እጥፍ ድርብ ሆነ፡፡አቤል እና ብሩክ በጣም ተግባብተዋል አብረው ጌም ኳስ መጫወት ነው ስራቸው፡፡


በንደዚ አይነት ሁኔታ ለ3 ወር ኖርን፡፡ በአንድ እሁድ ቀን የጥቁር ልብሴን እንዳወልቀው አቶ ሄኖክና ወ/ሮ ኤልሳ ኮስተር ብለው ነገሩኝ፡፡ እኔም ሀዘኔን ለመግታች ወስኜ ጥቁር ልብሴን አወለቅኩኝ ፡፡ እናትና አባቴንም ያገኘሁኝ ያህል ተሰማኝ፡፡

አቶ ሄኖክ ስራቸው ፊልድ ነው እና ብዙም ጊዜ እቤት አይገኙም እኔና ብሩክም ከ3 ወር በፊት እንደነበርነው አይደለንም በጣም ተግባብተናል፡፡ ት/ት ቤታችንም አንድ ላይ ስለሆነ ተለያይተን አናውቅም፡፡ ብሩክ 12 ክፍል ሲሆን እኔ ደግሞ 11 ነኝ ስለዚህም በጣም ተግባብተናል፡፡

የት/ት አመት ግማሽ ላይ ደረስን፡፡ እናም እረፍት ወጣን፡፡ አቶ ሄኖክ እንደ ሁል ጊዜው ፊልድ ላይ ናቸው፡፡

እረፍት ከወጣን ከ 2 ቀን በኀላ የወ/ሮ ኤልሳ ወንድም ከጠዋቱ 3 ሰዐት አካባቢ መጣ.........

ክፍል 14 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ