Get Mystery Box with random crypto!

..........የሀዘኔ መጨረሻ...... ክፍል 12 ........ክፍል ውስጥ አስገብተው | Campus love ❤ Stories

..........የሀዘኔ መጨረሻ......

ክፍል 12

........ክፍል ውስጥ አስገብተውኝ ....." እኔ የአባትሽ ጓደኛ ነኝአይዞሽ እኔ አለሁላቹ አባትሽ እንድንከባከባቹ ቃል አስገብቶኝ ነበር ስለዚህ አብራቹ እዚ ከኛ ጋር ትኖራላችሁ፡፡ ደግሞ ትምህርትሽን እንዳቋረጥሽ ማታ ኤልሲ ነግራኛለች እና አሁን ትቀጢዋለሽ ብሩኬ የሚማርበት ት/ቤት ትገቢያለሽ " አሉኝ ፡፡ እውነት ለመናገር አቶ ሄኖክ እንደዛ ሲሉኝ በቃላት ልገልፃቸው የማልችለው ስሜት ተሰማኝ፡፡ ትንሽ ከቆየሁ በኀላ ቀና ብዬ " እና ለምን ለአባቴ ለቅሶ እቤት መጥተው አላፅናኑንም " አልኳቸው ፡፡ አቶ ሄኖክም " የኔ ስራ ፊልድ ነው እና ብዙ ጊዜ እዚህ ሀገር አልገኝም ለዛነው እና ለናትሽም ለቅሶ ጊዜ አልመጣሁም እና ይቅርታ አድርጊልኝ " አሉኝ፡፡ ፊት ለፊት የሚገኘው ወንበር ላይ ቁጭ ብለው በሀዘን ተውጠው "አባትሽ እስር ቤት አስጠረቶኝ ነበር....አው ከማረፉ ከ 2 ቀን በፊት አስቀድሞ የኔ ውድ ጓደኛ መሞቱ ታውቆት ነው መሰለኝ " ልጆቼን አደራ ....አደራ ሲለኝ ነበር ፡፡ ከዛ እኔ በንጋታው ወደ ሌላ ሀገር ለስራ ሄድኩኝ ፡፡ መሞቱን የሰማሁት እራሱ እዚህ ከመጣሁኝ በኀላ ነው " አሉኝ ፡፡ ሳላስበው እንባዬ ድብ ድብ አሉ፡፡


ከተቀመጡበት ተነስተው አጠገቤ ቁጭ አሉ ደረታቸው ላይ ለጥፈውኝ "እኔ እንደ አባትሽ ልሆንልሽ አልችል ይሆናል ግን እንደ አባትሽ እይኝ ምክንያቱም እኔ እንደ ልጄ ነው የማይሽ " አሉኝ፡፡ እቅፍ አደረግኳቸው፡፡

ወደ ማዕድ ቤት ተመለስን ብሩክ አቤልን ጉልበቱ ላይ አስቀምጦ ስልኩን ሰጥቶት ጌም እያጫወተው ነበር፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ደግሞ ቡና እየጠጣች ነበር ፡፡ አቶ ሄኖክ ወ/ሮ ኤልሳን " ውዴ አንዴ ነይ "አሉዋት፡፡ተነስታ ሄደች፡፡

አቤልም ት/ቤት ስለረፈደበት የብሩክ ሹፌር ወደ ት/ቤት ይዞት ሄደ፡፡ በፍጥነት ተነስቼ ቁርስ የበላንበትን እቃዎች ላነሳሳ ስል ብርቄ መጥታ " ተይው እኔ አነሳሳዋለው ጋሼ ምንም እንዳትሰራ ብለውኛል " ብላ እጄ ላይ ያለውን ሰሀን ተቀበለችኝ ፡፡ እኔም እሺ አልኳት፡፡ ማዕድ ቤቱና ሳሎን ቤቱ ብዙም አይራራቅም፡፡ ብሩክ ሳሎን ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ እያየኝ ነበር፡፡ ከዛ በአይኖቹ ነይ አለኝ፡፡ እኔም ሄጄ ሶፋው ላይ ቁጭ አልኩኝ፡፡

ሁለታችንም መነጋገር ፈልገናል ግን ፈርተናል የተቀመጥኩት ፊት ለፊቱ ስለነበር በጣም ጨነቀኝ የሆነ እንከን ያለብኝ ይመስል ተርበተበትኩኝ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኀላ "አስታወስሽኝ " አለኝ፡፡ እኔም በአዏንታ አንገቴን ነቀነቅኩለት፡፡ የሆነ እንግዳ ስሜት ተሰማኝ ፡፡

ወድያው ወ/ሮ ኤልሳ እየተፍለቀለቀች መጣች፡፡ "ሰላም" አለችኝ ከመቀመጫዬ ተነስቼ "አቤት " አልኳት፡፡ ፈገግ እያለች " ነይ" አለችኝ፡፡ አቶ ሄኖክ ወደ ብሩክ ጠጋ ብለው ትከሻውን መታ መታ እያደረጉ " ሰላምን ተንከባከባት እሷ ማለን ......" ብለው ጀመሩለት፡፡ እኔና ወ/ሮ ኤልሳ ወደ ላይኛው ክፍል ሄድን፡፡ ይመስለኛል ..........

ክፍል 13 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ