Get Mystery Box with random crypto!

....የሀዘኔ መጨረሻ...... ክፍል 11 .....ብሩክም እኛን ለማየት ዞር አለ ....ሲያየን | Campus love ❤ Stories

....የሀዘኔ መጨረሻ......

ክፍል 11

.....ብሩክም እኛን ለማየት ዞር አለ ....ሲያየን በጣም ደነገጠ የሱ ሲገርመኝ የወ/ሮ ኤልሳም ባለቤት በትኩረትና በትዝብት ይመለከቱን ጀመር፡፡ ...... ትንሽ ከተፋጠጥን በኀላ የወ/ሮ ኤልሳን ባለቤት አጠገቡ ሄዴ እጄን ለሰላምታ ዘርግቼ " ሰላም እባላለው "አልኳቸው እሳቸውም እጄን ለመጨበጥ እየተጣደፉ "ሰላም እንዴት ነሽ " አሉኝ፡፡ እኔም "ደህና " አልኳቸው ፡፡ አቤልን "ና የኔ ልጅ " ብለው አገላብጠው ሳሙት፡፡ ዞር አልኩኝና እጄን እንደመዘርጋት እያልኩኝ ብሩክን " ሰላም እባላለው አልኩት"እሱም እጄን ይዞኝ በሀሳብ ነጎደ ቶሎ ብዬ እጄን ከእጁ ላይ መነጨቅኩት

የወ/ሮ ኤልሳ ባለቤትም "እኔ ሄኖክ " እባላለሁኝ አሉን፡፡ እኔም ፈገግ ብዬ አቤልን ይዤ ልወጣ ስል አቶ ሄኖክ "ይቅርታ ሰላም " አሉኝ እኔም ሊያዙኝ መስሎኝ ዞር ብዬ "አቤት " አልኳቸው ፡፡ " ባልሳሳት የኮንስትራክሽን ባለሞያው የሙሉጌታ ልጆች ናችሁ አይደል " አሉን፡፡ ይህን ስሰማ አባቴ ትዝ ብሎኝ ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡ አቤልም አለቀሰ ከትንሽ ደቂቃዎች በኀላ እንባዬን እየጠራረኩኝ በኩራት "አዎ" አልኳቸው፡፡ አቶ ሄኖክም " ስለ ሙሉጌታ ሁሉንም ነገር ሰምቻለው እንደውም ላፈላልጋቹ ነበር "አሉን፡፡ ወ/ሮ ኤልሳ ወደ አቶ
ሄኖክ ዞር እያለች " ለምንድን ነው ልታፈላልጋቸው የነበረው ውዴ " አለቻቸው ፡፡ " የአባታቸው አደራ አለብኝ " ብለው ፈገግ አሉ፡፡ ብሩክ አሁንም ደንግጦ አፉን ከፍቶ እየተመለከተን ነው ፡፡ እኔም ባላየ ባላወቀ ማለቴን ቀጥያለው፡፡ ቁርስ አብረናቸው እንጅንበላ አቶ ሄኖክ ጋበዙን፡፡ እኔና አቤልም አሻፈረን አልን ፡፡

ኮስተር ሲሉብን አብረናቸው መመገብ ጀመርን፡፡ የተቀመጥኩት ከብሩክ ፊት ለፊት ነበር፡፡በጣም ጨነቀኝ ብሩክም ቁርሱን ትቶ እኔን በዝምታ ማየቱን ቀጥሎል፡፡ እያየኝ መሆኑን ለማወቅ ቀና ስል አይን ለአይን እንገጣጠማለን በፍጥነት አይኔን ከአይኖቹ ነጥዬ ምግቡነ መመልከት እጀምራለው፡፡ ከትንሽ ደቂቃዎች በኀላ ወ/ሮ ኤልሳ ብሩክን "በላ የኔ ልጅ እንዳይረፍድብህ ሂድ" አለችው ፡፡ እሱም እኔ ላይ እያፈጠጠ ማም ዛሬ ክላስ አልሄድም" አላት፡፡ ከመቀመጫዋ ተነስታ የብሩክን ጭንቅላት እየነካካች በድንጋጤ "ምነው ልጄ አመመክ እንዴ " አለችው ፡፡ አይኑን ሰበር አድርጎ " አይ ትንሽ ስለደበረኝ ነው " አላት፡፡ አቶ ሄኖክም " በቃ ተይው ውዴ ዛሬ እረፍት ያድርግ "አሏት፡፡ "እሺ በቃ" ብላ ተቀመጠች፡፡

ወድያው አቶ ሄኖክ ከመመገቢያ ክፍሉ ወጡ፡፡ እኔም እቃውን ለማነሳሳት ተነሳሁኝ፡፡ አቶ ሄኖክ ብቅ ብለው "ሰላም እሱን ተይውና አንዴ ነይ እፈልግሻለው " አሉኝ፡፡ እኔም " እሺ" ብዬ ሄድኩኝ፡፡

ከብሩክ አጠገብ ያለ ክፍል ውስጥ አስገብተውኝ...........

ክፍል 12 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ