Get Mystery Box with random crypto!

....የሀዘኔ መጨረሻ ....... ክፍል 10 ......ዞር ብዬ 'አቤት | Campus love ❤ Stories

....የሀዘኔ መጨረሻ .......

ክፍል 10

......ዞር ብዬ "አቤት" አልኳት "እንግዲህ.....ደሞዝሽ 1500 ብር ነው፡፡ ወንድምሽን እኔ አስተምረዋለው አታስቢ" አለችኝ፡፡ የማደርገው ግራ እንደገባኝ "እሺ" ብያት ሄድኩኝ ፡፡ ግን በቀን ውስጥ የምሰራውን ስራ ሳስበው በጣም እንደሚከብደኝ ተረዳሁኝ፡፡ ግን ለአቤል ብዬ መስራት አለብኝ አልኩና እራሴን አፅናናሁኝ፡፡

ሰዐቱ 12:30 ይሆናል ወ/ሮ ኤልሳ እኔንና አበራ ወደ ገበያ ላከችን፡፡ እኛም ሄድን ግን ታክሲ አጥተን ስለነበር ከምሽቱ 3 ሰዐት ነበር የተመለስነው የግቢውን ቀር ከፍተን እንደገባን ወ/ሮ ኤልሳ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ "ለምንድን ነው በዚህ ሰዐት የመጣችሁት አንደኛችሁን አታድሩም ነበር" አለችን፡፡ አበራም " ታክሲ አጥተን ነው እኮ እሜቴ" አላት፡፡አበራ ማለት የቤቱ ዘበኛ ነው፡፡ እኔ ግን አንገቴን ዘቅዝቄ ዝምታን መረጥኩኝ ወ/ሮ ኤልሳ እየተኮሳተረች "በይ አሁን ወደውስጥ ገብተሽ እራትሽን በልተሽ ተኚ ነገ ብዙ ስራ ይጠብቅሻል" አለችኝ ፡፡እኔም አንገቴን እ! ዳቀረቀርኩኝ "እሺ" ብያት ገባሁኝ፡፡ ቀጥታ ወደ መኝታ ክፍሌ ነበር የገባሁት የእውነት ቀዛ ሰዐት ማልቀስ ፈልጌ ነበር፡፡ ግን ፊትለፊቴ አቤል ተኝቶ ሳየው እና የቤዚ ቃል ትዝ ሲለኝ አቤልዬን እቅፍ አድርጌው ተኛው፡፡

በለሊት ብርቄ መጥታ ቀሰቀሰችኝ እኔም ተነስቼ ምግብ ቀመስራት አገዝኳት ...ከዛ የወ/ሮ ኤልሳን ልጅ ለመቀስቀስ ወደ መኝታ ክፍሉ ሄድኩኝ ፡፡ ..ስገባ በጣም ደነገጥኩኝ ያ እንዳውም ሁለት ጊዜ ቤተክርስቲያን አግኝቼው ሊያዋራኝ ፈልጎ ጥዬው የሄድኩት ልጅ ነበር፡፡ በፍጥነት ከክፍሉ ወጣሁኝ በሩ ጋር ቆሜ ተገረምኩኝ፡፡ በፍጥነት ወደ መክታ ክፍሌ ሄጄ ሻርፕ ኮፍያ ያለው ሹራብ ምናምን አድርጌ ተመልሼ ብሩክን ለመቀስቀስ ወደ ክፍሉ አመራሁኝ፡፡ ቀሰቀስኩት መነሳቱን እንዳረጋገጥኩኝ ከክፍሉ ልወጣ ስል .... እጄን ያዘኝ እኔም የለበስኩትን ሻርፕ አስተካክዬ ወደሱ ዞርኩኝ "አቤት " አልኩት እሱም ማነሽ አለኝ ፡፡ ፊቴን እየሸፋፈንኩኝ "አዲስዋ የቤት ሰራተኛ ነኝ" አልኩት፡፡ እጄን ለቀቀኝና እጁን በቀሽም ስሜት ፀጉሩ ላይ ጣል አድርጎት "ይቅርታ ማም ነግራኝ ነበር ፡፡ በጣም ይቅርታ " አለኝ፡፡ እኔም " እሺ" ብዬው ብዬ ከክፍሉ ወጣሁኝ ፡፡ ከክፍሉ እንደወጣሁኝ ተሰምቶኝ የማያውቅ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡

በመቀጠል ትላንት ወ/ሮ ኤልሳ ስትዘረዝርልኝ የነቀረውን ስራ ወስራት ጀመርኩኝ፡፡ ወደ ምግብ መመገቢያው ክፍል ልገባ ስል ብሩክ እንደሚያውቀኝ ትዝ ሲለኝ ወደ ውስጥ መግባት ደበረኝ፡፡ ውጪ ቁጭ አልኩኝ ፡፡ አቤል ከእንቅልፉ ተነስቆ ዩኒፎርሙን ለብሶ ወደኔ መጣ ፡፡ "የኔ ቆንጆ በጣም አምሮብሀል" ብዬ እቅፍ አደረኩት፡፡ ወድያው ብርቄ መጣችና ወ/ሮ ኤልሳ እየጠራቺኝ መሆኑን ነገረችኝ ፡፡ መሄድ አልፈለኩም ነበር ግን ግድ ስለሆነ አቤልን ይዤው ወደ ምግብ መመገቢያው ክፍል አመራሁ፡፡ ልክ ክፍሉ ውስጥ እንደገባሁኝ ወ/ሮ ኤልሳ "ውይ መጣቹ ኑ ልጄንና ባለቤቴን ተዋወቁዋቸው " አለችን ፡፡ እኔም ወደ ጠረቤዛው ቀረብ አልኩኝ ብሩክም እኛን ለማየት ዞር አለ .........


ክፍል 11 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ .....