Get Mystery Box with random crypto!

..የሀዘኔ መጨረሻ ..... ክፍል 9 .....አንኳኳን.... የግቢውን በር | Campus love ❤ Stories

..የሀዘኔ መጨረሻ .....

ክፍል 9

.....አንኳኳን.... የግቢውን በር የከፈተልን የጥበቃ ሰራተኛው ነበር፡፡ ከማስቴ አክስት ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኀላ ወደ ውስጥ ገባን ወድያው የቤቱ ባለቤት መጣች ፡፡ የማስቴን አክስት በግርምት እየተመለከተቻት ''እንዴት ዛሬ መጣሽ አለቻትጠ'' የማስቴ አክስትም የመጣችበትን ጉዳይ ነገረቻት፡፡ ከዛ ወደ ውጪ እንነጋገር አለቻት፡፡ ካወሩ በኀላ ተመልሰው መጡ፡፡ ሴትየዋ እጄን እንደመጨበጥ አያለች "ኤልሳ እባላለው "አለችኝ ፡፡ እኔም እራሴንና አቤልን አስተዋወቅኩዋት፡፡ ''ዘነቡ ሁሉንም ነገር ነግራኛለች አይዟቹ አሺ" አለችን፡፡ እኔም እሺ አልኳትና እጄን የአቤል ትከሻ ላይ ጣል አደረኩት፡፡ ዘነቡ ማለት የማስቴ አክስት ናት፡፡

ትንሽ ቁጭ ካልን በኀላ ዘነቡ በይ ማስቴ ተነሺ እንሂድ" አለቻት፡፡ ማስቴም "እንዴ አክስቴ ግን እኮ"ብላ ልታወራ ስትል ወ/ሮ ኤልሳ "መስታወት ሁሉን ነገር ዘነቡ ነግራኛለች አይዞሽ እኔ አለው "አለቻት፡፡ ማስቴ በሀሳቡ ባትስማማም ግን ምንም ማድረግ ስላልቻለች እኔንና አቤልን ተሰናብታ ከአክስቷ ጋር ሄደች፡፡ወ/ሮ እስከግቢው በር ድረስ ሸኘቻቸው፡፡ ወደ እኛ ጋር መጥታ እኔና አቤል የምንናልፍበትን ክፍል አሳየችን ፡፡ በመቀጠል የስራ ድርሻዬን መዘርዘር ጀመረች፡፡

"ጠዋት ከእንቅልፍሽ 12 ሰዐት ትነሻለሽ ከብርቄ ጋር ቁርስ ትሰሪያለሽ " ብርቄ ማለት እነሱ ቤት የምትሰራ የቤት ሰራተኛ ናት፡፡ ከዛ ብላ ትዕዛዝዋን ቀጠለች፡፡ "ልጄን መኝታ ክፍሉ ሄደሽ ትቀሰቅሺዋለሽ እሱ ከመኝታ ክፍሉ እንደወጣ ክፍሉን በደንብ ታፀጃለሽ፡፡ በመቀጠል እኛ ቁርስ ልንበላ ወደ ማዕድ ቤት ስንሄድ የኔና የባለቤቴን መኝታ ክፍል ታፀጃለሽ፡፡እሱን እንደጨረሽ ከብርቄ ጋር ሆናችሁ እቃውን አጣጥባቹ ቤቱን በደንብ አስተካክላቹ እንደጨረሳቹ ምግባቹን ትበሉና አንቺ ከዘበኛው ጋር ገበያ ሄደሽ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ገዛዝተሽ ትመጫለሽ፡፡ እዚህ ቤት ምሳ ብዙም አይደለንም ብሩኬ ት/ቤት ይዞ ይሄዳል ባለቤቴ ደግሞ ውጪ ነው የሚበላው ስለዚህ ምሳ ሰዐት ላይ ብዙም ስራ አይበዛብሽም" አለችኝ ብሩኬ ያለችው ልጆን ነው፡፡

" ከሰዐት በኀላ ብዙም ስራ የለም ግቢውን ታፀዳጃለሽ ከዛ 11 ሰዐት አካባቢ ብርቄን የሚታገዝ ነገር ካለ ታግዢያትና እረፍት ታረጊያለሽ ከዛ እራትሽን በላልተሽ ትተኛለሽ" አለችኝ፡፡ እኔም በእሺ ስሜት አንገቴን ነቀነቅኩላት፡፡ "በይ እሺ ለዛሬ ከብርቄ ጋር ሁኚ " ብላ የኩሽናውን በር አሳየችኝ እሺ ብዬ ልሄድ ስል "ሰላም" አለችኝ እኔም ዞር ብዬ "አቤት" አልኳት "እንግዲ.........

ክፍል 10 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ