Get Mystery Box with random crypto!

የሀዘኔ መጨረሻ...... ክፍል 8 .......'ልጄ እናትሽ.....የምትለኝን አል | Campus love ❤ Stories

የሀዘኔ መጨረሻ......


ክፍል 8

......."ልጄ እናትሽ.....የምትለኝን አልሰማሁም ለዚህ ሁሉ ነገር ተጠያቂው እኔ ነኝ እባክሽ ይቅር በይኝ "አለኝ፡፡ በስስት እየተመለከትኩት "የኔ አባት ምንም አላጠፋህም እኮ" አልኩት:: ወድያው ትንፋሹ መቆራረጥ ጀመረ፡፡" አባ" ብዬ ፊቱን ደባበስኩት ፡፡ አባቴ ጨክኖ የዛን ቀን ወደማይመለስበት ጥሎን ሄደ፡፡ ላብድ ደረስኩኝ እግዛብሄር ምን አድርጌው ይህንን ሁሉ ስቃይ እንዳመጣብኝ ማወቅ ፈለኩኝ ፡፡ ወድያው እራሴን ሳትኩኝ ፡፡

ከነቃሁኝ በኀላ ለመጠንከር ወሰንኩኝ፡፡ የወንድሜ ሀላፊነት አለብኝና ጠንካራ ለመሆን ለራሴ ቃል ገባሁኝ፡፡ ሙሌ ተቀበረ ቤታችንም ሀዘን ላይ ስለነበርን ለ1 ሳምንት ተጨማሪ ጊዜ ሰጡን ፡፡ ሳምንቱም አለቀ ያ ሰውዬ መጥቶ ከቤቱ አሶጣን ፡፡ እንደቀልድ ከተወለድንበት ያ ብዙ ደስታ ካየንበት ቤት ወጣን ፡፡ ስንወጣ የቤዚን እና የሙሌን ፎቶ ብቻ ይዘን ነበር የወጣነው ፡፡ ማስቴ ማልቀስ ጀመረች "በቃ አይዟቹ እኔ አንድ የማውቃት ዘመዴ አለች እሷ ጋር እንሄዳለን" ብላ ይዛን ሄደች፡፡ እዛ ስንደርስ ቤቱ 1 ክፍል ነበር ማስቴ ዘመዴ ያለችው አክስትዋን ነበር በጣም ደግ ናት፡፡ ምግብ ሰጥታን አሳደረችን፡፡ግን እንደዚህ ሊቀጥል እንደማይችል ገባኝ በንጋታው ስራ ለመፈለግ ሄድኩኝ ፡፡ ቀኑን በሙሉ ስዞር ዋልኩኝ ግን ስራ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ አቤልም ተጨነቀብኝ ለኔ ከባድ የህይወት ደረጃ ላይ የደረስኩኝ ያህል ተሰማኝ፡፡

ይህንን ያየች የማስቴ አክስት በጣም አሳዘንናት "በሉ አሁን አንድ ቦታ እንሂድ "አለችን ማስቴም "የት ነው የምንሄደው "አለቻት ፡፡ "አንድ ልብስ የማጥብላት ሴት አለች እና ሰራተኛ ትፈልጋለች፡፡ ደግሞ እነሱም ማረፊያ ያገኛሉ" አለቻት ፡፡ ማስቴ ሳቅ እያለች "አይ አክስቴ ሰሊ እኮ ምንም ስራ መስራት አትችልም "አለቻት ከተቀመጥኩበት ተነስቼ "ችግር የለውም ማስቴ 2 ቀን ሰው ካሳየኝ ሁሉንም ነገር ማድረግ አያቅተኝም" አልኳት ፡፡እሷም" ሰሊ ይሄ ስራ እኮ ላንቺ አይገባሽም" አለችኝ፡፡ኮስተር ብዬ አቤልን እየተመለከትኩት " አቤል አንዴ ውጣ "አልኩት እሱም እየተነጫነጨ ወጣ፡፡ እሱ እንደወጣ የማስቴን እጅ ይዣት "ማስቴ እኔ እኮ ትንሽ ልጅ አይደለሁም ወንድሜን ማስተዳደር ያለብኝ ትልቅ ሴት ነኝ፡፡ "አልኳት አይኗ ውስጥ እንባዎች ተጠራቀሙ "ማስቴ አንቺ እኮ ቤተሰቤ ነሽ ለዛ አይደል እስከዛሬ ያልተለየሽን "ስላት "እንዴት እተዋችኀለው" አለችኝ" እኮ አሁን ዕድል ሲመጣልኝ ፍቀዲና ሸኚኛ" አልኳት እቅፍ አደረገችኝ "ግን ሰሊ እራስሽንም ወንድምሽንም መጠበቅ አለብሽ እሺ" አለችኝ ማስቴ ወደ አክስቷ ዞር አለችና "ግን ሁሉን ነገር እስክትለምደው አብሬያት እሆናለው" አለቻት አክስቷም "ችግር የለውም ሴትየዋን ስለምግባባት እናስፈቅዳታለን" አለቻት፡፡ ትንሽ ቁጭ ካልን በኀላ ወደ ሴትየዋ ቤት ሄድን ፡፡ ቤቱ በጣም ትልቅ ነበር ፡፡ አንኳኳን.....

ክፍል 9 እንዲቀጥል ማድረግ አትርሱ...

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━