Get Mystery Box with random crypto!

.......የሀዘኔ መጨረሻ....... ክፍል 7 ..........መንገዴን ቀጥያለው .. | Campus love ❤ Stories



.......የሀዘኔ መጨረሻ.......

ክፍል 7

..........መንገዴን ቀጥያለው ... በድንገት ቆም ብዬ "አቤት" አልኳቸው ማስቴ "ምን ሆነሻል ልጁን ልትገይው ነው እንዴ" ብላ እጄን ከአቤል እጅ ላይ አስለቅቃ አቤልን ያዘችው ፡፡ ተንበርክኬ "ውይ አቤልዬ ይቅርታ "አልኩት:: መንገዳችንንም ቀጠልን እቤት እንደደረስን 2 ፖሊሶች እና አንድ ቀን ቤታችን መቶ የቤቱን ካርታ የወሰደውሰውዬ መጡ፡፡በሩን የከፈትኩላቸው እኔ ነበርኩኝ:: "አቤት" አልኳቸው:: ሰውዬው በኩራት "አባትሽ ብሬን በጊዜው ስላልከፈለኝ አሁን ቤቱን አወርሰዋለው" አለኝ::

በመንግስት ደረጃ አራጣ አበዳሪ መሆን ያስቀጣል ግን ለምን ፖሊሶቹ ለምን እንደመጡ አልገባኝም ስገምት በገንዘብ ገዝቷቸው ነው መሰለኝ ::

ከዛ ብዬ ላወራ ስል አንደኛው ፖሊስ ቤቱን" በ 1 ሳምንት ልቀቁ አለበለዛ የማይሆን ነገር ይፈጠራል" አለኝ ፡፡ ከዛ ሶስቱም ሄድ በሩን ዘግቼ በርስር ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ ወድያው አቤል መጣ:: መምጣቱን ሳይ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንባዬን ጠራረኩኝ" አቤልዬ አልኩት"፡፡ "ሰሊ ምነው አለኝ ""ምንም አልሆንኩም አልኩት" "ሰሊ ቤተክርስቲያን እንሂድ "አለኝ ::እኔም እሺ አልኩት ወድያው ለባብሰን ወደ ቤተክርስቲያን ሄድን ፡፡አቤል ለመሳለም ሄደ እኔም ተንበርክኬ "ምን አጠፋን ምን ለምን እንደዚ ታደርጋለህ "እያልኩ ማልቀስ ጀመርኩኝ ፡፡ አቤል እየሮጠ መጣና "እህቴ እባክሽ ተነሺ" አለኝ፡፡ እኔም ቶሎ ብዬ ተነስቼ ወደ መቀመጫ ቦታው ሄደን ተቀመጥን አቤል "እህቴ እባክሽ እንደዚህ አትሁኚ" ብሎ እቅፍ አደረገኝ:: ማልቀሴን ማቆም አልቻልኩም አታልቅሺ አለኝ ሳቅ እያልኩኝ እንባዬን እንደመጠራረግ አድርጌ "ይኜው ካሁን በኀላ አላለቅስም" አልኩት....

ትንሽ ቁጭ እንዳልን ያ እንዲየውም አንድ ቀን መጥቶ እጄን የያዘኝና ሰዐት የጠየቀኝ ልጅ አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ ፡፡ ብዙም አላስተዋልኩትም ነበር ፡፡ "ሰላም" አለኝ ፡፡ እኔም ዞር ብዬ "አቤት "አልኩት ሳየው ደነገጥኩኝ "ስምሽ ሰላም ነው እንዴ" አለኝ "አው ምነው" አልኩት ፡፡ አይ ምንም ብሎ "እኔ ደግሞ ብሩክ እባላለው" ብሎ እጁን ለሰላምታ ሲዘረጋ አቤልን በል ተነስ አሁን እንሂድ አልኩት፡፡ አቤልም ተነሳ የአቤል ትከሻ ላይ እጄን ጣል አድርጌ ዞር ስል ብሩክ እጁን እንደዘረጋ ነው፡፡" መጨባበጡ አስፈላጊ አይመስለኝም ስለዚህ እጁህን ሰብስበው" ብዬ አቤልን ይዤ ሄድኩኝ፡፡ቀናት እንደጉድ እየፈጠኑ ቤቱን ልቀቁ የተባልንበት ቀን ደረሰ፡፡ ሙሌን ለማግኘት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄድኩኝ፡፡

ናፍቆታችንን ከተወጣን በኀላ ስለ ቤቱ ሁሉንም ነገር ነገርኩት፡፡ በጣም ደነገጠጠ ከዛ እራሱን ሳተ በመሀከላችን የብረት አጥር ስለነበረ ልይዘው አልቻልኩም ፡፡ "ወይኔ አባቴ" እያልኩኝ መጮህ ጀመርኩኝ ፡፡ ወድያው ፖሊሶቹ አንስተው ወሰድት፡፡ ወደ አንድ ክፍል ነበረ ያስገቡት ተከትያቸው ገባሁኝ ሊያሶጡኝ ሞከሩ አልወጣም አልኳቸው ጉልበት መጠቀም ጀመሩ ወድያው ሙሌ ነቃ ፡፡ ከእጃቸው እራሴን ፈንጥቄ አውጥቼ ሙሌን አቀፍኩት ፡፡" አባ እኔ አልችልም አንተንም ቤዚንም አጥቼ መኖር አልችልም" አልኩት፡፡ በትኩረት እያየኝ "ልጄ እናትሽ ......

ክፍል 8 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ..

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share