Get Mystery Box with random crypto!

የሀዘኔ መጨረሻ.... ክፍል 14 .......3 ሰዐት አካባቢ የ | Campus love ❤ Stories

የሀዘኔ መጨረሻ....


ክፍል 14

.......3 ሰዐት አካባቢ የወ/ሮ ኤልሳ ወንድም መጣ፡፡ እናም ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ "ይልማ እባላለው" አለኝ፡፡ እኔም የውሸት ፈገግታ ፊቴ ላይ ጣል እያደረግኩኝ "እኔ ደግሞ ሰላም እባላለው" አልኩት፡፡ ሲጀመር ይልማን ቀልቤ አሎደደውም ይሄን ደግሞ ብሩኬ አውቋል፡፡ ግን ግድ ስለሆነብኝ ቁጭ አልኩኝ ከትንሽ ቆይታዎች በኀላ ይጨንቀኝ ጀመር፡፡ ይልማ በሚያስጠላው ፊቱ ፈገግ ሲልብኝ የምሰራው ስራ አለ ብዬ ተነስቼ ወደክፍሌ ሄድኩኝ፡፡ ብሩኬም ተከትሎኝ መጣ፡፡ " ሰሊ አጎት ተብዬውን አልወደድሽውማ" አለኝ ፡፡ በአዎንታ አንገቴን ነቀነቅኩለት፡፡ በፈገግታ እያየኝ ግንባሬን ስሞኝ ወጣ፡፡ ወዱያው አቤል መጣና video game መጫወት ጀመርን፡፡

ከዛን ቀን ጀምሮ ይልማ እቤት ይመላለስ ጀመር፡፡ በቀን2 3 ጊዜ መምጣት ጀመረ፡፡ እኔም በራስ መተማመኔ እየተመናመነ ሄደ፡፡ ጭራሽ ወደ ክፍሌ እየወጣ በኩራት "ሰላም እንዴት ነሽ" ይል ጀመረ፡፡ እኔም እየተሳቀቅኩኝ "ደና" እለዋለው፡፡ የኔና የብሩክ ክፍል አጠገብ ለአጠገብ ስለነበረ ድምፅ ያሰማል ብሩክ የይልማን ድምፅ ሲሰማ ወድያው ይመጣል፡፡ ይልማ ብሩክ መምጣቱን ሲመለከት በፍጥነት ይሄዳል፡፡ ብሩክም ይልማ እንደማይመቸው ሁኔታዏች ያሳብቃሉ፡፡ ብዙን ጊዜ የማሳልፈው ክፍሌ ነው፡፡

ቅዳሜ ቀን ጠዋት አካባቢ ነበር ....አቤልና ብሩኬ ሳይክል ለመንዳት ወጥተው ነበር፡፡

ይልማም እንደ ሁል ጊዜው በጠዋት ነው የመጣው፡፡ ይልማ እንደመጣ ወ/ሮ ኤልሳ ብርቄን ጠርታት ወደገበያ ሄድ፡፡ በቤቱ ውስጥ የነበርነው እኔና ይልማ ብቻ ነበርን፡፡ከክፍሌ እንደወጣሁኝ ይልማን አገኘሁት፡፡ እየተርበትበትኩኝ ሰላም አልኩት፡፡ እሱም ሰላምታ ሰጠኝ፡፡ ቶሎ ብዬ ወደ ታች ወረድኩኝ፡፡ ታች ስወርድ ማንም አልነበረም፡፡ እሱም ተከትሎኝ መጣ፡፡ በፍርሀት "ማንም የለም እንዴ" አልኩት፡፡ እሱም እየተጠጋኝና እየሳቀ "አ.....ው ማንም የለም" አለኝ፡፡ ፈርቻለው ግን ፍርሀቴ እንዲታወቅብኝ አልፈለኩም ነበር፡፡ ፈገግ ብዬ "እሺ" አልኩትና እየሮጥኩኝ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ ክፍሌንም ቆለፍኩት፡፡

ከ5 ደቂቃ በኀላ የክፍሌ በር ተንኳኳ፡፡ በድንጋጤ "ማነው" አልኩኝ፡፡ "ይልማ ነኝ ክፈቺልኝ" አለኝ፡፡ እየተንቀጠቀጥኩኝ ሆዴን አሞኛል ልተኛ ነው" ስለው በቁጣ ስሜት "ክፈቺ ብዬሻለው አለበለዚያ በሩን እሰብረዋለው" አለኝ፡፡ በጣም ፈራሁ መልስም አልሰጠሁትም ፡፡ በሩን ለመክፈት ትግል ጀመረ የማደርገው ጠፍቶኝ አልጋዬ ላይ ቁጭ አልኩኝ፡፡ ከብዙ ትግል በኀላ ክፍሌን ሰብሮት ገባ፡፡ በአን እጁ ቢራ በአንዱ ደግሞ ቢላ ይዞ ነበር ፈገግ እያለ "... ዛሬ .....ብቻችንን ተገናኘን አይደል ቆንጂዬ .....አለን፡፡ ከክፍሉ ለመውጣት ስሞክር ገፍትሮ አልጋው ላይ ጣለኝ፡፡ መጮህ ጀመርኩኝ ፡፡ እየታገለ ሱሪዬን በያዘው ቢላ መቆራረጥ ጀመረ፡፡ እያለቀስኩኝ ተወኝ አልኩት እሱ ግን ጭራሽ የያዘውን ቢራ እላዬ ላይ ማፍሰስ ጀመረ..........

ክፍል 15 እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ


Any comments inbox @Juliiian