Get Mystery Box with random crypto!

እንደው ህዝቡ ተዘረፈ አንድ እንኳ ስርዓት የሚያስዝ ጠፋ ______________________ ባለ | Hunda Eda Tube

እንደው ህዝቡ ተዘረፈ አንድ እንኳ ስርዓት የሚያስዝ ጠፋ
______________________
ባለተሽከርካሪዎች በነዳጅ ጭማሪና በታሪፍ ማሻሸያ ሽፋን በህዝባችን ዘረፋ እያካሄዱ ነው።

በ32 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ 60 እና ከዚያ በላይ እያስከፈሉ ህዝብን ሲዘርፉ ሀይ ባይ መስሪያ ቤት እንኳ ጠፋ

በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን አሁን በአዲስ ከተሻሻለውም ታሪፍ በላይ መጀመሪያውኑ ከባድ ዘረፋ ሲካሄድ ሀይ ባይ ጠፍቷል።

የህግ ያለ ኑሮ ውድነቱ ያቃጠለው ህዝባችን ለህክምና ቀጠሮ እንኳ ሆስፒታል መድረሻ ብር ከፍሎ በቀጠሮ ቀን ለመድረስ እያቃተው ነው

ከታች ያለው የታሪፍ ማሻሸያ ሳይደረግ በፊት እንኳ አሁን የተሻሻለውን እጥፍ ትራንስፖርት እየከፈልን ነበር።ለማንኛውም ቢያንስ አሁን በተሻሻለው ወቅታዊ ታሪፍ ይሁን እንጂ ህዝብ አይዘረፍ

የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ ከዚህ በታች ቀርቧል:-
➙➙➙➙➙➙➙➙➙
- በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5360 ሲሆን አዲሱ ታሪፍ 0.560ዐ ብር በኪሎሜትር ሆኗል፡፡ ጭማሪ በኪሎ ሜትር ዐ.0240 ሳንቲም ነው፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0.6150 ሲሆን አዲስ ታሪፍ ዐ.6464 ነው፡፡ ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር ዐ.0314 ሳንቲም ይሆናል፡፡

- ደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር ዐ.5120 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.5420 ነው፡፡ ጭማሪ ዐ.030ዐ ሳንቲም፡፡

ደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር ዐ.5680 ሲሆን አዲስ ታሪፍ ዐ.6054 ብር ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር ዐ.0374 ሳንቲም፡፡

– ደረጃ ሶስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር ዐ.4750 ሲሆን አዲስ ታሪፍ ዐ.5081 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር ዐ.0331 ሳንቲም ነው፡፡