Get Mystery Box with random crypto!

​​ .... የእውነት ማሰብ ደከመኝ በማሰቤ ጭንቀት እንጂ ምንአተረፍኩ....የእውነት ማሰብ | Brukti poem❄💖

​​ ....

የእውነት ማሰብ ደከመኝ በማሰቤ ጭንቀት እንጂ ምንአተረፍኩ....የእውነት ማሰብ አቁሜ ባለማሰብ ውስጥ መኖር ፈለኩኝ....ግን ይቻላል እንዴ? እንጃ ግን እንደ አዲስ እንደተወለደ ህፃን ምንም እንደማያውቅ ሁሉ እኔም እንደሱ መሆን ፈለኩ ሁሉንም ረስቼ ምንም ተፈጥሮ እንደማያውቅ ሆኜ መኖርን ተመኘው ህመሜ ህመም ተብሎ መግለፅ እስኪያቅት ድረስ ታመምኩ....የእውነት አሁን ደህና መሆን ፈለኩ አዲስ ሰው መሆን ግን እችል ይሆን? አላውቅም ግን እራስወዳድ ሆኜ ሳይሆን ህመሜን መቋቋም የማልችልበት ደረጃ ላይ ስደርስ በቃ ደህና መሆን ፈለኩ...