Get Mystery Box with random crypto!

መንታ መንገድ ይላል አርዕስቱ 'መንታ መንገድ ፊት ቆሞ ፈራጁ፣ ምረጥ ተባለ ከመንገዶቹ፣ ግራዉን መ | Brukti poem❄💖

መንታ መንገድ
ይላል አርዕስቱ
"መንታ መንገድ ፊት ቆሞ ፈራጁ፣
ምረጥ ተባለ ከመንገዶቹ፣
ግራዉን መንገድ እየወደደዉ
ለሀይማኖት ሲል ቀኙን መረጠዉ።
ቀኝ በጎ ነዉ ሲባል የሰማ፣
ነገዉን ብሎ ግራዉን ያማ፣
ሚስኪን አፍቃሪ ፍቅሩን ተቀማ።
ግራዉ ፈራጁን ማግኘት ቢነፈግ፣
ፈገግታ ሰጡት ለቅሶ ሚሸሽግ።
ሳቀ ሳቀና አንብቶ አንብቶ፣
ፈራጅን ሲያልም ዉሎ አምሽቶ፣
ተስፋ ሲቆርጥ ፣ ፈርሶ አደረ፣
ከተጠራበት ፣ ከህይወት ቀረ።"