Get Mystery Box with random crypto!

ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ brana_book — ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
የቴሌግራም ቻናል አርማ brana_book — ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
የሰርጥ አድራሻ: @brana_book
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 373

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2022-07-31 18:27:58 እግዚአብሔርን "በትዕዛዝ" ሳይሆን በውዴታ ሁልጊዜ እናመሰግነዋለን። ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ "Life of Thanksgiving" በሚል ርዕስ ያዘጋጁትና "የምስጋና ሕይወት" በሚል ወደ አማርኛ የተተረጎመውን ድንቅ መጽሐፍ ዛሬ ልጋብዛችሁ። መጽሐፉን በእንግሊዝኛም በአማርኛም በሁለት አማራጭ ከታች አስቀምጨዋለሁ። መልካም ንባብ!

@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
153 viewsMIKIYAS DANAIL, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:14:11 መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ -ሐምሌ 24 1962 ዓ.ም. ዕረፍታቸው ነበር፡፡
148 viewsMIKIYAS DANAIL, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:12:19
157 viewsMIKIYAS DANAIL, 15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 00:02:46
192 viewsMIKIYAS DANAIL, 21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 17:46:53
"ልዩ መንፈሳዊ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት"
የአ/አ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የሕንጻ እድሳት ኮሚቴ አስተባባሪነት በተዘጋጀው ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በአንጋፋ ኦርቶዶክሳውያን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች (አርቲስቶች) ወግ ÷ግጥም÷ ጭውውት ÷ መዝሙር ዝማሬ ÷ ድራማ ÷ መነባንብ ÷ የአንድ ሰው የመድረክ ተውኔት ÷ እና ሌሎችም ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡
በዕለቱ ግሩም ኤርምያስ፣አለማየሁ ታደሰ፣ተስፉ ብርሃኔ፣ ትዕግስት ግርማ፣ ሚሊዮን ብርሃኔ፣ መስከረም አበራ ፣ነቢዩ ኤርምያስ እና ሌሎችም ...... ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

ቀን፡- ነሐሴ 8/2014 ዓ/ም ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ:- 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ አዳራሽ
የመግቢያ ዋጋ 300 ብር ብቻ
ለበለጠ መረጃ 0911-117613 , 0913645364 ደውሉ፡፡
ኑ! የልብ መሻትዎን መንፈሳዊ ስራን በመደገፍ ያግኙ!!
211 viewsMIKIYAS DANAIL, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 21:38:30 ማስያስ

ዳግም ጥቆማ

#መቅድመ_ነገር

መጽሐፏን ያገኘኋት ከፌስ ቡክ ጥያቄና መልስ ፡ በሽልማት መልክ ነበር ። እንደ አጋጣሚ ሀዋሳ ነበርኩና በአንዲት በጓደኛዬ በኩል መጽሐፉን ተቀብዬ ለመጽሐፉ አዘጋጅ ልባዊ ምስጋናን በማቅረብ መጽሐፉን አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ አጠር ያለች ይዘታዊ ዳሰሳ (content review) ለማዘጋጀት ቃል ገብቼ ነበር ። ብዘገይም በቃሌ ተገኝቻለሁ ። ይኸው እነኋችሁ!!!

#የመጽሐፉ_ርዕስና_ዓላማ

ማስያስ ፦ በአረማይክ መሲሕ ፣ በዐረብኛው አልመሲሕ በግሪኩ ደግሞ ማስያስ እያልን የምንጠራውን ሥግው ቃል መድኃኔዓለምን ጥዑመ ስም የያዘ ነው ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት " ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ " ያለው ግዘፍ አካል ነስቶ ለአፍ የሚጥም ፣ ለጆሮ ደስ የሚያሰኝ ፣ ለአጋገር የሚመች ፣ ለዓይን የሚስብ ፣ ለንባብ በሚጋብዝ ምጥን ቃል " ማስያስ " በሚለው ስያሜ አግኝቼዋለሁ ።

በመጽሐፉ ሽፋን ገጽ ላይ ጸሐፊው ስለ መጽሐፉ ጠቅላይ ዓላማ (General Objective) " የኦርቶዶክሳዊው ነገረ መለኮት መቅድማዊ ነጥቦች " በማለት መሠረታዊ የሆኑ የነገረ መለኮት ጽንሠ ሃሳቦችን (Conceptual framework of Theology) ሊያስውቅ የሚችል መጽሐፍ እንደሆነ ለመግለጽ ሞክሯል ።

መምህር ብርሃኑ አድማስም ስለ በመጽሐፉ ኆኅት በተገብቶ ዲ/ን ሚኪያስ መጽሐፉን ማስያስ ያለበትን ምክንያት " ክርስቶስ የትንቢት ሁሉ ፍጻሜ ፣ የንባብ ሁሉ ትርጓሜ ፣ የምሳሌያትና የጥላዎች ሁሉ ጥላ አካል ፣ የስብከትና የትምህርት ሁሉ መዳረሻ የአገልግሎት ሁሉ ዓላማ ፣ የጉባኤያት ሁሉ ጉዳይ ፣ የምሥጢራት ሁሉ ማኅተም ፣ የሕይወት ሁሉ እስትንፋስ መሆኑን የሚያምኑ አገልጋዮች ተግባራቸው ሁልጊዜም ይህንኑ እርሱን በምእመናን ልቡና ለማሰደር የሚረዱ ትምህርቶችን ፣ ጽሑፎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ ነው ። ዲያቆን ሚኪያስም መጽሐፉን " ማስያስ " ያለበት ምክንያት ይኸው የአገልግሎታችን ሁሉ ማዕከል እና የቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ምሥጢር እርሱ መሆኑን ለማሳየት ይመስለኛል ። " በማለት የመጽሐፉን ወሳኝ ዓለማ (Critical Objective) ያብራራል ።

#የመጽሐፉ_ይዘት

ይህ በ327 ገጽ ፣ ከ40 በላይ ሀገርኛ ፣ ከ50 በላይ የባሕር ማዶ ማመሳከሪያ ዋቢ መጻሕፍት ፣ በ300 የኅዳግ ማስታወሻዎች(Foot notes) የተሰነደው " ማስያስ " የተሰኘው መጽሐፍ በሰባት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን

#ምዕራፍ_1 = ኦርቶዶክሳዊ ፍኖተ አእምሮ

- ሃይማኖትን (ክርስትና) የአእምሮ ሕመም (Mental Illness) አድርገው እምነት (Faith) እና አመክንዮ (Reason) በጽንፍ ተቃርኖ ውስጥ ያሉ አድርገው በስህተት ለሚጓዙት የስህተታቸውን ምንነትና የስህተቶቻቸውን መንስኤ ይገልጻል ። ውግንናውን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በማድረግ በማስረጃ ይሞግታል ።

- በነገረ መለኮት ትምህርትም ሰፊ ቦታ የሚሰጣቸውን ዕውቀት ፣ አእምሮ ጠባዐይ ፣ አእምሮ መንፈሳዊና ምስጢረ ሥላሴ የተሰኙ ወሳኝ ጉዳዮች ሲያብራራ በተጨማሪም የባሕርየ እግዚአብሔር (Essence of God) አይመረመሬነት በኢ- አውንታዊ ነገረ መለኮት (Negative Theology) የተቃኘውን የአበውና ሊቃውንት ትምህርት ያቀርባል ። እንደ ማጣፈጫ ጨው ከተጠቀሳቸውም መካካል
" በነገረ መለኮት ዕውቀታቸው የተመሰገኑ ሕንዳዊው ሊቀ ጳጳስ ጳውሎስ ማር ጎርጎርዮስ ስለ ልዑል እግዚአብሔር መጻፍ ሲጀምሩ እንዲህ ይላሉ " ስለ እግዚአብሔር ማንነት እንዳስተምር ብጠየቅ ፡ የማስታወሻ ወረቀቶቼን ይዤ ወጥቼ የትምህርቴን ርእስ ተናግሬ ለረዥም ሰዓት ዝም ብዬ ከቆየሁ በኋላ ስላዳመጣችሁኝ አመሠግናለሁ " ብዬ ከመናገርያ ቦታዬ እወርዳለሁ " በማለት ጥልቅ ነገርን ተናግረው ነበር ። " ገጽ 29

#ምዕራፍ_2 = ፍጥረት

- ከላይ በአሚነ እግዚአብሔር የተወጠነው ትምህርት በዚህ ምዕራፍ በአእምሮ ፍጥረተ ዓለም ይጸናል ። በትልቁ ዓለም የሚኖረው ትንሹ ዓለም (Microcosm)፣ ግሩምና ድንቅ የሆነው የሰው ልጅን የፍጥረት ሁሉ ዘውድ የሆነበትን ምክንያት ይዳስሳል ።

- በመቀጠልም በእግዚአብሔር አርአያና መልክ የተፈጠረው የሰው ልጅን ድቀትና ድኅነት በሰፊው ያስቃኛል ።

#ምዕራፍ_3 = የመገለጡ ጥላዎች በብሉይ ኪዳን

- "ሐዲስ ኪዳን ማለት የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ ነው " እንዲሉ ወንጌል ሳትሰራ ወንጌልን በጻፉ በብሉይ ኪዳን ወንጌላውያንና በዘመነ አበው ፣ በዘመነ መሣፍንት ፣ በዘመነ ነቢያት ፣ በዘመነ ነገስት " ታሪኮች " ማስያስ "ን እያሳየ ያስደንቀናል ።

- የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መካከለኞች ፣ የሰማያዊ ሙሽራ እናትና ጓደኛ ያስተዋውቀናል ። በተለይን እናቱ በነገረ ድኅነት (Soteriology) ለሰው ልጆች መዳን ስለ አላት ድርሻ ያሳውቀናል ።


#ምዕራፍ_4 = ሥጋዌ

- ቀደም ሲል የሙሽሮቹን እናትና ጓደኛ ያስተዋወቀን ፤ አሁን ደግሞ ሰማያዊው ሙሽራ ማስያስን ያስተዋውቀናል ። የሰርጉ ባለቤት(ማስያስ) ፣ የሰርጉን ዓይነት (ተዋሕዶ) ፣ የሰርጉን ዕለት፣ ሰዓትና ቦታ የሚገልጽ........የሰማያዊ የሰርግ ጥሪ ካርድ ይሰጠናል ።

#ምዕራፍ_5 = ነገረ ቤተ ክርስቲያን

- የሰርጉን የጥሪ ካርድ ይዘን ወደ ሰርግ ቤቱ(ቤተ ክርስቲያን) ይወስደናል ።

#ምዕራፍ_6 = ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ አምልኮ

- የሰርጎች ሁሉ ሰርግ በሆነው(ቅዳሴ) ድግስ ያሳትፈናል ።

#ምዕራፍ_7 = ሱታፌ አምላክ
-ከሰርጉ ማዕድ አሳትፎ ከሙሽራው ጋር ያዛምደናል ።


#የመጽሐፉ_ጠቀሜታ

" እስመ ረኪበ ቀጢናት በቀጢናት ፣ ወረኪበ ገዚፋት በገዚፋት ፤ ቀጢን ውእቱ ነገረ መለኮት ወየኀሥሥ ኅሊና ቀጢነ " እንዲሉ አበው ፣ መጽሐፉ ነገረ መለኮታዊ እንደመሆኑ የረቀቀና የመጠቀ ኅሊናን ይሻል። ነገር ግን የመጽሐፉ አዘጋጅ የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን የነገረ መለኮት ሐሳቦች አጉልቶ የታሪክና የሀሳብ ፍሰቱን በጠበቀ አጻጻፍ ውብና ሁሉም አንባቢ ሊረዳው በሚችልና ቀጢነ ኅሊናን በሚሰጥ መልኩ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው ።

ሚከዋ ብዕርህ ትለምልም!!!

መቅድሙ እንዲህ ከሆነ ውስጡ እንዴት ይሆን?

ዲ/ን ዘአማኑኤል ገዛኸኝ
2017/07/11
ሐዋሳ
226 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 21:38:27
202 viewsMIKIYAS DANAIL, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ