Get Mystery Box with random crypto!

#እጅግ_ድንቅ_የሆነ_አስተማሪ_የንስሐ_ሕይወት_ታሪክ:- ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶሪያ እና ቅዱስ ባስልዮስ | ዝክረ ብሒለ አበው

#እጅግ_ድንቅ_የሆነ_አስተማሪ_የንስሐ_ሕይወት_ታሪክ:-

ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶሪያ እና ቅዱስ ባስልዮስ ዘአንጾኪያ በተነሱበት ዘመን የምትኖር ልቧ በኀጢአት የሰከረ ለኀጢአት ተገዚ የሆነች ኀጢአቷን የምትጽፍ  አንዲት ሴት ነበረች::

ይቸ ሴት የተለያየ ኀጢአት የምሰራ ነበረች
ትዘሙታለች
ትዋሻለች
ታማለች
ትሰርቃለች
ትገድላለች
በአል ትሽራለች
ትሰክራለች
በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ልብሷ ኀጢአት ነበር:: ነገር ግን የምሰረውን ኀጢአቷን ሁሉ አየጻፈች ታስቀምጥ ነበር ከዕለታት አንድ ቀን የጻፈችው ኀጢአትቷን ብታየው ስንክሳር አክሎ ተመለከተችው::

ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚውሉ የቅዱሳን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነው የዚች ሴትም ኀጢአትም ይህን አክሎ ነበር:: እንዳየችው ደነገጠችና ኀጢአቷን ተሸክማ አባት ወደ አለበት ወደአንጾኪያ ሄደች::በዚያም አባ ባስልዮስን አገኘችው አባቴ በዚህ ያለው ኀጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችው አባ ባስልዮስም ይፋቅልሽ አላት:: ገልጣ ብታየው ሁሉ ተፍቆ አንዲት ኀጢአቷ ቀርታ አየቻት በጣም ከባድ ኀጢአት ነበረች ሊሰሩአት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች አባቴ ይችሳ አለችው አባ ባስልዮስም ይችን ኀጢአትሽን ማስተስረይ የሚችል ልጄ ቅዱስ ኤፍሬም ነው ሂደሽ ለእርሱ ንገሪው አላት::

አባ ባስልዮስ ይሄን ያላት ኀጢአቷን መፋቅ አቅቶት አይደለም የራሱ ክብር ከሚገለጥ የቅዱስ ኤፍሬም ክብር እንዲገለጥ ፈልጎ ነው ደግሞም ስትመላለስ ንስሐ እንዲሆናት ፈልጎ ነው እሷም አባ ባሰስልዮስ እንዳላት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶርያ ሄደች በባዶ እግሯ እንቅፋቱ እየመታት እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን ቀዳ እየጠመጠመች ተጉዛ ከቅዱስ ኤፍሬም ደረሰች አባቴ በዚህ ያለው ኀጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችው ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም ለአባቴ ለአባ ባስለዮስ እንጂ አላት::

ቅዱስ ኤፍሬም ኀጢአቷን መደምሰስ አቅቶት አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት ነው ስትመላለስ ኀጢአቷ እንዲቀልላት ነው ሂደሽ ለአባ ባስለዮስ ንገሪው እሱ ይደመስስልሻል አላት እሷም አግኝቸው አይሆንልኝም ብሎ ወደ አንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደ ቀድሞው በህይወት አታገኝውም ሙቶ ካህናት ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘውት ሲሄዱ ታገኝዋለሽ ሳትጠራሪ የተጻፈው ኀጢአትሽን ከአስከሬኑ ላይ ጣይው አላት እርሷም እሽ ብላ ሄደች::

የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቀያት ደረሰች ሙቶ ካህናት ፍትሀት እየፈቱት አየች የእግዚአብሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኀጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስከሬኑ ላይ ጣለችው ከአስከሬኑ ድምጽ ወጥቶ ኀጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል::

አምላኳን አመሰገነች ደስታ ዘመረች ከዚህ በሇላ ዓለምን ንቃ ገዳም ገብታ ኑራለች::

እንደ ዚች ሴት ኀጢአቱን የሚያስታውስ ማን ነው? ወደ ካህን ሂዶ ንስሐ የገባስ ስንቱ ነው? ስለኀጢአቱ በረሃ የተንከራተተ ማን ይሆን?

የዚችን ሴት መጨረሻ ያሳመረ የሁላችንም ጨረሻ ያሳምርልን ኀጢአቷን የደመሰሰ የሁላችንም ኀጢአት ይደምስስልን አምላኬ ሆይ ያለ ንስሐ አትጥራኝ!!!