Get Mystery Box with random crypto!

Daily Meditation

የቴሌግራም ቻናል አርማ behayluminilu — Daily Meditation D
የቴሌግራም ቻናል አርማ behayluminilu — Daily Meditation
የሰርጥ አድራሻ: @behayluminilu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

ሂድና በ "ሰሊሆም" መጠመቂያ ታጠብ አለው ትርጓሜውም "የተላከ"ማለት ነው። ስለዚ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ። ዬሀ 9:7
and said to him, "Go,wash in the pool of "SILOAM" (which means "sent"). so he went aweywashed and come back seeing. jon 9:7
ለማንኛዉምሀሳብአስታያየት
0965841672 👈
@yenemrchaeysus
👆👆👆👆

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-27 20:01:21 #ወዳጄ_ሆይ

መልክ ትዳር አይሆንም ፣ የተስተካከ ተክለ ሰውነት ቤትህን አያቆመውም ልብ በል ትዳር ማለት የህይወትን ጣዕም የምታውቅበት
የምትደጋገፍበት፣ በሳል የምትሆንበት፣ አባት የምትሆንበት፣ ከብቸኛነት ወተህ ሁለተኛ እናት የምታገኝበት፣የህይወትህ ማጣፈጫ የፈጣሪ ስጦታ ነው።

ወንድሜ ደስታን የምሰጥህ ሴት ከፈለክ
መልኳን ሳይሆን ከአስተሳሰቧ፣
አለባበሷን ሳይሆን ፈጣሪን የምትፈራ መሆንዋን ልብ ብለህ እይ በአሁኑ ስአት ፈጣሪዋን የምትፈራ ሴት ማግኘት መታደል ነውና ።
መልኳን ሳይሆን ለአንተ ያላትን አመለካከት አስብ ለዘላለም አብሮህ የሚኖርው ልቧ ላይ ያለው ላንተ ያላት ፍቅር እንጂ መልኳ አይደለም
ወንድሜ...ለህይወትህ ስኬትን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን ልብህ ያረፈባትን ሴት አግባ አይን ቀላዋጭ ነው ብዙ ያምርዋልና ልብህን አዳምጥ።

ፈጣሪዋን ፈሪ ትዳሯን አክባሪ ታዛዥ ሚስት ከፈለክ አተም ፈጣሪህን ፈሪ ሁን ፈጣሪን የሚፈራ ፍቅርን ያውቃልና
..............
ለሁላችንም ፈጣሪውን የሚፈራ የተባርከና የተቀደሰ ፍቅርና ትዳር ይስጠን።

@behayluminilu join
@behayluminilu join
376 viewsBa Hi, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:32:44 ጃማ የወጣቶች ህብረት

@behayluminilu
188 viewsBa Hi, edited  11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:11:19 Demonology

በተለያዩ ጊዚያት ከሰይጣን ሀይል ጋር በተያያዘ ብዙ የተለያዩ ምልከታዎች አሉ።
ምልከታዎችንም በሁለት ከፍለን እንያቸው ።
1ኛ, አንዳንዶች ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር በንፅፅር ያስቀምጡታል ። እግዚአብሔር ሲዘጋ ሰይጣን የሚከፍት እንዲሁም እግዚአብሔር ሲከፍት ሰይጣን የሚዘጋ ተቃራኒ ሀይል አድርገው ይመለከቱታል።

2ኛ, ሰይጣን በእግዚአብሔር ፣በፍጥረቱ እና በቤተክርስቲያን ላይ ያለውን ተቃርኖ እና ተቃውሞ ይዘነጉታል።

ሰይጣን ከእግዚአብሔር ጋር በንፅፅር የሚቀመጥ ሀይል አይደለም ። እግዚአብሔር የከፈተውን የሚዘጋ እንዲሁም የዘጋውን የሚከፍት ሀይል የለም ። እግዚአብሔር በልዩነት የሚታይ አምላክ እንጂ በንፅፅር የምናስቀምጠው ሀይል አይደለም ። ሰይጣንን ካነፃፀርንም የምናነፃፅረው ከፍጥረት ጋር ነው ። ለምሳሌ ከቅዱሳን መላዕክት ጋር ። በመሰረቱ ፉጡር እና ፈጣሪ ሊነፃፀሩ አይችሉም ።

በሌላ ጎኑ ደግሞ የሰይጣንንም ተንኮል መዘንጋት የለብንም ።
“ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰል እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ልቡና ተበላሽቶ ለክርስቶስ ካላችሁ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትወሰዱ እሠጋለሁ።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 (አዲሱ መ.ት)
ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው የሰይጣን ተንኮል እንዲሁ በቀላሉ ልናልፈው የሚገባ ገዳይ አይደለም ። ጳውሎስን ለስጋት የዳረገው ጉዳይ የሰይጣን በአማኞች ላይ ያለው ዕቅድ ነው ።

እንዲሁም ፦ “ይህንንም የምናደርገው ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤ የእርሱን ዕቅድ አንስተውምና።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 2፥11 (አዲሱ መ.ት)
የሰይጣን ዕቅድ ምን እንደሆነ ማወቅ መሰረታዊ ነገር ነው ። እርሱ ብቻ አይደለም ከሰይጣን ወጥመድም እራሳችንን ለመጠበቅ ነቅቶ መጠበቅ የግድ ነው ።
ስለ ሰይጣን እና አሰራሩ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ስፍራዎች ላይ ተፅፎ እናገኛለን ። በጣም የሚገርመው ደግሞ አሉታዊ ሆነው ከተጠቀሱት ከአንዳንድ ምግባሮች በላይ ስለ ሰይጣን መፃፉ ነው ። ይህ ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስ ችላ ያላለው ጉዳይ መሆኑንን እንረዳለን ።

ሰይጣን የክፋት ምንጭ ቢሆንም ማንኛውም የክፋት እንቅስቃሴ ሁሉ ከሰይጣን አይደለም ።
ክፋት ባደረግን ቁጥር ደግሞ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው እያልን ማላከክ የለብንም።
ሮሜ 7
¹⁶ ማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆነ፣ ሕጉ በጎ እንደሆነ እመሰክራለሁ፤
¹⁷ እንዲህ ከሆነ፣ ይህን የማደርገው እኔ ራሴ ሳልሆን፣ በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኀጢአት ነው።
¹⁸ በእኔ፣ ማለትም ኀጢአተኛ በሆነው ተፈጥሮዬ ውስጥ ምንም በጎ ነገር እንደማይኖር ዐውቃለሁ......

በመቀጠል ስለ ሰይጣን ውድቀት እና የውድቀት ምክንያት እንዲሁም ሰይጣንን እንዴት እንቃወመዋለን ?? እና መናፍስትን የማስወጣት የፀጋ ስጦታ አለ ወይ?? በሚሉ ሶስት ክፍል ሀሳቤን አቀርባለሁ ።
ይቀጥላል .......

@behayluminilu
@behayluminilu
591 viewsBa Hi, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 06:39:14 ​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━─━━ ⊱✿⊰ ━━━━━━──


➲ ፍቅር ዕውር ነው



አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ፡፡እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን የቆዳ በሽታ ያዛት፡፡ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች፡፡በቀን በአንደኛው ባልዋ ለጉብኝት ራቅ ወደላ ስፍራ ሄደ፡፡በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጠመውና እና ዓይኑን አጣ፡፡ሆኖም የጋብቻ ህይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ፡፡ግን ቀናት እያለፉ ውበቷን ደረጃ በደረጃ አጣች፡፡

ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳራቸው ሕይወት ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን በድንገት ሞተች፡፡ ድንገት መሞቷ ታላቅ ሀዘን አምጥቶለታል፡፡ሀዘን ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ፡፡በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች
አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? በእነዚህ ሁሉ ቀናት ሚስቱ ነበር የምትረዳው፡፡ ብለው ይወያዩ ነበር፡፡ሰውየውም

አይነስውር አይደለሁም ብሎ መለሰ፡፡ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነው፡፡ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እነዳልሆነ እንዲሰማት ነበር፡፡ስለዚህ እንደማላይ ነገርኳት፡፡እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች፡፡እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው ፡፡

አንዳንድ ጊዜ አውቀን አየተን ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዬች ስናልፋቸው ፣ በዙሪያችን ካሉ ሰዎችን ጋር ያለን መልካም ግንኙነት እንዲጠነክር ይረዳል፡፡



@behayluminilu
@behayluminilu
549 viewsBa Hi, 03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:38:58 “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”
— ሮሜ 8፥34
244 viewsBa Hi, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:45:28 ስንፍና ባንቺ አያምርም!

ወጣት ሆነሽ ካልተለወጥሽ መቼ ልትለወጪ ነው?አቅም ባለሽ ሰዓት ካልሰራሽ መቼ ልትሰሪ ነው? ካልዘራሽ እኮ አታጭጂም፤ ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ይሄን ወርቃማ ዕድሜዬን ተዓምር እሰራበታለው በይ

ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልጊው? ከራስሽ አልፈሽ የምትወጂያቸውን ሰዎች መቀየር አትፈልጊም? እርግጠኛ ነኝ ትፈልጊያለሽ! ስለዚህ ተነሽ! የምትችይውን ሁሉ አድርጊ! ቁጭ አትበይ! የማይጠቅምሽን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅሽም ንቂ ወዳጄ! ስንፍና ባንቺ አያምርም!

@behayluminilu
@behayluminilu
@behayluminilu
568 viewsBa Hi, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:01:18
ይህንን ምስል ላላመኑ ለምታውቋቸው ሰዎች ሁሉ በመላክ የወንጌልን በር ክፈቱ!!

መልካሙን ዜና እርሱም የጌታችንን የመድሃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ የፍቅሩን ስራ አብስሩላቸው!!



@behayluminilu
@behayluminilu
269 viewsBa Hi, edited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:24:33 የእግዚአብሔር ፍቅር

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
የአዲስ ኪዳን ትልቁ አፅንኦት አንተ ለእግዚአብሔር ያልህ ፍቅር ሳይሆን እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር ነው ።
አንተ ለእግዚአብሔር ያለህ ፍቅር አስፈላጊ አይደለም እያልኩ አደለም እኛ ለእርሱ ያለን ፍቅር ይዋዥቃል እርሱ ለእኛ ያለው ፍቅር ግን በፍፁም አይወድቅም
እግዚአብሔር እኛን ከሁኔታዎች ጋር ባልተገናኝ ፍቅር ነው የወደደን

“ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።”
— ኤፌሶን 3፥18-19
እግዚአብሔር ፍቅር ነው የእግዚአብሔር ፍቅር በግሪክ <አጋፔ> የምንለው ፍቅር ነው ።
ይህ አይነት ፍቅር ምክንያታዊ ያለሆነ ፍቅርን ያመለክታል /ያሳያል (indicated unconditional love)
የእግዚአብሔር ፍቅር ከመታወቅ የሚያልፍ ነው የፍቅሩን ልክ ለማወቅ የመለኮት ምስጢረ ሊገለጥለህ ያስፈልጋል የክርስቶስ የመስቀል ላይ ስራ ብቻውን እንኳን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ያሳያል

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
ፍቅር የመንፈሳዊ ነገር መለከያ/standard የላቀ የመንፈሳዊ ሕይወት ከፍታ ነው ።

ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝ ነገር ሁሉ የግድ ከፍቅር ጋር ይገኛል ምክንያቱም ፍቅር የእግዚአብሔር ባህሪ ስለሆነ ።

እግዚአብሔር ሲወደን ክእኛ ሁኔታ ባህሪ ጋር አደለም የወደደን ከእራሱ ሁኔታና ባህሪ ነው የወደደን ስለዚህ እግዚአብሔር እኛ ስናጠፋ አይጠላንም እግዚአብሔር ሲወደን በዘላለም ፍቅሩ ነው የወደደን

@behayluminilu
@behayluminilu
@behayluminilu
@behayluminilu
230 viewsBa Hi, 06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:59:40 መላ አለው

እንዴት እንደሚያሻግር መላ አለው ጌታ
በስራው ትክክል ታምራዊ አምላክ ነው
አልሰጋም ከንግዴ አልፈራም እኔ
እንዴት እንደሚያሳልፍ ያውቃል መደኔ

መላ አለው ለሁሉም መላለው
መላ አለው ለማኖር
መላ አለው ለማሻገር
መላ አለው ለመባረክ
መላ አለው እሱ
መላ አለው ጌታ

ግጥም ባሂ

@behayluminilu
@behayluminilu
452 viewsBa Hi, edited  04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:19:10 ለቻናሌ ቤተሰቦች የቀረበ ጥሪ

ሰላም የቻናሌ ቤተሰቦች በኔ የተጠቀማቹ ብዙ ያተረፋቹ በውጭም በውስጥም ያላቹ ያባቴ ልጆች ላግዝ ፈልጋለው ምትሉ ከ 100 ብር ጀምሮ የቻላችሁት በማድረግ አገልግሎቱን ከኔጋ አስቀጥሉት አግዝሀለው ምትሉ ደስ እያላቹ አድርጉ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ ስለሚል ተባረኩልኝ ላግዝ ፈልጋለው ምትሉ ከዚ ሰአት ጀምሮ ይቻላል ማገስ

ንግድ ባንክ በሀይሉ ምኒሉ
1000356029023

ህብረት ባንክ በሀይሉ ምኒሉ
309411848695018

ከጎኔ እንደምቶኑ አምናለው ስለ ትብብራቹ ጌታ ይባርካቹ

@yenemrchaeysus inbox
276 viewsBa Hi, edited  19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ