Get Mystery Box with random crypto!

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓ '. #ተመኒ '. ✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ ┗◛◛ | Ayto fikrsh

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አስራ_ሁለት ❲⓬❳
╰───── • ❊ • ─────╯

"""አንድ ቦታ ወሰዱኝ ግራ ገባኝ ቦታዉ የመቃብር ቦታ ነዉ ያአሏህ ቆይ ምን እየሆኑ ነዉ ብዬ ወደ አሊም ስዞር መልስ የለም ወደ ሰኢዲም ስዞር መልስ የለም አሊ ለሁለታችን ቦታዉን ጥሎ ሄደ እኔና ሰኢዲ ብቻ ቀረን ሰያም
<ይሄ ቀብር የማን እንደሆነ ታዉቃለህ
<<እሚገርመዉ እኔ የሆነ ቀብር ላይ እንዳለን እንጂ የማን ቀብር ላይ እንዳለ አላስተዋልኩም ነበር ግራ ገባኝ ወደ ሌላ አቅጣጫ ፊቴን ስዞር ኡስቷዛችን ከወራቶች በፊት ወደ አኼራ ሄደዉ ለመቅበር መጥተን ነበር እናም እንዴ ሰያ እዛ ጋርኮ የኡስቷዝ ሷሊ ቀብር ይታየኛል አልኩት እሱም
<አይ እኔ የምጠይቅህ የአሁን የቆምንበትን ብቻ ነዉ ብሎ ና በቃ ብሎ ወደ አንድ ጥላ ስር ወስዶኝ እራሱን ማስተካከል ጀመረ
"አንተ ብዙ የማታዉቀዉ ነገር ተፈጥሯል አንተ ለስንት ቀን ነዉ ሆስፒታል የተኛህዉ
<<ለአንድ ቀን ነዋ ከዛም ግን ቶሎ አልተነሳሁም
<አይደለም አንተ ሆስፒታል የተኛህዉ ለአስራ አንድ ወር ነበር
<<እንዴህ ሆኖ ቆይ ለምን
<ሃሚዬ ሁሉንም ሰዎች አዉፍ በላቸዉ
<<እያወራህ ያለህዉ ነገር አልገባኝም
<ተመኒም ወደ አኼራ ሄዳለች ለአንተ ያልተነገረህ እስክታገግም ተብሎ ነበር ያልተነገረህ እናም ሃሚ ተመኒም አንተ ከታመምክ ቡሀላ ሀኪም ቤት እየተመላለሰች ነበር ግን እርጉዝ ሆና ምግብም ፈሳሽ ነገርም እየወሰደች አልነበረም ቀን ከለሊት መልቀስ ነበር ስራዋ ከዛም ወሯ እየገፋ ሲመጣ አቅም አንሷት ከቤት መዉጣት አቃታት ሳሪና ሀናን እያስታመሟት እሷ ጋር ቆዮ ነገር ግን ተመኒ አስቸጋሪ ባህሪ ነበራት እሱም ምግብ በስርአት አለመብላቷ ነበር የመዉለጃ ቀኗ ደርሶ ግን ሆስፒታል ስትወሰድ ግን አቅም አንሷት ደም አነሷት ሂወቷ አለፈ ልጇን በሰላምተገላግላ
<<ሃኒ ይዛ የመጣችዉ የኔን ልጅ ነበርንዴ
<አዎ ቤቱንም አንድትሸጥ ያደረግነዉ እኔና አሊ ነን ህፃኗ ያለችዉ በአባቷና በእህቷ ቤት ነዉ
<<ቆይ እኔ ምን ህኜ ነዉ የዚህይ ያህል የታመምኩት
<ተመተህ ነበር ተቀጥቅጠህ
<<ቆይ እሺ ስነቃኮ እያስታወስኩ የነበረዉ የተላኩትን ኬክ ነበር እንዴት የዚህን ያህል ጊዜ ተኝቼ ማለቴ እንዴት ቆየዉ
<የተመታህበት ቦታ አደገኛ ነበር ሁላችንም መሞትህን ነበር ስንጠባበቅ የነበረዉ
<<እሺ አሁን ልጄ ጋር ዉሰደኝ በአሏህ ብዬ ሰያን ይዤዉ ወጣሁ እሱም ግን ምንም መልስ ሳይሰጠኝ ወደ አንድ ትልቅ የሀብታም ሰፈር ይዞኝ ገባ በሩንም አንኳኳና ወደ ዉስጥ ይዞኝ ገባ ሀኒ ስታየኝ ደስ አላህ ህፃኗን ይዛት እየተጫወተች ነበር ወደኔ መጥታ ህፃኗን ሰጠችኝ ባለፈዉምኮ ሁሉን ነገር ስላልገባህና ስላላወክ ነዉ ያልነገርኩህ ያልሰጠሁህ አፉዋን ብላኝ ህፃኗን ሰጠችኝ እናም ቤት ገብታ አንድ ወረቀት አምጥታ ሰጠችኝ እኔም ልከፍተዉ ስል አይ ለብቻህ አንብበዉ ተመኒ ናት ፅፋ የሰጠችኝ አሁን ህፃኗን ስጠኝና አንተ ወይ እዚ ወይ እዛኛዉ ቤት ስትለኝ አይ ቆይ እዛኛዉ ቤት ይሻለኛል ብዬ ወደ እናትና አባቴ ቤት ብያት ጥዬዉ ወጣሁና በደመነፍስ ቤት ደረስኩ ግን እስከዛሬ በአይኔ የአላየሁት መስዑድ የት ሂዶ ነዉ?

""ቤት ደርሼ ደብዳቤዉን ከፈትኩት የተመኒ ፅሁፍ መሆኑን በቶሎ ነበር የለየሁት አይ ተመኒ በጣምኮ የሚነበብና የሚወደድ ፅሁፍ ነዉ ያላት ብቻ ማንበብ ጀመርኩ
(የኔ ባል ሃሚ ስታነብ ተረጋግተህ መሆን አለበት እና ደሞ እኔን ከልብህ የምታፈቅረኝ ከሆነ አደራ በቀል የሚባል ነገር እንዳታስብ ተበቃዩ አንድ አሏህ ብቻ ነዉ ታዉቃለህ እዉነቱን ስትሰማ ከኔ መሞት በላይ እንደሚያሳምምህ አዉቃለሁ ሃሚዬ መረጋጋት እንዳለብህ ግን ደጋግሜ እነግርሀለዉ የኔ ልዩ ባል የኔ ትሁትና ሃሚዬ መፃፍ እራሱ እየከበደኝ ነዉ የኔ ፍቅር......

#የመጨረሻው_ክፍል_⓭_ይቀጥላል
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አስራ_ሶስት ❲⓭❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╔═════ೋೋ═════╗
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╚═════ೋೋ═════╝