Get Mystery Box with random crypto!

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓ '. #ተመኒ '. ✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ ┗◛◛ | Ayto fikrsh

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አስራ_አንድ ❲⓫❳
╰───── • ❊ • ─────╯

"""አንዲት ሴት እንደሸጠችለት ነግሮኝ በሩን ዘጋዉ እንዴ በቃ ተመኒ ከነ ልጄ በአንድ ቀን ካደችኝ ማለት ነዉ ቆይ ያያለችኝ ፍቅረኛዋ ሲመጣ ወደሱ ሄዳ ነዋ እያልኩ እያሰብኩ በሰመመን ወደ እናቴ ቤት ተጓዝኩኝ ቤት ደርሼም ከማንም ከምንም ጋር ሳላወራ ሳምንታት አልፈዉ ወራቶች ተተኩ ከማንም ጋር መነጋገር አቆምኩኝ አንድ ቀን ታድያ ጊቢ መናፈሻ ዉስጥ ተቀምጬ ቁረአን እየቀራሁ ሳለ ላይ የጊቢዉ በር ተንኳኳ ማነዉ ብዬ ዘበኛዉን ሳየዉ የለም ተነስቼ በሩን ከፈትኩት ነገር ግን ለወራት ስፈልጋት የነበረችዉ ሀናን ናት ደነገጥኩ ግራ ገባኝ አብራት አንዲት በጣም ህፃን ልጅ አቅፋት ነበር ደንግጬ አንቄ ሳምኳትና አስገባዋት ሀኒ ግን ለምንድ ነዉ ለአንድ ቀን መጠበቅ ያቃታቹ እኔኮ ኬኩን በማግስቱ ለማምጣትም ቢሆን እችል ነበር ግን ደሞ ቤተሰቦቼ አለቀቁኝም ብዬ ስቀባጥር ሀናን ማልቀስ ጀመረች ግራ ገባኝ እሺ ተመኒ ስልክም ቀይራ ከሆነ ስጪኝና ልሞክርላት ብዬ ሳያት አሁንም ታለቅሳለች ግራ ገባኝና ሀኒ ምነዉ የተፈጠረ ችግር አለንዴ አልኳት አይ የለም ብላኝ እኔም ከሰሞኑ አባቴ ወስዶኝ ነበር የተመለስኩት ከሀገር ዉጪ ነበርኩ
<<ማሻአላህ ደስ ይላል ግን ተመኒስ
<ማለት
<<ምን ማለት ያስፈልገዋል አንድ ቀን ሀኪም ቤት ብቆይ እሷ መጥታም አልጠየቀችኝም ደሞም እርጉዝ ነኝ ብላኝ ሁሉ ነበር አሁን ግን ሳስበዉ ወደመጀሪያ ፍቅረኛዋ ተመልሳ ነዉ መሰለኝ
<ሃሚ እባክህ አታሳምመኝ
<<ሃኒዬ ቤቱን እራሱኮ ሸጣዋለች
<ቤቱንኮ እኔ ነኝ የሸጥኩት እሷኮ ብላ ማልቀስ ጀመረች
<<ተይዉ በቃ ሲገባት ትመለሳለች ይልቁኑስ ይቺ ልጅ የማናት ከመንገድ አጊንተሽ ነዉዴ
<አይደለም ሃሚዬ እባክህ አታሳምመኝ ብላኝ ህፃኗን አቅፋት ይዛት ሄደች ልከተላት ግን አልፈለኩም ምክንያቱም እንዴት በአንዴ ይክዱኛል ብዬ እየተበሳጨዉ ነበር ብቻ ብዙም ሳልቆይ አሁንም በሩ ተንኳኳ ተነስቼ በሩን ከፈትኩት ሀአሊና ሰኢዲ ናቸዉ ምንም ሳልላቸዉ ከፍቼ ወደ ዉስጥ ልገባ ስል አሊ
<ምን እየሰራህ ነበር
<<ቁረአን እየቀራሁ ነበር
<ማሻአላህ ነዉ
<<ተባረከላህ አሁን ገብቼ ልተኛ ነበር በል ደና ሁኑ ብዬ ሰኢዲንም ሰላም ሳልል ወደ ቤት ልመለስ ስል ሰኢድ ቀደም ብሎ ሃኒስ አለኝ
<<ከከሀዲ እህቷ ጋር አብራ መጥታ ምንም ሳትናገረኝ ሄደች አልኩት ሰኢዲም ተናዶ ከአሊ ጋር ወደ ዉጪ ይዘዉኝ ወጡና ወደ አንድ ቦታ ወሰዱኝ ግራ ገባኝ ቦታዉ የመቃብር ቦታ ነዉ ያአሏህ ቆይ ምን እየሆኑ ነዉ ብዬ ወደ አሊም ስዞር መልስ የለም ወደ ሰኢዲም ስዞር መልስ የለም.....

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_አስራ_ሁለት ❲⓬❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╔═════ೋೋ═════╗
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╚═════ೋೋ═════╝
.↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴.