Get Mystery Box with random crypto!

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓ '. #ተመኒ '. ✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ ┗◛◛ | Ayto fikrsh

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ስምንት ❲➇❳
╰───── • ❊ • ─────╯

""ይሄ ማለት ደሞ አፈቅርሻለሁ ማለት ነዉ ግን በጣም ይቅርታ አንቺ ላትወጂኝ ትችያለሽ እኔ ግን ወድሻለሁ
<ሃሚዬ
<<ወዬ
<እኔ ማለትም አንተን በጭራሽ እወደዋለዉ ብዬ አስቤ አላዉቅም ነበር አንተ ከምታፈቅረኝ በላይ ነዉ ያፈቀርኩህ ቆይ እሺ እኔ ምን ላድርግ
<< ተመኒዬ በቃ እንጋባ አብረን እንኑር
<እንዴ ሃሚዬ አንተም
<<ምነዉ ምን አደረኩ
<ሀኒን ለማን ትቼ ነዉ እኔ የራሴን ሂወት የምኖረዉ
<<የኔ ዉድ እሷንማ መቼም አንተዋትም እኔ በበኩሌ አንቺ እራሱ ለብቻዋ ትሁን ብትይኝ አልቀበልሽም ሁሌም ከኛ ጋር ነዉ የምትኖረዉ
<የኔ ባል ማለት እችላለሁ
<<ሚስትየዉ ማለት ከቻልኩና ከፈቀድሽልኝ
<እረ በደንብ ትችላለህ ግን አንድ ነገር መቅደም አለበት
<<ምን
<ሀኒን ለማሳከም ወደ ዉጪ ልሄድ ነዉ እናም ከእዛ እስክመለስ ትጠብቀኛለህ
<<አዎ እጠብቅሻለሁ
<እሺ ከዛም ኢንሻአሏህ ስመለስ ከአባቢ ጋር ተመካክረን ኒካህ እናስራለን እናም በቃ አብረን እንኖራለን
<<እንዴ ሰርጌስ
<ሰርግህን ማን ይመጣል ቆይ እኛኮ ብዙ ሰዉ አናዉቅም ከዚ ስትወስደኝኮ በሰርግ ከሆነ መደገስ አለብን እኔ ደሞ እናቴ የለችም በኒካህ ቀለል አድርገን መኖር ብንጀምር ይሻለናል
<<አይሆንም ቆይ እሺ አባትሽ በሰርግ ነዉ የምትወስዳት ብለዉ ቀዉጢ ቢያረጉትስ
<አባቢ እንደዛ አይልም ግን በቃ እሺ ጊዜዉ ሲደርስ እናስብበታለን
<<ሚስትየዉ በዚ ንግግሬ አላዘንሽብኝም አይደል ግን በቃ ለኔ ፍቅርም ሴትን በተቃራኒ ማሰብም ለመጀመሪያ ጊዜዬ ስለሆነ ብኝ ነዉ እሚገርምሽ እንዴት እራሱ መጠየቅ እንዳለብኝ አላዉቅም አንቺንም በድፍረት ያወራሁሽ ስለምቀርብሽ ነዉ ብያት ከተመኒ ጋር አንዳንድ ነገሮችን አዉርተን ሀኒን ይዛ እስከምትሄድ ድረስ እነሱ ቤት ቆይቼ ተመለስኩ የምር ገና ከመሄዷ ናፍቆቷ ሊገለኝ ነዉ እሷም ደርሳ ደወለችልኝ በቃ ሁሌም ማታ ማታ ትደዉልልኝና በቪዲዮ ኮል እናወራለን ለአሊ ሁሉንም ነገር ነግሬዉ ከኡሚ ጋር ተማክረዉ አባቴን አሳምነዉ ጨርሰዋል አዎ አሁን ላገባ ስለሆነ አባቴን ምንም ቢጎዳኝም አክብሬዉ ማዉራት ጀምሬአለዉ አንድ ቀን እሱም ተፀፅቶ እነ ሰኢዲን ይቅርታ እንደሚጠይቃቸዉ ዉስጤ ያምናል ወንድሜ ደሞ ለዳእዋ ሊወጣ ሁለት ቀን ብቻ ነዉ ከኛ ጋር የሚያሳልፈዉ በነገራችን ላይ የሆነ ቀን በጥፊ የመታኝ ወንድሜ ስሙ መስዑድ ይባላል መሱ ብቻ ነዉ የምንለዉ ቲኒሽ ስሙ አዛ ስለሚያረገኝ ነዉ መሱ ብቻ የምንለዉ እሱ ነዉ ዳእዋ የሚወጣዉ ሲመስለኝ ለአራት ወር ነዉ መሰለኝ እሱ ከቤተሰባችን ድብቅ ነገር ነዉ ነገሩ ሁሉ ከአባቴ ጋር ነዉ የሚገጥመዉ እሱን ሸኝ የተባልኩት ደሞ እኔዉ ነኝ ሰኢድን ጠርቼዉ እስከ መናህሪያ ሸኘዉትና ለሰኢድ ከሰሞኑ ተፈጥሮ ያልነገርኩትን ነገሮች በሙሉ ነገርኩት እሱም በጣም ደስ አለዉ ግን ደሞ ፊቱ ብዙም የደስታ ምልክት አይታይበትም ምንም ሳልለዉ ዝም ብዬዉ መጓዝ ጀመርኩ
<ሃሚ
<<ወዬ ወንድሜ
<ታዉቃለህ አንተ ማለት ለቤታችን ባዳም ጓደኛም የአማቼ ወንድምም አይደለህም
<< እ እሱንማ አዉቃለሁ እኔ ማለት ለአንተም ለኡሚም ለሳሪም እኔ ማለት ብዬ ሰኢድን ሰፍ አደረኩት እሱም በምን አወክ አለኝ እኔም ሃሚ መሆኔንኮ መታወቂያ ላይ ነዉ ያየሁት እሱንም የትምርት ቤት መታወቂያ
<ቀልደህ ሞተሀል ለዚ ነዉ ከማወራዉ ያቋረጥከኝ
<<እህ ዜና ይመስልኮ አስረዘምከዉ እኔ ምለዉ ቆይ እኔ ሳልሰማ ዜና ዘገባ መስራት ጀመርክንዴ ስለዉ ሰኢድ ተናዶ በጥፊ ደረገመብኝና አቀፈኝ
<ሃሚዬ ለምን የዛሬን እንኳን አትሰማኝም
<<እሺ በቃ ወንድሜ እሰማሀለዉ አናግረኝ ስለአናደድኩህ በጣም ይቅርታ ብዬዉ የመታኝን ቦታ እያሻሸዉ ማዳመጥ ጀመርኩ
<ታዉቃለህ አንተ ማለት ለቤታችን ባዳም ጓደኛም የአማቼ ወንድምም አይደለህም አንተ ማለት ለኔ ትክክለኛ ወንድሜ ነህ ታዉቃለህ አንድም ቀን ከሳሪ ነጥዬ አይቼህ አላዉቅም ብሎ መንሰቅሰቅ ጀመረ
<<እኔ ስለምን እንደሚያወራ ስላልገባኝ የሆነ ጥግ ወስጄዉ አብረን ተቀመጥንና አወራዉ ጀመር እስቲ ሰያ የተፈጠረዉን አንድ በአንድ ንገረኝ ኡሚ ታክማ ተመለሰች አይደል እሱን አዉቃለሁ ግን ሌላ የተፈጠረ ነገር ካለ ንገረኝ
<ኡሚ በሰላም ታክማ ተመልሳለች ግን ደሞ የታከመችዉ አንተ በሰጠህኝ ገንዘብ አይደለም
<<እና
<አባትህ ናቸዉ ያሳከሟት ሲቀጥል ደሞ ትላንትና ኡሚ እግር ስር ተደፍተዉ ይቅርታ ሲጠይቋት ነበር
<<እሺ ከዛንስ
<ከዛንማ ለአንተ እንዳልነግርህ አስጠንቅቀዉኝ ነበር ግን ደሞ አንተ በኛ የተነሳ አባትህን እየጠላህ ነበር እኔ ደሞ ጥላቻቹ እንዳይኖር ከበፊትም ስነግርህ ነበር
<<የአባቴ ስራ ቢያስገርመኝም ግን ሰያ ከድሮም ከአባቴ ቀልብ እንዳልገባ ይነግረኝ ነበር ብቻ አስደናቂ ነገር በመስማቴ ደስ አለኝ ብቻ ፈዝዤ ሰኢድን ምንም ሳልለዉ ስቀር ሌላም አለ አለኝ ምን አልኩት
<አባትህ የገዙልን ቤት አለ ነገ እዛ እንገባለን ዛሬ እቃ ገዛዝተዉ እያስተካከሉ ነዉ
<<ቆይ ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔ የት ነበርኩ ወንድሜ
<አንተኮ ገንዘቡን ሰተህን ከኛ ቤት ከጠፋህ ሁለት ወር ሆነህ ኡሚ ታክማ የመጣች ጊዜ እራሱ መጣህናኮ በቶሎ ነዉ የወጣህዉ አንተ እኛን የተዉከን ነበር የመሰለን ግን ደሞ አሁን ምክንያትህን ስትነግረኝ ነዉ ወንድሜ ስለሆንክ ያመንኩህ ባዳ ቢሆን አላምንም ነበር
<<ሰያ አፉ በለኝ ግን ተመኒ ከኔ አትራቅ ብላ ነበር የያዘችኝ ቤት እራሱ ብዙም አልመጣም ነበር ብቻ ደስ ይላል እና አባቴ ልብ ገዛ ማለት ነዉ
<አይ ከአንተ ጋር ስላልተግባቡ እንጂኮ እሳቸዉ ክፉ ሆነዉ አይደለም ይልቁኑ ገንዘብህን በፈለከዉ ሰአት ናና ዉሰድ
<<አይ እሱ ገንዘብኮ የኔም አልነበረም ተመኒ ናት የሰጠችኝ ስለዚ ዉስጤ ለእናንተ ብሎ ስለነየተ መቼም አለቀበልህም ይልቁኑ ለሳሪ ንግድ እንድትጀምር አሪፍ ሱቅ ክፈትላት ኡሚንም ደሞ ምንም ስራ እንዳትሰራ ሰራተኛም ቅጠርላት ሲቀጥል ደሞ ሳሪም አንተም ትምርት ጀምሩ ሳሪ ያቆመችዉን የግል ትምርት ትቀጥል
<ወንድሜ
<<ወዬ
<አንድም የቀረኝ ነገር ነበር
<<አብሽር ንገረኝ ግን ቶሎ በል
<ሳሪኮ
<<ሳሪኮ ብሎ ሳይጨርስ ተመኒ ደወለችልኝ እሚገርማቹ የሀናንን ስልክ አልመለስኩም እስከ አሁን እሷን ማዉራት ስጀምር ሰያም የሆነ ስልክ ደዉሎ እያወራ ሄደ እኔ ከተመኒ ጋር እያወራሁኝ በቀጥታ ቤቴ ገባሁ የነተመኒንም ቤት አልፎ አልፎ እጎበኘዋለሁ ዛሬ ግን ስላልሄድኩ ተመኒን ማታ አወራሻለሁ ብዬ ወደ ግቢ ገባሁ አባቴ ዉጪ ላይ ተቀምጦ የለመደዉን ለከፋ ለከፈኝ እንደበፊቱ የምናገረዉ መስሎት ነበር
<ጎሮምሳዉ አልበዛም
<<አባዬ አፉ በለኝ ብዬ ወደሱ ሄጄ ጉልበቱን ሳምኩት
<ደነገጠ ምነዉ ምን ተገኘ
<<ምንመ አልተገኘም ግን አባቴ ሆነህ የሚገባህን ክብር መስጠት ነበረብኝ
<አይ አብሽር ልጄ አትጨነቅ ይሄኮ የሚስተካከል ባህሪህ እንደሆነም አዉቃለሁ ችግሩም የኔ ነበር የአንተ አይደለም ይሉቁኑስ አንተዉ አፉ በለኝ የኔ ልጅ ብሎ ተንሰቅስቆ አለቀሰብኝ ያረቢ አባቴ ለመጀመሪያ ግዜ አልቅሶ አስለቀሰኝ ብቻ ፍቅራችን ተመለሰ እረ ተጀመረ ማለት ሳይኖርብኝ አይቀርም ምክንያቱም እኔ በብዛት ያሳደጉኝ የነሰያ እናትና አባት ናቸዉ ብቻ አልሀምዱሊላህ።