Get Mystery Box with random crypto!

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓ '. #ተመኒ '. ✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ ┗◛◛ | Ayto fikrsh

┏◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚◚┓
". #ተመኒ ".
✎ፀሐፊ፦ በፎዚያ
┗◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛◛┛

╔─━━━━━━░★░━━━━━━─╗
. በ @Ayto_fkrshe የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝


╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ሰባት ❲➆❳
╰───── • ❊ • ─────╯

""ወንድም ነበረኝ እሱም የለም ነበር እናም ሳሪና አጎቴ ብቻ ነበር የቀሩት ነገር ግን ሁሉንም ነገር አጎቴ ሰበብ ሆኖ አበለሻሸዉ
<እንዴት ሃሚ ማለት ምን ተፈጠረ?
<<አጎቴ ሳሪን ካለ ርህራሄ ደፈራት አጎቴ
<ምን እንዴት ቆይ የሚከላከልላት ሰዉ አልነበረም
<<አዎ እሷ ስትታገለዉ በጣም መቷት ስለነበር እራሷን ስታም ነበር እናም እሱ ከቤት ጠፋ ሳሪ ግን እራሷን አላወቀችም ነበር እኔና አሊ ተገናኝተን ወደ ቤት አብረን ነበር የገባነዉ እናም አሊ እንተደፈረች ሲያዉቅ እራሱን ስቶ ወደቀ እሷንም እሱንም ጮኬ ሰዉ በመጥራት ወደ ሀኪም ቤት ሄድኩኝ ሳሪ ከብዙ ሰአታት ቡሀላ ነቃች መደፈሯንም ስታዉቅ በጣም እራሷን ልታጠፋ እየሞከረች በብዙ ጥበቃ ነበር ያልተጎዳቸዉ ወንድሜ አሊ ግን ቢነቃም ለወራት ያህል አያወራም ነበር ድንጋጤዉና ሲወድቅ የተመታበት ቦታ ጎድቶት ነበር እናም በዚ የተነሳ ነበር ሳሪን አባቴ ከቤት አባረራት ሳሪ ደሞ አሊ ሰርቶ በሚያገኘዉ ገንዘብ ነበር ቤተሰቦቿን የምትረዳዉ ሳሪ ወደ ቤት ስትመለስ ግን በጣም ተቸገሩ እኔም ለተወሰነ ጊዜ ወንድሜን ሳስታምም ቆይቼ ወደነ ሰኢዲ ጋር ስሄድ ሳሪ ቤት አልነበረችም ሁሉም ተክዘዉ ያዩኛል ወንድሟ ሰኢድን ጠርቼ ስጠይቀዉ ሳሪ የቡና ቤት ስራ ጀምራ ነበር በጣም ነበር የደነገጥኩት አዲስ አበባን በጣም ዞርኩኝ ሳሪን ብዙ ቦታ ፈለኳት ግን አላገኘዋትም እናም ከአንድ ጭፈራ ቤት በጥቆማ ጥቆማ ስሄድ ግን ሳሪን አንድ ትልቅ ሰዉዬ ይነካካትና ይስማት ነበር እሷም አቀርቅራ ምንም አትለዉም አይቼ መታገስ ሲከብደኝ ወንድሜ ለመንካት እንኳን የሚሳሳላትን ሳሪን ሰዉ በሀራም ሲነካት ሳይ መታገሱ ከበደኝ ሄጄ ሰዉየዉን መትቼ ከዛ ቤት አሶጥቼ ዳግመኛ ከወጣች እንደምመታት ና እንደምጎዳት ነግሬአት ወደ ቤት አድርሼአት ወደ አባቴ ቤት ተመለስኩ እሱንም ገንዘብ ለነሱ እንደሚያስፈልግ ነግሬዉ ጠየኩት እሱ ግን ገንዘቡ ባንክ እያጨናነቀ ለኔ የለኝም ስራ ላይ አዉዬዋለዉ አለኝ ሳሪ ደሞ በድጋሚ ወደዛ ሂወት ልትመለስ ነዉ በጣም ሲጨንቀኝ የአባቴን ጓደኞች ከሳሪ አባት ጋር የሰሩትን ሰዎች ጠየኳቸዉ እነሱም እና ምን አገባን ለነሱ ቤተሰብ ብለዉ አሾፉብኝ ወንድሜም እሪሱን አዉቆ ማዉራት ስለጀመረ ለሱ ነግሬ አማከርኩት እሱ ሽባ መሆኑ ተሰምቶት እማያዉቀዉ ግን የዛን ቀን ቅስሙ ተሰበረ ኡሚም ተጨነቀች አባቴም ገንዘብ ለእናንተ አልሰጥም ከሰጠዋቹ ለሱ ልትረዱ ነዉ ብሎን ከለከለን።
"""አንድ ቀን ግን ከእንቅልፌ ተነስቼ ወደ ትምርት ለመሄድ ተስተካክዬ ልወጣ በሩን ስከፍት ወንድሜ ደጅ ላይ እየተንፏቀቀ በሩን መክፈት ሲያቅተዉ አየሁ የዉጪዉን በር ለመክፈት እየታገለ ነበር እሱን ተሸክሜ አስገብቼዉ ወደ ዉጪ ወጣሁ ስራ ስሞክር ሁሉም አያምኑኝም እናም የግዴታዬን ወደ ስርቆት ገባሀ አዉቃለሁ መስረቅ ጥሩ አይደለም ግን ምን ላድርግ ሳሪ እህቴ ሆና የሀራም ስራ ላይ ገባች ሰኢድ ወንድሜ ሆኖ ፍርፋሪ ይለምን ጀመር ኡሚ ደሞ ከአልጋዋ መነሳት አቅቷት ታለቅሳለች ታዉቂያለሽ ተመኒ ገንዘቡን ወስጄ ስሰጣቸዉ የተሰማቸዉ ደስታ ምን ያህል እንደሆነ ወንድሜም አሁን በበሽታዉ አያዝንም ስለሁሉም ግን አንቺን ማመስገን እፈልጋለሁ ብዬ ወደ ተመኒ ስዞር ተመኒ አቅፋኝ ማልቀስ ጀመረች ግራ ተጋባሁ በኔ ታሪክ እሷ እንደዚ መሆኗ አስገረመኝ ለካ ለሰዉ የሚያዝንም ሰዉ አለ አልኩ በልቤ
<<በይ አትነፋረቂ ብዬ ሳቄን ስለቀዉ እሷ ለቃኝ ፈገግ ማለት ጀመረች በቃ ከተመኒ ጋር በጣም ተቀራረብን አንዳንዴ ደሞ ሀናንን እኔ እጠብቃታለሁ ተመኒ ደሞ ስራዋን ሰርታ ትመጣለች ቀስ እያለ እኔ ከተመኒ ፍቅር ያዘኝ ግን ደሞ ምን እንደማረግ ግራ ተጋብቼ ወደ ወንድሜ ጋር ሄድኩኝ
<<አሊ አሰላም ከለይኩም ወንድሜ
<ወአሌይኩም ወሰላም ወረህመቱላህ ወበረካቱሁ ጎሮምሳዬ ብሎ ግንባሬን ሳመኝና ከእግሩ ስር ተቀመጥኩ ምን ሆነህ ነዉ የተጨነክ ትመስላለህ
<<ወንድሜ ፍቅር ያዘኝ መሰለኝ
<ማሻአላህ እና ልትዘወጅ ነዋ ብሎ ሳቀብኝ
<<አዎ አስታወስካት አንድ ቀን አምጥቻት ነበር
<ኦዉ አዎ አወኳት ለነሳሪ እናት መታከሚያ የሰጠችልኝን ነዋ እረ ማሻአላህ ነዉእና ምን አሰብክ
<<ምን እንደማረግማ አንተዉ ንገረኝ እንጂ እኔ ምን አዉቃለሁ
<እሺ የኔ ጎሮምሳ በቀጥታ እንደምቶዳት ነግረሀት ኒካህ እሰሩ እሷ ከወደደችህ
<<እሺ ግን ዛሬ የግድ ልነግራት ይገባል ብዬ ተነስቼ ወደነ ተመኒ ቤት ሄድኩኝ ተመኒም ሀናንን ለህክምና ለመዉሰድ እየተዘጋጀች ነበር ከምን እንደምጀምርላት ግራ ገብቶኝ ሀናን ደክሟት እስክትተኛ ጠብቄ ተመኒን አስቀምጬ ላወራት መዘጋጀት ጀመርኩ
<<ተመኒ
<ወዬ ሃሚዬ
<<የሆነ ነገር ልነግርሽ ነበር አትቀየሚኝም
<አዎ ንገረኝ ምንድ ነዉ
<<ተመኒዬ
<ወዬ ንገረኝ እየጠበኩህኮ ነዉ
<<እሺ በቃ እነግርሻለሁ ይወልሽ ምን መሰለሽ ተመኒ ታዉቂያለሽ በአንቺ ልብ ዉስጥ ምናልባትም የሆነ ሰዉ ተቀምጦ ሊሆኖ ይችላል ግን ደሞ እኔ በጣም ነዉ እየናፈቅሽኝ ያለሽዉ ስላንቺ በማሰብ ነዉ ጊዜዬን የማሳልፈዉ ስላንቺ እሩቅ ማለም ጀምሬአለዉ ይሄ ማለት ደሞ አፈቅርሻለሁ ማለት ነዉ ግን በጣም ይቅርታ አንቺ ላትወጂኝ ትችያለሽ እኔ ግን ወድሻለሁ
<ሃሚዬ
<<ወዬ
<እኔ ማለትም አንተን በጭራሽ.....

⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╭───── • ❊ • ─────╮
#ክፍል_ስምንት ❲➇❳ ይቀጥላል
╰───── • ❊ • ─────╯

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╔═════ೋೋ═════╗
@Ayto_fkrshe
@Ayto_fkrshe
╚═════ೋೋ═════╝