Get Mystery Box with random crypto!

Assosa online

የቴሌግራም ቻናል አርማ asosaonline — Assosa online A
የቴሌግራም ቻናል አርማ asosaonline — Assosa online
የሰርጥ አድራሻ: @asosaonline
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 802
የሰርጥ መግለጫ

እውነተኛ ታማኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን እናደርሳለን፡፡
ቻናሉን ሼር ኢንቫይት እና ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ::

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-05 20:25:37 የጋራ ግብረ ኃይሉ ማሳሰቢያ ሰጠ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ሰሞኑን በሀገሪቱ በታላቅ ድምቀት በተከበሩ የአድዋ ድል በዓልን እና በዛሬው ዕለት ተከብሮ በዋለው የካራማራ ድል በዓል ላይ በመገኘት በሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና በህዝብ መካከል ግጭት ለመቀስቀስ ሞክረዋል አለ።

ይህን ያለው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው።

ግብረኃይሉ ፥ " ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ሌት ተቀን የሚጠብቁ የፀጥታ አካላትን ክብር አስፀያፊ ስድቦችን በመሳደብ ደፍረዋል " ብሏል።

ከፀጥታ ኃይሎች ጋር አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ለመግባት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም ሲል ገልጿል።

ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎች ሁሉንም ትንኮሳዎች በትግስት በማለፍ በዓላቱ በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ግብረ ኃይሉ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖች እና ግለሰቦች የሚፈልጉትን በግልፅ ህግና ስርዓት ተከትለው ማድረግና ሐሳባቸውን በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተፈቀደላቸው ስፍራ ማራመድና መፈፀም ሲችሉ ብሄርን ከብሄር፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት ጋር ለማጋጨት ስራዬ ብለው ሌት ተቀን በህቡዕ እና በግልጽ ጭምር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል።

እነዚህ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ግብረ-ኃይሉ አሳስቧል።

ማንም ከህግ በላይ ስላልሆነ ህግ ጥሰን ድርጊታችንን እንቀጥላለን የሚሉ ከሆነ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ እንዲሁም በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው የጋራ ግብረኃይሉ አስጠንቅቋል።

የጋራ ግብረ ኃይሉ በመግለጫው ላይ ውስን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ያላቸውን በስም አልገለፀም።

@asosaonline
422 views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 14:00:22 #Update

" ፕሬዜዳንቱ እስክንድር ነጋ ብቻ ሲለቀቁ ሌሎቹ በሙሉ ለእስር ተዳርገዋል " - ባልደራስ ፓርቲ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከ25 በላይ አባላቱ እንደታሰሩ አስታወቀ።

ይህን ያሳወቀው ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ነው።

ዛሬ የካቲት 26 የሚከበረውን የ " ካራማራ የድል " በዓል ለማክበር በ " ድላችን ሀውልት " የተገኘው የባልደራስ ቡድን ወደ አደባባዩ እንዳይገባ ከተደረገ በኋላ፣ የቡድኑ አባላት በሙሉ ወደ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል ሲል አመልክቷል።

ባልደራስ ፓርቲ ፤ ፕሬዘደንቱ እስክንድር ነጋ ብቻ ሲለቀቁ ሌሎቹ በሙሉ ለእስር ተዳርገዋል ሲል አሳውቋል።

አባላቱ ምንም አይነት የህግ ጥሰት ሳይፈጽሙ፣ ከህግ ውጭ መታሰራቸውን የገለፀው ባልደራስ አጠቃላይ ታሰሩብኝ ያላቸውን አባላት ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከእነዚህ መካከል የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ስንታየሁ ቸኮል ፣ አስቴር ስዩም ፣ አስካል ደምሌ ይገኙበታል።


@asosaonline
410 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 12:11:51 አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ተይዘው ተወሰዱ።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዘዳንቱን አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አባላት እና ደጋፊዎቹን፤ ፓሊስ በ3 መኪና ጭኖ እንደወሰዳቸው ገለፀ።

ፓርቲው " ክስተቱ የተፈጠረው በሰላማዊ መንገድ የካራማራን የድል በአል ለማክበር በሄዱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው " ብሏል።

ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ ፕሬዚደንቱ አቶ እስክንድርን ጨምሮ የባልደራስ አመራሮች የካራማራ የድል በዓልን እንዳያከብሩ ተከልክለው እንደነበረ ፓርቲው ገልጿል።

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አባላትና ደጋፊዎቹ በአሁን ሰአት በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደሚገኙም ፓርቲው አሳውቋል።

ክስተቱን በተመለከተ በፖሊስ የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

@asosaonline
404 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 08:45:05
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበሩ መገለፁ ይታወሳል።

@asosaonline
438 views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 15:20:20 የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጽን ይመለከታል ፦

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ከቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293,865 ሴት 250,703 ድምር 544,568 ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27,979 ሴት 26,456 ድምር 54,435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ፈተናው ተሰጥቷል። በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321,844 ሴት 277,159 ድምር 599,003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።

የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ ተከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣ በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል።

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል። ነገር ግን በተናጠል የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 141 ተማሪዎች ላይ ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው የተለያየ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ። ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)
@asosaonline
633 views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 15:15:30
ማስታወቂያ ለቅዳሜ ገበያ የጉልት ነጋዴዎች በሙሉ
*************************************
ነባሩን የቅዳሜ ገበያ ወደ ቀደመ ቦታው ለመመለስ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሰረት የፊታችን ቅዳሜ ማለትም የካቲት 19/2014 ዓ/ም በቀድሞ ቦታው ገበያው የሚጀምር መሆኑን እያሳወቅን
1.የከሰል፣ እንጨት፣ ቀርቀሀና ጭድ ንግድ ላይ የተሰማራችሁ አሁን ባላችሁበት ስቴድዮም ጀርባ እንድትቀጥሉ፤
2. ጫት ተራ በአትክልትና ፍራፍሬ ጅምላ ነጋደዎች አገልግሎት መምሪያው እስኪያሳውቃችሁ ድረስ ባላችሁበት እንድትቆዩ፤
3. የልብስ ዘርፍ ላይ ተሰማርታችሁ አልጋ የሰራችሁና ደረሰኝ የተቆረጠላችሁ እስኪጣራ ድረስ ለጊዜው የታገደ በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እያሳሰብን ከልብስ ዘርፍ ውጭ ያላችሁ እና አልጋ ሰርታችሁ ደረሰኝ የቆረጣችሁ የጉልት ነጋደዎች ከላይ በተገለፀው ቀን መገበያየት እንድትጀምሩ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ
****-*--****
የገበያ ቦታ መሸጥ ፣መለወጥም ሆነ ማከራየት የማይቻል መሆኑን እያሳወቅን በዚህ ድርጊት የተሰማራችሁ አካላት ላይ አስፈላጊው እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን፡፡
የአሶሳ ከተማ አስ/ር አገልግሎት ጉዳዮች መምሪያ

@asosaonline
476 viewsedited  12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 18:21:26 #Ethiopia ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ ክፍል 1 PM Abiy Ahimed


1.2K viewsedited  15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 16:37:08 #የተጠቃለለ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሰጧቸው ምላሾች [ የተጠቃለለ ] በአጭሩ ቀርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለም/ቤት አባላቱ ምላሽ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል የኢኮኖሚ ሁኔታ ፣ የዋጋ ግሽበት / የኑሮ ውድነት፣ ሙስና ፣ የተፈቱ እስረኞችን በተመለከተ ፣ አፋርን በተመለከተ፣ ኦነግ ሸኔን በተመለከተ ፣ የልዩ ሀይሎች ጉዳይ ፣ ድርቅን በተመለከተ ፣ የዲፕሎማሲ ምደባ ይገኙበታል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-02-22
423 views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ