Get Mystery Box with random crypto!

አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ተይዘው ተወሰዱ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዘዳንቱን | Assosa online

አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ተይዘው ተወሰዱ።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዘዳንቱን አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አባላት እና ደጋፊዎቹን፤ ፓሊስ በ3 መኪና ጭኖ እንደወሰዳቸው ገለፀ።

ፓርቲው " ክስተቱ የተፈጠረው በሰላማዊ መንገድ የካራማራን የድል በአል ለማክበር በሄዱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው " ብሏል።

ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ ፕሬዚደንቱ አቶ እስክንድርን ጨምሮ የባልደራስ አመራሮች የካራማራ የድል በዓልን እንዳያከብሩ ተከልክለው እንደነበረ ፓርቲው ገልጿል።

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አባላትና ደጋፊዎቹ በአሁን ሰአት በልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደሚገኙም ፓርቲው አሳውቋል።

ክስተቱን በተመለከተ በፖሊስ የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

@asosaonline