Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ:- የአሶሳዩ ኒቨርሲቲ በማታና ቅዳ | Assosa online

ማስታወቂያ
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ:-
የአሶሳዩ ኒቨርሲቲ በማታና ቅዳሜና እሁድ ትምህርት መርሃ ግብር በመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራም በአሶሳ፣ በ2014 ዓ.ም መማር ለምትፈልጉ አዲስ አመልካች የመጀመሪያ ድግሪ ከየካቲት 24/2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም በተከታታይ የስራ ቀናት ምዝገባ ይካሄዳል፡፡
በመሆኑም ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች አድሱ ሥርዓተ ትምህርት ፕሮግራሙ በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስክ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በአካል ወይም በተወካይ በኩል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሪጅስትራል ኦርጅናል ዶክመንትና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በማቅረብ ለመጀመሪያ ዲግሪ ለአሶሳ አመልካቾች 100 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢ አካውንት 1000021168355 በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ዩኒቨርሲቲው የሚሠጣቸው የትምህርት መስኮች
በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም
1. በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ (College of Business and Economics)
ማናጅመንት (management)
አካውንቲግ (Accounting)
ኢኮኖሚክስ (Economics)
ህዝብ አስተዳደር ልማት ስራ አመራር (Public Administration Development Management)
ቱሪዝም ማናጅመንት (Tourism Management)
2. በማህበራዊሳይንስናስነ-ሰብኮሌጅ (College of social science and humanities)
ጅኦግራፊ (Geography)
ሥነ-ዜጋ (Civic)
እንግሊዝኛ (English)
ሳይኮሎጂ (Psychology)
ሶሾሎጂ(Sociology)
ጋዜጠኝነት እና ስነ -ተግባቦት (Journalism and Communication)
3. በተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ /College of Natural and computational science /
ባዮሎጂ (Biology)
ኬሚስትሪ (Chemistry)
ፊዚክስ (Physics)
ስፖርትሳይንስ (sport science)
ሒሳብ (Mathematics)
እስታትስቲክስ (Statistics)
ጅኦሎጂ (Geology)
4. በምህንዲስና ኮሌጅ (College of engineering)
ሲቪልመህንዲስና (Civil engineering)
ኤሌክትሪክና ኮምፒውተር ምህንዲስና (Electrical and computer engineering)
ግንባታና ቴክኖሎጂ አመራር (Construction Technology Management )
ቅየሳ ምህንዲስና (Survey engineering)
ውሃ ሀብት ምህንዲስና (water resource and irrigation engineering)
-መካኒካል እንጂነርግ (Mechanical Engineering)
5. በኮምፒውቲግና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ (College of computing and informatics)
ኮምፒውተር ሳይንስ (Computer science)
ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (Information Technology)
ኢንፎርሜሽን ሳይንስ (Information Science)
6. በግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ (College of agriculture and natural resources)
እፅዋት ሳይንስ (Plant science)
እንስሳት ጤና (Animal health)
ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ (Natural resource and management )
እንስሳት ሳይንስ (Animal science)
ግብርና ምጣኔ ሀብት (Agricultural economics)
አፈር ሀብት እና ተፋሰስ አያያዝ (soil Resource and watershed management)
7. በህግ ትምህርት ቤት /school of law /
 በህግ /LLB in Law /
የመመዝገቢያ መስፈርት
ለመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያመስፈርት
በሌቨል ለተመረቁደረጃ 3 እና 4 ሲኦሲ ውጤት ከለላቸው እስከ አንድ አመት ድረስ ለማቅረብ ውል በመግባት ማመልከት የሚችሉ ሲሆን የመምህራን ሰልጣኞችን አይመለከትም
 የቀድሞ 12ኛክፍልከሆኑለወንዶች 3.2 ለሴቶች3.0
 2013/14 ዓ/ም ያጠናቀቃችሁ ከ700 የተፈተናችሁ 350 እና ከዚያ በላይ ከ600 የተፈተናችሁ 300 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡
 2012/13 ዓ/ምለወንዶች 330 እናለሴቶች 320 እናለታዳጊክልሎችበሁለቱምጾታ 310፤ለአካልጉዳተኛ 300
 2011 ዓ/ም 140 እና ከዚያበላይ
 2008-2010ዓ/ም 295 እና ከዚያበላይ
 2007 ዓ/ም 295 እና ከዚያበላይ
 2006ዓ/ምተፈታኞች 250 እና ከዚያበላይ
 2003-2005 ዓ/ምተፈታኝ 265 እና ከዚያበላይ
 2002 ዓ/ም 280 እና ከዚያበላይ
 2001-200 እና ከዚያበላይ ሊኖራቸው ይገባል
ለመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች መማር የምትፈልጉትን ድፓርትመንት በመምረጥ ማመልከት ይኖርባችኋል
ምልመላውን ላለፉ ሰልጣኞች በውስጥ ማስታወቂያ የመመዝገቢያ ቀን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ 0578875023 በመደወል መረጃ ማገኘት ይቻላል::
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት
@asosaonline