Get Mystery Box with random crypto!

#Dessie ደሴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ የሚያስችል ከ605 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ከፌቤላ | Assosa online

#Dessie

ደሴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ የሚያስችል ከ605 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ከፌቤላ የዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር በመተባበር በተያዘው ሳምንት ለነዋሪዎች እንደሚከፋፍል የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የዘይት አቅርቦቱ በ 'ሸማች ማህበር' በኩል ይቀርባል የተባለ ሲሆን በገበያው ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል የቁጥጥር ስራም እየተሰራ ነው ተብሏል።

በከተማዋ በሸማች ማህበራት በኩል የሚቀርበው የዘይት ዋጋ ፡-

1. ባለ 3 ሊትር 290 ብር ከ06 ሳንቲም

2. ባለ 5 ሊትር 474 ብር ከ40 ሳንቲም

3. ባለ10 ሊትር 936 ብር ከ69 ሳንቲም

4. ባለ 20 ሊትር 1 ሺህ 834 ብር ከ66 ሳንቲም

5. ባለ 25 ሊትር 2 ሺህ 277 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

t.me/asosaonline