Get Mystery Box with random crypto!

★★ናቲ ና ሜሪ★★ ክፍል-35 ናቲ ሊያገኘት በጣም ከመቸኮሉ የተነ | ኤሽ ጣፋጭ ታሪኮች

★★ናቲ ና ሜሪ★★

ክፍል-35



ናቲ ሊያገኘት በጣም ከመቸኮሉ የተነሳ በጠዋት የሚገናኙበትን ኘሮግራም ለማመቻቸት ገመድ አልባ ስልኩን ከጉያው አውጥቶ የሜሪን ስልክ በምሽቱ ያስለቅሰው ተያይዟል።

፠ ሄሎ ናቲዬ

፠ ወዬ የኔ ፍቅር ነገ ስንት ሰአት ነው የምንገናኘው

፠ ከ 9 ሰአት በሃላ ቢሆን ደስ ይለኛል

፠ ምን ሆነሻል ዛሬ እስከዛሬ በለሊት ለመገናኘት እንዳልተሯሯጥን ዛሬ....

፠ ፀጉሬን ጠዋት ለመሰራት አስቤ ነበር እንደውም ለምን ማታ አንገናኝም

፠ ሰላም ነው ግን የኔ ፍቅር ሀሳብሽ በፍፁም ባይገባኝም በዘጠኝ ሰአቱ ተስማምቻለው!!

፠ እሺ ቻው

፠ ቻው

የሜሪ ልብ በሁለት ሀሳቦች መሀል መዋዠቁን ቀጥሏል አንዱ ለምን ስልክሽን ቀይረሽ አጠፊበትም ይህን ሁሉ ጉድ በየትኛው አቅምሽ ተሸክመሽ ትኖሪያለሽ እያለ የግራ ልቧን እንደ ክፉ ውጋት ጠቅ ያደርግባታል። አንደኛው ደግም አግኝተሽው ሁሉንም አፍረጥርጠሽ ነገረሺው ጥፋቱን በደንብ አውቆት በፀፀት ዘላለሙን እንዲኖር ፍረጅበት እያለ ቢወተውታትም ሁለቱንም ለማድረግ መንቀዥቀዡን አልፈለገችም ሰከን ብላ ንዴቷን ለመቆጣጠር ትታገል ጀመር ነገር ግን ንዴቷ አይሎ በንዴት ናቲ ጋር መደወል ጀመረች።

፠ ሄሎ

፠ ወዬ የኔ ቆንጆ ሚስት

፠ ናቲዬ ከጓደኞቼ ጋር ቀጠሮ ነበረኝ እረስቸው ብታይ አሁን ትዝ አላለኝም መሰለህ ለምን ከነገ ወዲያ አንገናኝም

፠ ምን አይነት ቀልድ ነው የምትቀልጅው ያምሻል እንዴ .....ናቲ ንዴት ያንዘፈዝፈው ጀመረ የሆነ ችግር እንዳለ ቢገባውም መገመት ግን ፍፁም አልሆንልህ አለው!!

፠ እረ የቀልዴን ነው አረጋጋው.... ብላ ንዴቱን ስታይ በረድ ብላ አረጋጋችው

፠ እንደዚህ አይነት ቀልድ.............

ናቲ ሲያወጣ ሲያወርድ ቢያድርም አንድም ችግር ሊፈጥር የሚችል ነገር ጠብ አልልህ አለው። ጠዋት በጊዜ ደውላ ፀጉር ቤት ልትሄድ መሆኑን እያወሩ ሳለ በአል በመሆኑ ባንክ እንደሚዘጋ ትውስ አላቸው። ውይ ዛሬ ለካ ዝግ ነው በቃ ከነገወዲያ እንገናኝ ፈጣሪ አላለልንም ማለት ነው አለችው ፈጠን ብላ!! ናቲ ይሄ ከነገ ወዲያ አልጥምህ ስላለው እንዴትም አምታቶ እንደሚመጣ አሳምኗት ስልኩ ተዘጋ።

ከ 2 ሰአታት የ መኪና ጉዞ በሀሏ ሰፈሯ ደርሶ ደለላት

፠ ደረስክ ናቲዬ

፠ አዎ ውጪ ሜሪዬ

፠ እሺ መጣው

ልክ ስታገኘው ሁሉን እረስታ ምንም ክፉ ነገር ልታሳየው ባለመምከሯ ጥርጣሬው ልክ አለመሆኑን እራሱን በማሳመን የተለመደ ፍቀራቸውን ያጣጥሙት ተያያዙ። የያዙት ክፍል ከገቡ በሃላ ናቲ መንገዱ ስላደከመው ከተዘረጋው አልጋ ላይ እጁን እና እግሩን ዘረጋግቶ ጋደም አለ። ባልተለመደ ሁኔታ ጉሮሮው ስር በሁለት እጇ ጠፍራ ያዘችው እንድላፋት ፈልጋ ነው ብሎ ችላ ቢላትም እጇ እየጠነከረ መጣ ናቲ በጣም ትንፋሽ ሲያጥረው እጇን መንጭቆ አስለቀቃት።

፠ እንዴ ምን ሆነሻል

፠ ገድዬክ እኔም ብምት ስሜቴ ነው

፠ እረ ተይ የኔ ፍቅር እኔ ምገባው ገነት የራስሽን ታውቂዋለሽ እዛ ምንገናኝ መስሎሽ ጉድ እንዳትሆኚ

፠ ለምን የ አምፖሉን ሽቦ በጥሰን አንይዘውም ጌታን በጣም ደስ ይለኛል

፠ ሜሪ እየማልሽ ነው ይታወቅሻል አይደል

፠ ጌታን ከልቤ ነው ከዛ ሁሉን እርስት በቃ....

ናቲ ውዝግብግቡ ወጣ ቀልድ እና ምሯ እውነት እና ውሸቱ ተምታቶበታል። ምን ሆና ነው ብሎ የምክንያቷን ጫፍ ለማግኘት ታች ላይ ቢልም በፍፁም ሊሆንለት ግን አልቻለም።

ማታ ባልተለመደ መልኩ በጊዜ ተኛች ናቲ በጣም ግራ ተጋብቶ እዛው ክፍሉ ውስጥ ይጠጣ ጀመረ። ስክር ብሎ ሲደካክመው ፍንግል ብሎ ተኛ።

ጠዋት እንደ አዲስ በፍቅር ቢነሱም ሜሪ በመሀል በመሀል የሰማችው ነገር ሲያበግናት ወደ ቤት ካልሄድኩ ብላ ስትሮጥ እሱም ምክንያቷ ባይገባውም በሩጫ ሲከተላት ለተመለከተ ሻርኘ እና ተራራው ጎደለ እንጂ ቀረፃ ላይ ያሉ የህንድ ፊልም አክተሮች መምሰላቸው ሀቅ ነው።

እንዲህም እንዲያም እያሉ አራት ቀናት ምላቸው ትላንት በተነጋገሩት መሰረት ናቲ በጠዋት ወደ ቤቱ ካልተመለሰ አብረው ካረፋፈዱ መለያየቱ ስለሚደብራቸው የግዱን በጠዋት ለመሄድ ሲዘገጃጅ ሜሪ ሁሉንም የረሳች ይመስል አረፋፍደህ ትሄዳለህ ብላ ትጎተጉተው ጀመር ....ካረፈድኩ ተይ በሃላ ይደብረናል ..ፍንክች አልልም ብላ ሀሳቡን አስቀየረችው። በማርፈዱ ተስማምተው ከያዙት ክፍል ወጡ።

ልክ 7:30 ምሳቸውን ቀማምሰው ፊልም ለማየት ተነጋግው ወደ ሲኒማ ጉዞዋቸውን ቀጠሉ። ሜሪ ከፊት ለፊት ናቲን ትታው ምንቅር ምንቅር እያለች ትጓዝ ጀመር።

፠ ምን ሆነሽ ነው የምትሮጪው ተረጋጊ እንጂ

፠ ከኔ ጋር ምንም ማድረግ ደስ አይልህማ

፠ ስለሚለኝ አይደል እንዴ የመጣሁት

፠ እንደውም ተወው ወደ ቤቴ ሄጄ ባርፍ ይሻለኛል .....ብላ ወደሃለ ተመልሳ ጥላው ሄደች ናቲ አራቱንም ቀናት ወደቤቴ እያለች ሲመልሳት ስለቆየ ምርር ብሎት ባሁኑ አልተከተላትም እንደጠገቡ ወይፈኖች ሁለቱም በየአቅጣጫቸው እየዘለሉ ቻው ሳይባባሉ መለያየቱ የለመደባቸው ይመስላል።

እንደተለመደው ነገሮችን እስክትረሳ ብሎ አንድ ሶስት ቀን አሳልፎ ደወለላት።

፠ ሜሪዬ

፠ አቤት

፠ ምን ሆነሻል ዛሬም ለንብጭሽን እንደጣልሽ ነሽ በይ አፍጥኝው ሚስቴ ናፍቃኛለች ወደ ቤቴ ተመለሽ ...አለ ፈገግ ብሎ

፠ አልሰማህም እንዴ

፠ ምኑን

፠ ሁሉም ነገር እንደተባነነብህ ነዋ!! እረ በቃ ከተነቃብህም በሃላ ይደብራል...
፠ ምን ማለት ነው ...

፠ ሁሉንም ስሰራ የነበረውን አውቄያለሁ አንተ አይደብርህም አሁንም ግቢ ድረስ መጥቼ ላግኝሽ እፈልጋለው እያልክ እሷን እየጀነጀንክ እኔነን እንደምትወደኝ ስታባብለኝ .......

ብላ ጄሪ መሆኗን ፍንጭ ቢጤ ሰጥታው ስልኩን እላዩ ላይ ጥርቅም አደረገችበት....ናቲ መብረቅ እንደመታው ሰው ድርቅ ብሎ ቀረ መልሶ ስልኳ ላይ ቢምክር ተዘግቷል። ምን እየሰራች ይሆን? እኔን ተበቀልኩ ብላ አንዳች ስህተት እንዳትሰራ ብቻ? የት ሆና ይሆን? ሀሳቡ ተዘበራርቆ ስልኳን ሲምክር ውሎ አመሻሹ ላይ ሰራለት።

፠ ሜሪ ተረጋጊ ምንም አይነት ስህተት እንዳትሰሪ

በጣም ብዙ ከብረት የጠነከሩ ቃላት አዥጎደጎደችብኝ የእውነት በህይወቴ እንዲህ ቅስሜ የተሰበረበት ቀን በፍፁም ኖሮ አያውቅም....... ያደረኳቸው ነገሮች ተገለባብጠው ይህን በመሰለ መልኩ መቅረባችው በእጅጉን ቢያስገርመኝም አላደረኩም እንዳልል አድርጌያለሁ አድርጊያለው እንዳልል ተገለባብጠዋል። እንዳብራራላት እድሉን እንድትሰጠኝ ብጠይቃትም የኔ እወነት ዋጋ አጣ። እኔ ውሸታም መሆኔን የዋሸሁት ደግም ከሁለቱም ጋር ልወሰልት በመፈለጌ እንደሆነ ሁለቱም 100% አምነውበት ደምድመው ጨርሰዋል።