Get Mystery Box with random crypto!

★★ናቲ ና ሜሪ★★ ክፍል -34 ሜሪ ለ ጄሪ ፠ ሄሎ ጄሪ | ኤሽ ጣፋጭ ታሪኮች

★★ናቲ ና ሜሪ★★

ክፍል -34




ሜሪ ለ ጄሪ

፠ ሄሎ ጄሪ

፠ ሄሎ ማን ልበል

፠ ሜሪ ነኝ ጄሪዬ

፠ ወዬ ሜሪዬ እንዴት ነሽልኝ

፠ አለሁልሽ ማሬ

፠ ሁሉም ሰላም

፠ ሁሉም ሰላም ነው

፠ እንዴት መልካም ልጅ ነሽ አነጋገርሽ ስረአት አለው እንዲህ መልካም ሴት ሆነሽ ነው ናቲ ሊወሰልትብሽ እኔ ጋር የመጣው

፠ ማለት?

፠ አይገርምሽም መጀመሪያ እኮ አብራቹ ሆናቹ ነው ሚስቴ ላይ መወሰለት እፈልጋለሁ ብሎ እኔም ባሌ ላይ ብየው የተገናኘነው

፠ ምን ? እኔ እኮ ይቅርታ ልጠይቅሽ ነበር ካንቺ ጋር ሆኖ ወደኔ እንዲመጣ በማድረጌ

፠ ኖ ሜሪዬ አታሎናል ባክሽ

፠ በዛ ላይ ደግም አንቺን ለብር ነው የሚፈልግሽ አብረን ሆነን የሱፍ ብር ከሷ ነው ምቀበለው እያለ ሲፎክርብኝ ነበር

፠ እኔን ብር ፍለጋ ነበር የቀረበው

፠ አዎ ብታይ ምን ያልምከረው ነገር አለ መሰለሽ እኔ እራሱ ብዙ ብሬን እሱ ጋር በመመላለስ ነው የጨረስኩት

፠ በፈጣሪ ልክ ነሽ አንዴ ብርላኪልኝ ብሎ የለኝም ስለው እንዴት እንደሆነብኝ ብታይ አይ ናቲ
፠ ተጠንቀቂ በፍፁም የሚሆንሽ ሰው አይደለም ስለ ፍቅር በፍፁም የሚያውቅ ሰው አይመስለኝም በኔ ብትማሪ መልካም ነው እህቴ።



ሜሪ እጅግ በጣም የዋህ ሴት ናት እንኳን ትንሽ በእውነት ያሸበረቀች ውሸት ቀርቶ ልሙጥ ውሸት በማደናገር ለውሰው ካቀረቡላት እንደፈጣሪ ቃል መቀበሏ ሀቅ ነው። በትንሹ ወደ ሃላ መመልከት እንኳ አይቀናትም። ይህን ማድረጎ የዋህ ቀና ነች የሚያስብላት መስሎ እንደሚሰማት በተደጋጋሚ ለ ናቲ ብትነግረውም ይህን ያህል ሁሉን ነገር ጣል አድርጋ የምትባለውን ታምናለች ብሎ ግን በፍፁም አስቦት አያወቅም።

ናቲም ቢሆን ስለ ሱፉ ማውራቱ ከሜሪ ብር እቀበላታለሁ ለማለት ፈልጎ ሳይሆን ለጄሪ ማሰቡ ነበር።
ጄሪን እርግፍ አድርጎ ቢተዋት ....እኔ ማለት ተራ ሴት ነኝ? እኔ ማለት የወረድኩ ሴት በመሆኔ ነው ሚስቱን ሲያገኝ የተወኝ? ብላ እንድታስብ .......... እኔ ናቲን የተውኩት ለብር ያለውን አመለካከት ተመልክቼ ለብር ያለው ፍቅር አንገሽግሾኝ የምትልበትን ምራል እንድታገኝ ቢሆንም ........።


ጄሪ ለ ሜሪ


፠ ካንቺ ጋር መች ነው ቆይ በድጋሚ የጀመረው

፠ ቀኑን ነገረቻት

፠ ከዛ በሃላ እኮ ካልመጣሽ ከእሷ ጋር አድራለሁ ብሎኝ ግቢ ሄጄ አብረን አድረናል

፠ ምን?

፠ ለካ ሁለታችንንም ሲጫወትብን ነበር?

ይህንንም ቢሆን ከ ሜሪ ጋር ታርቀው ነገር ግን ሳያገኛት ያደረገው ነገር ሲሆን። አንደኛ ብር እንደሌላት ስለሚያውቅ ባለመምጣቷ ተማምኖ። ሁለተኛው ግን ናቲ ወስላታ ስለሆነ ተውኩት የምትልበትን ምራል ሊሰጣት ፈልጎ ነበር። እመኑኝ የትኛውም ወንድ ሌላ ሴት ጋር እሄዳለው የሚላት ተናዳ እንድተወው አስቦ እንጂ እሄዳለው ስላልኳት አብራኝ ልታድር ትመጣለች ብሎ የሚያስብ ጅል ወንድ በፍፁም ይኖራል ብዬ አላምንም።

ናቲ መወስለት ቢፈልግ ለ ሜሪ ምንም ሳይነግራት ሁሉንም በሚስጥር ማድረጉን በመረጠ ነበር። በየትኛውም መንገድ እንኳን መገናኘት መተያየት የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር አለመቻሉን እንኳን እሱ እነሱም ጠንቅቀው ያውቃሉ ግን ያንን አልመረጠም።



ጄሪ ለ ሜሪ

፠ ሄሎ ሜሪዬ

፠ ወዬ ጄሪ

፠ ሳልነግርሽ ጉድሽን

፠ ምንድነው ደም

፠ እረ ይሄ ናቲሽ ጓደኞቼ ጋር እየደወለ አስታርቂኝ ብሎ እያለ ነው በቅርብ ደም ግቢ ድረስ ሊመጣ መሆኑን ነገረችኝ ጓደኛዬ

፠ ምን

፠ አይገርምም ደም እኮ ምክንያት የሚደረድረው ነገር ነው የሚያስቀኝ አሁን ብትነግሪው 1000000 ምክንያት ደርድሮ ሊያሳምንሽ መምከሩ አይቀሬ ነው አይ የምክንያት ሰው ናቲ ....haha



ናቲ ምሎ መካዱ ህሊናውን ቢያጎብጠው ምንም ሳትበድለው ስለበደላት ይቅርታዋን መማፀኑ ልቧ እያወቀ ይህንንም ዞር አድርጋ ሜሪን ለማሳመን ተጠቀመችበት።

ሜሪ ናቲ ለ ብር እንደማይፈልጋት ለማወቅ ሁለት እርምጃ ወደ ሃላ መመልከት በቂዋ ቢሆንም አላደረገችውም። ባዶ ኪሷን ስትቀመጥ አብሯት ኩርምት ማለቱ እንዴት ማስታወስ ተሳናት። ብሯ አለቀ ብሎ የነደደው ልቡ እንዴት ከአይነ ህሊናዋ ጠፋ። እንካ ውሰድ ስትለው እንኳ ከእሷ አብሮ ማሳለፉን መርጦ የካርድ እንኳ ሳይተርፈው እቤቱ መግባቱን እንዴት መዘንጋት ይቻላታል።

እንዴት ከአይኗ ጆሮዋን ማመኑን ልቧ ፈቀደ?

እንዴትስ እንደጎዳት ከነገራት ልጅ መልካም ምክር አገኛለሁ ብላ አሰበች?

እንዴት ስለምታውቀው ናቲ የማታቃትን ጄሪን ማመኑ ሆነላት?

ትንሽ እውነት በትልቅ ውሸት ተጠቅልሎ ሲሰጣት ጫፍ ጫፉን ተመልክታ እንደት መዋጡስ ሆነላት?



ወንድሜ እኔ ከ ሚስትህ ላጣላህ ብፈልግ

ባሏ :- " ሚስቴ ቂጣ ስለምትወድ ቁርስ ከቂጣ በቀር አትበላም" ብትለኝ

እኔ:- "ባልሽ እሷ ቂጣ የምትበላው ስለቸገራት ነው አለኝ "......... ብዬ ለፀብ እንድትሆን አሰማምሬ ነው የምነግራት

ምኝ ከሆነች ሚስትህ በትንሽ እውነት የተጠቀለለውን ውሸቱን አምና እንዴት ችጋራም ትለኛለህ ብላ ጉሮሮህ ላይ መቆሟ አይቀሬ ነው። አላወራሁም እንዳትል ስለ ቂጣ መብላቷ ካንተ በቀር የሚያውቅ የለም አውርቻለሁ እንዳትል ስለመውደዷ እንጂ ስለ ችጋራምነቷ በፍፁም ትንፍስ አላልክም።

ልታስረዳት ስትምክር ወሬውን ከማመኗ በላይ እንዳወራህ እርግጠኛ ሆና የምጮኸው ጩኸት ያደክምሀል ...የምትችለውን ያህል ትጥር እና ስታስበው ጭራሽ የማታውቀውን ሰው ይህን ያህል አምና ትዳሯን የምትበትን ከሆነ ነገ እህቷ ጠልታህ ታጥቦ የተቀሸረ ምርጥ ወሬ ብታወራላት በተኛህበት ጉሮሮህን በጥሳ እንደምትጥልልህ ሴይጣን ሹክ ሲልህ ማስረዳቱንም ማሳመኑንም ትተህ እርግፍ አደርገህ መተወህ ግድ ይሆናል.........ታድያ ወንድሜ ትዳርህን በተንኩት ማለት አአ

....... ይህን ለመመልከት ሜሪ ጊዜ አልነበራትም? ማን ስለሆነች ነው ይህን የምትመክረኝ? ሴት ጋር ልሄድ ነው ብሏት እሱን ፍለጋ የሮጠች ልጅ እንዴት እንዴት ማዳመጡ ቀለላት?