Get Mystery Box with random crypto!

★★ናቲ ና ሜሪ★★ ክፍል-36 ፠ ሄሎ | ኤሽ ጣፋጭ ታሪኮች

★★ናቲ ና ሜሪ★★

ክፍል-36




፠ ሄሎ ናቲ

፠ ሰላም ነው ጄሪዬ

፠ አለሁልህ ስለ ሜሪ ልታወራኝ ፈልገህ ነዋ

፠ አዎ ያልሻት ነገር ........

ብዙ ካወሩ በሃላ ምንም አይነት ልታደርግለት ዝግጁ አለመሆኗን ገልፀችለት ቢቻላት እንደው ቢለያዩ እና ሜሪ እንደሷ ከመጎዳት ብታመልጥ ስሜቷ መሆኑን በቀጥታ ገለፀችለት። የጠበቀው ነገር ስለሆነ ያን ያህል በንግግሯ አልተገረመም ነገርግን በትንሹም ቢሆን ነገሮችን ታስተካክልልኛለች ብሎ አስቦ ስለነበር በመልሷ ተስፋ ቆረጠ። ከጄሪ ሌላ በምን የተጣመመ ፍቀሩን ማቃናት እንደሚቻለው ሲያስብ ቢቆይም ድካም ሆነበት ትርፉ።

ናቲ ለሜሪ

፠ አቤት

፠ እንዴት ነሽልኝ

፠ አለሁ ቆይ አልደከመህም

፠ ትዳሬን በትኜ ምኑን ተኛውት?

፠ በነገራችን ላይ ታውቃለህ አይደል

፠ ምኑን

፠ የፊሜኒስት አቀንቃኝ መሆኔን

ሳቅ አፈነኝ " ያኔ ስለ ጄሪ ሁሉን ነግሬሽ ትቻት ስመጣ..... ጄሪን ምን አደረካት? የሆነ ነገር አድርገህ ልታጠነክራት ይገባል እኮ እንዴት ዝም ብለህ ትተዋታለህ? እንደማለት ላረጋጋት ጥቂት ጊዜ ለሷ መስጠቴ ይህን ሁሉ ግርግር ፈጥሮ ትንሽ ሲጎዱ አጋጣሚውን ተጠቅም ፊሜኒስት መሆን አይከብድም?" ልላት ፈልጌ በእሳት ላይ ቤንዚን መነስነስ እንዳይሆንብኝ ሰግቼ ሳቄን አፍኜ

፠ አዎ.....አዎ አውቃለሁ

፠ እና የጄሪ ጉዳት ማለት የኔም ጉዳት ነው አሁን ከሷ ጎን ነኝ .....

አሁን ከቅድሙ በላይ ሳቄ ይታገለኝ ተያይዟል ....የሳ ፊሜኒስት መሆን ሳይሆን የሷ እና የጄሪ አንድ ሀሳብ ሳይኖራቻው መግባባታቸው ግርምትን ፈጠረብኝ። የሜሪ ፍላጎት ለምን እርግፍ አድርገህ ትተሃት ሳትመጣ ለምን ያን ያህል መቆየቱ አስፈለገ እንደሆነ አውቃለሁ። የጄሪ ግን ምን ይሆን? ለምን እርግፍ አድርገህ ሳትተወኝ? ይሆናል ብዬ አላምንም ካልሆነ ከሜሪ በተቃራኒው ነው ማለት ነው። ምንድነው ያስማማቸው አልገባኝም?" ያሰብኩት አስቆኝ ሳቄን አፈን አድርጌ

፠ እ... እሱማ ልክነሽ


ጥቂት ካወራን በሃላ ባለመግባባት ተግባብተን ስልኩ ተዘጋ።

ማረፍ ያለመደው ጭንቅላቴ ንዝንዙን ጀመረ .....

ቆይ ምኗን ወደህ ነው ይህን ያህል የምትጨነቅላት?

ቁንጅናዋን ነዋ ... መልሼ እረ አይደለም ከሷም በላይ ቆንጅዬ ከሆኑ ሴቶች ጋር አሳልፌያለሁ እኮ ግን የዚህን ያህል አልሆንኩም። አያድርግባት እና እሳት እዳየው ፌስታል ፊቷ ተጨማዶ ብትመጣ እንኳ ፍቅሬ እንደማይቀንስ አውቃለሁ። ታዲያ ምኗ ነው....

ስለምትለብስ ይሁን .....እረ በፍፁም ቡቱቶ ለብሳ አብዳ ብትመጣ ከልቤ አቅፌ እንደምቀበላት ልቤ ያውቀዋል ይህም በፍፁም አይሆንም።

በቃ ባህሪዋ ነው ብዬ ወስኜ ሳልጨርስ አሁን ቀንዴን እያስበቀለኝ ያለው ጭቅጭቋ እኔን አለማመኗ ትዝ ቢለኝ እሱም አብራት እያለ አብሪያት ለመኖር መጣሬ ምክንያቴን አፈረሰብኝ።......ኡኡኡኡኡ እረ እባካቹ አንድ የመውደዴን ምክንያት አፋልጉኝ እና እሳን ለመርሳት መላ ልፈልግ። .....እያለ ህሊናውን ሲምግት ቆይቶ ሲመረው ይደውልላት ጀመረ።

ናቲ ለ ሜሪ

፠ ቆይ ስራ የለህም እንዴ

፠ ከዚህ የተሻለ ከየት ይመጣል ስራ

፠ ካንተ ለመለየቴ ሰው አለማክበርህ ከበቂ በላይ እኮ ነው።

መሬት ወድቀሽ ብትነሺ ወርቅ አፍሰሽ ትነሺ ይመስል መሬት የወደቀውን የኔ ቢጤ ከመፀየፍ በላይ ሰው መናቅ የለም እኮ? የኔ ቢጤ ንቄ ለሀብታም አላሸረግድም። ለኔ ሰው ማለት በዳቦ እንደተያዘ ፌስታል ነው ውጫዊው የፌስታሉ ዋጋ ሳይሆን ወስጣዊዉ የዳቦ ዋጋ ነው የሚያሳስበኝ። በ500 ብር ፌስታል የ 1 ብር ዳቦ ከሚሰጡኝ በ1 ብር ፌስታል የ 500 ብር ዳቦውን እመርጣለሁ። በአጭሩ ከልብሱ ልቡ ውድ ለሆነ ሰው አጎነብሳለሁ ። አለማክበር ይሄ ከሆነ አዎ ሰው አላከብርም''.... ለማለት ቢቃጣኝም ለጊዜው በዝምታ ማለፉን መረጥኩ .....ቀጠለች


፠ ይህን ያህል የምትለማመጠኝ ለብር ፈልገኸኝ ነው አይደል? መደበሪያክ አደረከኝ እኮ። ካንተ ለመለየቴ የመጀመሪያ ምክንያቴ ምን እንደሆነ ታውቃለህ ያኔ ብር ስላልነበረኝ ባንተ ብር መብላት ባንተ ብር ማደር ባለመፈለጌ ነው ነበር። ከዛ በሃላ ነው የታመምኩት አሁንስ ደና ነህ?

በሀሳቤ ሜሪ እየከሳችብኝ መጣች ቆሌዬን ሳይሆን ቆዳዬን የገፈፈችኝ ያህል ከባድ ህመም ሙሉ ሰውነቴን ተሰማኝ። ምንም ሳልናገር መልካም ህይወት ብዬ ስልኩን ዘጋሁት።

ቆይ ብር ከኔ ፈልገህ ማለት ምን ማለት ነው?

የቱን ብርእንደሆነ በፍፁም አልገባኝም። ሳላውቅ ኢንቬስተር ጠብሼ ሀብቷን ደብቃኝ ይሆን እንዴ? እረ ሀብቷን ከሰው የሰማው መስሏት እንዳይሆን ደውዬ የማውቀው ነገር አለመኖሩን ላሳውቃት .....እያልኩ በራሴ እቀልድ ጀመር ስበሳጭ መሳቅ ይቀናኛል በጣም እየሳቅኩ በጣም አንጀቴ እርርር አለብኝ። ከብር ያነሰ ለተራ ፍቅር ነው እንዴ ይሄ ሁሉ መልፋቴ ......

ቆይ እኔ ብር ፍለጋ ልምጣ አንደውም ጀግና ነኝ ባዶ ኪሴን መሆኔን አውቀሽ ወደሽኝ ያንን ወሰድክ የምትይውን ስባሪ ሳንቲም ጠቅልዬ መውሰድ ከቻልኩ። ቆይ ከያዝሺው ብር አንሰሽ ነው ካንቺ በላይ ብሩን ፍለጋ እኔ ጋር መጣህ የምትይው? .......እያለ ናቲ የቆሰለ አንጀቱን በመጠጥ ሊያቃጥለው ወደ አንድ መጠጥ ቤት ጉዞውን ቀጠለ። ብቻውን ሲጠጣ አምሽቶ ወደ ያዘው ክፍል ዘው ብሎ ገብቶ ከአልጋው ላይ ተዘረረ።
:
:
:

#ከ__በሃላ

፠ ሜሪ የልጆቹ ቦርሳ የት ነው?

፠ ሶፋው ላይ ናቲዬ

፠ የረሃዋን አጊንቸዋለሁ የማርኮንን አጣሁት? ምን እየሰራሽ ነው ለምን ወተሽ አትሰጪውም ሹፌሩ ወደ ት/ት ቤት ሊወስዳቸው ውጪ ቆሟል እኮ ......
.
.
.ይቀጥላል