2021-11-02 12:10:42
የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የክተት ጥሪ
ሀገርን ከነ ሙሉ ክብሯ ለማቆየት ያለንን አማራጭ ሁሉ እንጠቀማለን ሲል የደቡብ ክልል መስተዳድር
ምክር ቤት አስ ታወቀ፡፡
መስተዳድሩ ባወጣው መግለጫ የክልላችን ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን
አሸባሪው የትህነግ ሴራ በማክሸፍ የሀገራችንን ህልውና በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ተሰላፊ
ይሆናሉ ብሏል።
ባለፉት ዓመታት በክልላችን በዚህ የሽብር ቡድን አቀናባሪነት በተከሰቱ ግጭቶች የበርካታ ዜጎቻችን
ህይወት ተቀጥፏል፣ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል፣ ዜጎች ተፈናቅለዋል፣ ዘርፈ ብዙ ጉዳት
መድረሱ ተገልጿል።
ይህ በአጉል ተስፋ የተሞላ ቡድን አሁንም ይህን እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል በአማራና አፋር
ክልል ህዝቦች የማያቋርጥ የህልውና ስጋት ደቅኖ ይገኛል። ይህ ህገወጥ ቡድን ጠቤ ከተወሰኑ ክፍሎች
ጋር ነው ቢልም ዋነኛ ግቡ ሀገራችንን ማፍረስ እንደሆነ እሙን ነው ብሏል መግለጫው።
ዛሬ በአማራና አፋር ክልሎች የጀመረውን የሽብር፣ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ መድፈር፣ ዘረፋና የሌብነት
ተግባር በእነዚህ አካባቢዎች ተገድቦ የሚቀር እንዳልሆነ መታወቅ አለበት ብሏል መግለጫው ።
ይህ የጥፋት ቡድን ትውልድን ሲያመክን የኖረ፣ ከውጭ ጠላት በላይ የኢትዮጵያን ክብር ያዋረደ ሰው በላ
ስርአት እስከወዲያኛው ታሪክ ሆኖ እንዲቀር የጠነከረ አንድነት ያስፈልጋል፤
ይህንን የሽብር ቡድን አምርሮ መዋጋት ደግሞ አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ መላው የክልላችን
ህዝቦች ቡድኑን በመገርሰስ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አስተለልፏል።
መስተዳድሩም የክልሉ ህዝቦች የሽብር ቡድኑን ተላላኪዎችና ሰርጎ ገቦችን መከታተልና የአካባቢን
ሰላም ከምንም ጊዜ በላይ ነቅቶ በመጠበቅ በግንባር እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣
ለክልል ልዩ ሃይሎች፣ ለሚሊሻዎችና ለተፈናቀሉ ወገኖች ስታደርጉ የቆያችሁትን ሁለንተናዊ ድጋፍ
አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ሲል ጠይቋል፡፡
በክልላችን ያለንን ብዝሀነትን በመጠቀም ሊያባላን ያሰፈሰፈውን የጠላት ሃይል ግብአተ መሬት
ለመፈጸም መላው ህዝባችን በአንድነት እንዲንቀሳቀስ፣ የክልላችን ወጣቶችም ጀግናው የመከላከያ
ሰራዊት እንዲቀላቀሉ፣ አካባቢያቸውን ተደራጅተው በንቃት እንዲጠብቁ፣ በየደረጃው ያለው አመራርም
የክልሉን ጸጥታ አካላት፣ ወጣቶች እና ምልዓተ ህዝቡን በማስተባበር በግንባር ቀደምትነት
እንዲረባረብና ለማይቀረው ድል ያለንን ሁሉ ምንም ሳናስቀር ጠላትን ለመመከትና ሀገርን ለማዳን
በማዋል ለሚደረገው ፍልሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት
መወሰኑን አስታውቋል፡፡
2.4K views09:10