Get Mystery Box with random crypto!

በእርዳታ ስም የሚደረግን ጣልቃ ገብነት መንግሥት አስጠነቀቀ በእርዳታ ስም የራሳቸውን የውጭ ፖሊሲ | @ArtsTvWorld - Arts TV - አርትስ ቲቪ

በእርዳታ ስም የሚደረግን ጣልቃ ገብነት መንግሥት አስጠነቀቀ
በእርዳታ ስም የራሳቸውን የውጭ ፖሊሲ የሚያራምዱ አንዳንድ አገራት ከድርጊታቸው ሊጠነቀቁ እንደሚገባ መንግሥት አሳሰበ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያና የእውነት ወዳጆች ሰልፍም ይህንኑ በተለያዩ ሰበቦች በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎትን የሚቃወም እንደሆነ አሳውቋል፡፡

ሰልፈኞቹ ጣልቃ የሚገቡ አገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረሱ ያለውን ጥፋት ሊያጤኑ እንደሚገባ ስለመግለፃቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ገልጸዋል፡፡
በዲያስፖራው በኩል ኢትዮጵያን ለመደገፍ የሚስተዋለው መነሳሳት የሚደነቅ ነው ብለዋል

መንግሥት የዲያስፖራውን ተነሳሽነትና የድጋፍ ጥያቄ በማስተባበር ይሰራልም ብለዋል፡፡
አገሪቱ ላይ የሚደረገውን ጫና በራሳቸው ተነሳሽነት ለዓለም ያሳወቁ ሰልፈኞችን ተመስግነዋል፡፡