Get Mystery Box with random crypto!

' እውነተኛ መኖር ለእናንተ ምን አይነት መኖር ነው? ምናልባት ብዙዎቻቹ እውነተኛ መኖርን የሚትተ | አርጋኖን ስነ-ግጥም ና ጭውውት ..On.Tg

" እውነተኛ መኖር ለእናንተ ምን አይነት መኖር ነው? ምናልባት ብዙዎቻቹ እውነተኛ መኖርን የሚትተረጉሙት የራሳችሁ የሆነ መተርጎምያ መንገድ አላችሁ። እውነታው ግን እውነተኛ መኖርን የምንረዳበትና የምንተረጉምበት መንገድ ልክ ነው የሚለው ነው። ለብዙ ሰው እውነተኛ መኖር መብላት፣ መጠጣት፣ መማር፣ መመረቅ፣ ስራ መያዝ፣ ጥሩ ቤት መስራት፣ ቆንጆ ሚስት ማግባት፣ ልጆች መውለድ ይመስለዋል። በውኑ እውነተኛ መኖርና ትክክለኛ የተፈጠርንበት #ዓላማ ያ ነው ወይ?

እውነተኛ መኖርን ወደ መረዳት እውነተኛ መረዳት መምጣት ግድ ይለናል። እውነተኛ መኖር ስለ መብል ከማሰብ በላይ ነው። እውነተኛ መኖር የተፈጠራችሁበትን ዓላምችሁን በማወቅ መኖር ነው። ለምን እንደተፈጠራችሁ፣ በዚህች ምድር ምን እንደምትሰሩ ካወቃችሁ እናንቴ እየኖራችሁ ያላችሁት እውነተኛ መኖርን ነው። ስለዚህ እውነተኛ መኖርን እየኖርን እንደሆነ ከምመስለን የውሸተ መኖር ልንወጣና እራሶቻችንን ልንታደግ ዘንድ ያስፈልጋል።"