Get Mystery Box with random crypto!

አናሲሞስ - Anasimos

የቴሌግራም ቻናል አርማ anasimos_tube — አናሲሞስ - Anasimos
የቴሌግራም ቻናል አርማ anasimos_tube — አናሲሞስ - Anasimos
የሰርጥ አድራሻ: @anasimos_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.69K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙሮች ግጥሞች ከነ ዜሞቻቸው ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
share ማድረግ እንዳይረሳ
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Youtube -https://youtu.be/hiPRAx332IY

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-05-29 10:56:17 "ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"

#ቅዱስ_ኤፍሬም
2.2K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 12:54:34 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፦
፩ኛ. ትዕቢተኛ ዓይን፥
፪ኛ. ሐሰተኛ ምላስ፥
፫ኛ. ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
፬ኛ. ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
፭ኛ. ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
፮ኛ. በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
፯ኛ. በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

ምሳሌ 6÷16-19
3.1K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 17:01:49
ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት?

ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ።

ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን።

ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!!

Deacon Henok Haile
3.2K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:11:46
ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
3.4K viewsኦርቶዶክስ ፕሮሞሽን ❖ ፭, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 06:27:07
#ግንቦት_1

#ልደታ_ለማርያም

በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና።

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ።

ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው።

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው።

በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
3.6K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 15:50:41
እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንኹት፥ እርስዋንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ የዘላለም ማረፊያው በሆነች በእናቱ ፍቅር እኖር ዘንድ፤ እርሷን ደስ አሰኝ ዘንድ ፤ ያማረው የፊቷንም ብርሃን እመለከት ዘንድ፤ በዓለም ካሉት አእላፋት ዝና ይልቅ ልቤ የድንግልን ፍቅር ይመኛል፣ የዓለሙ ዝና ነፍስን ለሚያቆስል ትዕቢት አሳልፎ ስለሚሰጥ ምን ይጠቅመኛል? የድንግል ፍቅር ግን ዕረፍትና ጸጥታ ይሆነኛል፣ ወደ መዳን መንገድም ስቦ ያስገባኛል፤ ልቡናዬ የክብርሽን ገናንነት ይናገር ዘንድ ይወዳል፥ መላሴ ግን በኃጢአት ፍሕም የተበላ ኮልታፋ ሆኖ ተቸግሯል፤ የልሳኔን ልቱትነት አርቀሽ፥ እኔ ደካማ ባሪያሽን በምስጋናሽ ቃል የምትሞይበት የኃይል ቀን መቼ ነው? ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደ ምትናፍቅ እኔም ምስጋናሽን እየተጠማሁ ያቺን ቀን እናፍቃለሁ። መቼ እደርሳለሁ? መቼስ አንቺን አመሰግንሻለሁ?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
2.7K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 12:50:34 “ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
3.9K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ