Get Mystery Box with random crypto!

አናሲሞስ - Anasimos

የቴሌግራም ቻናል አርማ anasimos_tube — አናሲሞስ - Anasimos
የቴሌግራም ቻናል አርማ anasimos_tube — አናሲሞስ - Anasimos
የሰርጥ አድራሻ: @anasimos_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.69K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙሮች ግጥሞች ከነ ዜሞቻቸው ለማግኘት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
share ማድረግ እንዳይረሳ
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
Youtube -https://youtu.be/hiPRAx332IY

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-11 15:57:29 ዘፈን ለምን ይከለከላል

➭ ዘፋኝነት የተከለከለበትን ምክንያት በግድ ማወቅ አለብኝ ለምን ትላለህ?

➨ ምክንያቱን ማወቅህ አያፀድቅህም አለማወቅህም አያስኮንንህም፡፡ ነገር ግን ዘፋኝ ብትሆን ትጠየቅበታለህ፡፡ ባትዘፍን ደግሞ ታዛዥ ተብለህ በእግዚአብሔር ዘንድ ትመሰገነበታለህ፡፡ ስለዚህ የሚመለከትህን ለምን አታደርግም?

➣ . . . ዘፈን ለምን እንደተከለከለ መዘርዘሩ ምስጢሩን እንደሚያጠበው መገለጹ ትክክል ነው፡፡ ቢሆንም ይሕ እንዳለ ሆኖ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት የዘፈንን ጎጂ ገጽታ ማሳየት ይገባል፡፡

ሀ. ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና፡፡

➣ ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ›› በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል፡፡ ኢሳ 13፥21 አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን ተረዳ፡፡
ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል ‹‹ . . . እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› 1መቃ 36፡27-28 የዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለውን አጋንንትን ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጎራ መሰለፋቸው ነው፡፡

➾ ዘፈን የአጋንንት ስራ መሆኑን ስታውቅ አይንህ ተገልጦ አንድ ምሥጢር መመርመር ይጀምራል፡፡ እስኪ ሀገራችንን ጨምሮ የጃማይካውያንንና የአንዳንድ የአፍሪካንና የሌሎችንም አህጉራት ዘፋኞችን ድርጊት ልብ ብለህ መርምር፡፡ ደግሞም ፀጉራቸውን አንጨብርውና በመናጥና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛውም እንደሆነ ማስተዋል ሞክር፡፡ የባለ ዛሮች ዝየራ አይተህ የምታውቅ ከሆነ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ባለውቃቤዎችስ ሲደነፉ ተመልክተህ አታውቅምን? የባለ ውቃቤዎች ድንፋታ ደግሞ ቁርጥ እዋኽ፣ እዋኽ እየተባለ የሚዘፈነውን ባህላዊ ዘፈን ይመስላል፡፡ ፍከራው ቀረርቶውና በየብሄረሰብ የምትመለከተውን ዘፈንና ጭፈራ ብትመረምር ከዚህ የቀረበ መመሳሰል አታጣበትም፡፡ ቅዱስ ሐዊ እንደተናገረው ‹‹ዘፈንና ዳንስ ከሰይጣን የተገኘ›› ነውና፡፡

➨ አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ የዘፈንና የጭፈራ ዓይነት ሁሉ ምንጮች ናቸውና፡፡ ከዚህ በኋላ የእኔ ስጋት ዘፋኞች እና ጨፋሪዎች አዳዲስ የዘፈን እና ጭፈራ መንገድ (ስታየል) ለመኮረጅ ሲሉ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ፍለጋ በየፀበል ስፍራው መዞር እንዳይጀምሩ ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች የሚሹት ገንዘብንና ዝናን ብቻ እንጂ ሃይማኖት እና ምግባርን አይደለምና፡፡

➲ ለ. ክርስትያን የሆነ ሁሉ ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡

ዘፋኝነት እንደ መተዳደርያ ስራም ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በዘፋኝነት ‹‹ሥራ›› የተሰማሩ ክርስትያኖች በሃይማኖት ለመኖር ከወደዱ በንስሐ እንደተመለሱ ዝሙት አዳሪዎችና ቀማኞች ሁሉ እነርሱም ሌላ የስራ አማራጭ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡

በዘመናችን የሐጢያት ተግባራት በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ግን እንደ ሙያ (ፕሮፌሽን) መቆጠር የለበትም፡፡ ‹‹መተዳደሪያዬ ነው›› እያሉ ሕሊናን የሚቆጠቁጥና መንፈሳዊነትን የሚጋፋ ስራ ከመስራት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ አትስረቅ አታመንዝር ያለ እግዚአብሔር ‹‹አትዝፈን›› ደግሞ ብሏል፡፡ ታዲያ በመንፈሳዊ ጎዳና ለሚመለከተው ዘፈን ከስርቆትና ከምንዝር በምን ይለያል? ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረስ አንድ ናቸውና፡፡ ምን ላድርግ? መተዳደሪያዬ ነው እያሉ በዘፋኝነት ጸንቶ ከመኖር አማራጭ መሻት ይበጃል፡፡ በዚህ ዓለም ስጦታው ዘፋኝነት ብቻ የሆነና ሌላ ምንም ዓይነት ተውህቦ (ስጦታ) የሌለው ሰው የለም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ፈጣሪም ዘፋኝነትን ባላወገዘ ነበር፡፡ አንበሳ ምግቡ ሥጋ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንበሳ ሳር እንዲበላ ማድረግ እንደማያቻል ሁሉ ዘፋኞች እንደሌላው ሰው በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው መኖር የማይችሉ ቢሆኑ ኖሮ ፈጣሪ ዘፋኝ አትሁኑ የሚል ትእዛዝ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ካሰቡበት እንደሌላው ሰው ሁሉ ዘፋኞችም ሌላ የስራ አማራጭ አላቸው፡፡

➼ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹ስለ ተግባረ እድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ህግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሰሩ ይገባል፡፡ . . . እንደ ዘፋኝነት፣ እንደ መጥፎ ጨዋታ፣ በእግር አንደማሸብሸብ (ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር፡፡›› ፍት.ነገ.መን.አን 23፡820 ይሕ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደስራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል፡፡

➲ ሐ. ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ሀጥያት ነው፡፡

➣ ገላ 5፡21 ስለዚህ ዘፈን መዝፈን በመጽሐፍ ቅዱስ በእጅጉ ይከለከላል፡፡ ክርስትያኖች በመንፈሳዊ ሀሳብ መመላለስ እንጂ እንደ ዘፈን ያለውን ስጋዊ ስራ መስራት የለባቸውም፡፡ በመንፈስ ተመላለሱ፤ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ›› ተብሏልና፡፡ ገላ 5:21

➲ መ. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል ዘፋኝነትም ተከልክሏል፡፡

➣ ሐመር መጽሔት ይህን ሲያስረዳ ‹‹ዛሬ የአለም ሕዝብ የሚያዘወትረውን ዘፈን ሐዋርያት በትምህርታቸው ደጋግመውና አጥብቀው ተቃውመውታል ይላል (ሐመር 2ኛ ዓመት ቁ 4 ገጽ 27) በእርግጥም ሐዋርያት በዲድስቅልያ ‹‹አትኩኑ ዘፋንያነ››፤ ‹‹ዘፋኝ አትሁኑ›› ብለዋል፡፡ ዲድስ አን7
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ፡፡ በዘፈንና በስካር አይሁን›› ብሏል፡፡ ሮሜ 13፡13 ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ << በስካር እና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል፡፡›› ይለናል 1ኛ ጴጥ 4፡3

➣ በላይኛው አንቀጽ በሰፈረው የሮም ክታቡ ቅዱስ ጳውሎስ ዘፋኝነትን ከዝሙትና ከስካር ጋር አስተካክሎ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ‹‹በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፡፡ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፡፡›› በማለት ዘፋኝነትን የርኩሳንና የነውረኞች ተግባር አድርጎታል፡፡ 2ጴጥ 2፡13-15

➭ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን የዘፈን ሰዎች በሌላ ማንነታቸው ሲገልጻቸው ደግሞ ‹‹ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትን የማይተዉ ዓይኖች አሏቸው፡፡ የማይፀኑትንም ነፍሳት ያታልላሉ፡፡ መመኘት የተለመደ ልብ አላቸው፡፡ የተረገሙ ናቸው፡፡›› ይላል 2ጴጥ2፡13-15
መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ ‹‹ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል፡፡›› ይለናል፡፡ መጽ ሐዊ አን50

➨ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ ‹‹ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችኋለሁ›› በማለት ይማፀናል (ተግ ዘዮሐ አፈ 28)

ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ፀንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን፡፡ መጽ ሐዊ አን 12 ይህ የሐዊ ቃል ሐዋርያው ‹‹የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው፡፡ እርሱም ዝሙት .. ስካር፣ ዘፋኝነት እንደነዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› ማለት በምን ይለያያሉ

Share በማረግ ትውልዱን እንታደግ

ሞዐ ተዋህዶ ቻናል
566 viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:18:22 Watch ""ተጨንቀናል" | ዘማሪት ወርቅነሽ ኃይሉ Zemarit_Worknesh_Hailu |@Anasimos Tube" on YouTube


1.0K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 06:27:06 አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
@ANASIMOS_TUBE
@ANASIMOS_TUBE
@ANASIMOS_TUBE
958 viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 17:26:25 ➠ መድሃኒአለም ማለት የአለም ሁሉ መድሃኒት ማለት ነዉ
ስጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ለኛ ሲል ህይወቱን የሰጠ

፨ አሮንና ልጆቹን ....... ለክህነት የመረጠ
፨ ኤልያስን ....... በአዉሎ ነፋስ የነጠቀ
፨ እዮብን ....... በባእድ ሀገር ከፍ ከፍ ያደረገ
፨ ሎጥን ........ ከእሳት ያወጣ
፨ ለሳምሶን ........ ሀይልን የሰጠ
፨ አዛርያን አናንያን ሚሳኤልን ....... ከእሳት የታደገ
፨ ጥበብና ማስተዋልን ....... ለሰለሞን የሰጠ
፨ ያዕቆብን ....... በመንገዱ የጠበቀ እና የባረከ
፨ እስራኤልን ....... ከግብፅ ባርነት ያወጣ
፨ ለሙሴ ....... ጽላት የሰጠ
ለኪሩቤል ላይ የተቀመጠ ክብሩንም የገለጠ ስጦታዉ የማያልቅበት

➽ ቸሩ_መድሃኒአለም_ይክበር
_ይመስገን_አሜን /፫/
➪ መድኃኒአለም _የገዢዎች ሁሉ
➪ መድኃኒአለም ____ የነገስታት ሁሉ ንጉስ
➪ መድኃኒአለም ____ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ነዉ
ኃይሌን ጉልበቴን ታድሳለህ
ቀና ቀና እንድል ታደርጋለህ
መድኃኒአለም መድኃኒቴ

መ ____ መሃሪ ይቅር ባይ አምላክ
ድ ____ ድካሜን ተመልከት ስለዉ ተበርክኬ
ኃ ____ ኃያላት የማይችሉህ የኃያላን ኃያል
ነ ____ ነፍሴ ትልኃለች ጌታዬ ይረዳኛል
አ ____ አለምን ለማዳን መስቀል ላይ የዋለ
ለ ____ ለዘላለም ፍቅር ነህ ሁሌ የማትቀየር
ም ____ ምህረትህ የበዛ
➪የድንግል_ማርያም_ልጅ_ቸሩ_መድኃኒአለም_አንተ_ነ
ህ_አባቴ !!

ቸሩ መድኃኒአለም በያላቹሁበት ይጠብቃችሁ ወጥቶ ከመቅረት ከድንገተኛ አደጋ ይጠብቃችሁ አሜን/፫/
የሚያኖረን ሰዉ ሳይሆን የአለም መድኃኒት የሆነዉ ለእኛ ሲል የእሾህ አክሊል የደፈዉ ቸሩ መድኃኒአለም ነዉ።
ቸሩ መድኃኒአለም ሃገራችን ይጠብቅልን
የዲያብሌስ ስራ እጅግ ተስፋፍቶብን
የሰዉኛ ዘይቤዉ ከእኛ ዘንድ ጠፍቶብን
ምግባራችን ከፍቶ ትዛዝህን ሽረን
..... በበደል ጨቂተን

ዉስጣችን ሲያነባ ካንተ ተሰዉረን
ለሰዉ ልጅ ነዉና ደምህ የፈሰሰዉ
በምህረት እጆችህ እንባችን አብሰዉ
ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረ አሁንም ላለ ኋላም የሚኖር ስሙ የተመሰገን ይሁን አሜን(፫)

@ANASIMOS_TUBE
1.3K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 13:01:41 "Philosophy is a love of wisdom but, true wisdom is God. Therefore, the love of God is the true philosophy"

" ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት ነው፡፡ እውነተኛው ጥበብ ደግሞ እግዚአብሔር ነው ስለዚህ እውነተኛው ፍልስፍና እግዚአብሔርን ማፍቀር ነው፡፡"

John of Damascus

@anasimos_tube
1.8K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 06:59:10 አቤቱ ግሩም ምክርህን ትመክረኝ ዘንድ ዳግመኛ አይኖቼን ወደ አንተ እነሳለሁ በእንባም አለምንሃለሁ ሌሎች መሆን ያለባቸውን ሳውቅ እና ስናገር እኔ መሆን ያለብኝ እንደየጠፋኝ ለአንተ 'የታመኑልህ ወዳጆችህን' መምሰልን ፍፁም ደስ የሚያሰኝህን የትዕዛዝህን መንገድ መከተልን መሻትን ከልቤ አትሰውር። እንደ አለም ሀሳብ የሆነ ሕይወትን አትስጠኝ ። ይልቁኑም በአደባባዮችህ መጣልን አትንፈገኝ።

ኃጥዕ ወልድከ ተክለፃድቅ
3.8K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 21:19:46 “ጨዋነት ዝምታ ሳይሆን የሚናገሩትንና የሚናገሩበትን ቦታ ማወቅ ነው። ከንግግር የሚሻል ዝምታ እንዳለ ሁሉ ከዝምታ የሚሻልም ንግግር አለ። ሁሉም በቦታው ሲሆን ዝምታ ጌጥ ፣ ንግግር ወርቅ ይሆናል።”

ሞዐ ተዋህዶ
2.9K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 17:03:10
"እኛ የመነኮስነው ለፍትፍት እንጀራ አይደለም"

"የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ በላይ የቤተክርስቲያንን አቋም አጠናክሩ"

"ቤተክርስቲያን ሰው የላትም ሰው ሁኑላት የብረት አጥር ሁኑላት፤ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሁኑላት።"

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (1932-1982) የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በረከታቸው ይደርብን።
3.1K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 17:05:23 #ዕርገት
#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

የዛሬው በዓል ምን ይደንቅ! እነሆ ነገደ መላእክት ኹሉ ሲዘምሩ፣ አንዳንዶቹ ከኋላው ተከትለዉት፣ አንዳንዶቹ ከፊቱ ቀድመዉት፣ አንዳንዶቹ በዙሪያው ከብበዉት፣ ሌሎቹ ከሐዋርያት ጋር ኾነው፡- “እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ! ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል” ሲሏቸው እናያቸዋለንና፡፡

ብዙ ድንቅ ምልክቶችን ያደረገው ይህ ኢየሱስ ነው፡፡ በዚህ የጌታችን በዓል፣ በዚህ በዕለተ ዕርገት ቀድመን እንደ ተናገርን ዲያብሎስ አለቀሰ (አዘነ)፤ ምእመናን ግን ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ እነሆ አሁን ደስ የሚያሰኘው ምንጭ ፈለቀ፤ እነሆ አሁን አበቦች ፈኩ፡፡ የወይን ቅርንጫፎች ደረሱ፤ የወይራ ዛፎችም ጥዑም መዓዛቸውን ሰጡ፡፡ በለሶችም እሸት ፍሬያቸውን ለገሱ፡፡ ነፋሱም ሐመልማላትን እንደ ባሕር ጨዋታ እያወዛወዘ ነፈሰ፡፡ ኹሉም ከእኛ ጋራ በጌታችን ዕርገት ተድላ ደስታ አደረጉ፡፡ ስለዚህ፡- “አሕዛብ ኹላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር ዕልል በሉ፡፡ እግዚአብሔር በዕልልታ፣ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዓረገ” እያልን ወደ ላይ ወደ ሰማያት ላረገው ለጌታችን እንዘምር ዘንድ ከእኛ ጋር የክቡር ዳዊትን ቃለ መዝሙር አምጡ፡፡

እነሆ ጌታችን ወደ ሰማያት ዓረገ፤ ነገር ግን ከእኛ አልተለየም፡፡ የወደቀውን አዳም ያነሣው ዘንድ የወረደው እርሱ እነሆ ዛሬ ከሰማየ ሰማያት በላይ ዓረገ፡፡

ነቢያት በትንቢት መነጽር ያዩት እርሱን እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሐዋርያትም የበሉት ከእርሱ ጋር እንጂ ከሌላ ጋር አይደለም፡፡ በአባቱ ዕቅፍ የነበረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በጲላጦስ የተፈረደበትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በመስቀል ላይ በሚስማር የተቸነከረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በዘባነ ኪሩብ ላይ የነበረውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ጻድቁ ዮሴፍ በጨርቅ የጠቀለለው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ በእጁ መዳፍ ፍጥረታትን የያዘውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ በመቃብር ያደረው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሱራፌል ያመሰገኑትም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም። በአባቱ ቀኝ የተቀመጠው እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው የኾነውም እርሱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

እግዚአብሔር በዕልልታ ዓረገ፡፡ አምላክ በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡ ከዘለዓለም አንሥቶ ፈጣሪ የኾነው፣ ኹሉንም ነገር ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው፣ አዳምን የሠራው፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው፣ ደስ ያሰኘውን ሄኖክን ወደ ሕይወት ያሸጋገረው፣ ኖኅን ከዓለም ጋር የጠበቀው፣ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር የጠራው፣ ይስሐቅን የነገረ መስቀል ምሥጢር ምልክት እንዲኾን ያደረገው፣ ያዕቆብን የዐሥራ ኹለቱ አዕማድ ሥር እንዲኾን ያደረገው፣ ለኢዮብ ትዕግሥትን የሰጠው፣ ሙሴን የሕዝቡ መሪ እንዲኾን አድርጎ የሾመው፣ ሳሙኤልን ከእናቱ ማኅፀን አንሥቶ በትንቢት የሞላው፣ ከነቢያት መካከል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ የቀባው፣ ለሰሎሞን ጥበብን የሰጠው፣ ኤልያስን በእሳት ሰረገላ የወሰደው፣ ነቢያት መጻእያትን እንዲያዩ ያደረጋቸው፣ ለሐዋሪያት ሀብተ ፈውስን የሰጣቸው፥ “አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ” ብሎም አሰምቶ የነገራቸው እርሱ ዛሬ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ዓረገ፡፡

ወደ ሰማያት በዕልልታ ያረገው፣ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው የክብር ጌታ ይህ ነው፡፡ መላእክትና አለቆች ኃይላትም ይገዙለታል፡፡ ቁርጥ ልመናችንን የሚቀበል፣ ወደረኞቻችንን ድል እንድንነሣቸው ኃይልን የሚሰጠንም እርሱ ነው፡፡ “እባቡን ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ እነሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ” እንዳለ በክፉ መናፍስት ኹሉ ሥልጣን ያለው እርሱ ነው፡፡

ነውር ነቀፋ የሌለብህ ንጹሃ ባሕርይ ሆይ! በነፍስ፣ በሥጋና በመንፈስ ጠብቀን፡፡ ይህን በዓል እናከብረው ዘንድ የሰበሰብከን የኹሉም አምላክ የኾንህ ጌታችን ሆይ ! በጽድቅ ፍሬ የተሞላን አድርገን፡፡ ለአንተም ከባሕርይ አባትህ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር፣ ኃይልና ስግደት ኹሉ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ይገባል፥ አሜን፡፡

(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
2.7K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 10:35:01 + ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 23 2014
አዲስ አበባ

ፎቶ :- ኢያሪኮ "የዘኬዎስ ዛፍ" የነበረበት ሥፍራ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

═══◉❖◉═══
✥• @Anasimos_Tube •✥
✥• @Anasimos_Tube •✥
═══════◉❖◉════════
2.3K viewsᕼᗩᏆᏞᗴ, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ