2022-01-09 17:27:46
ውሃ ውስጥ የገባን ሞባይል ስልክ ማስተካከያ መንገዶች
አንዳንድ ስልኮች ውሃን በቀላሉ እንዳያሰርጉ ተደርገው የተዘጋጁ ቢሆንም፥ ከውሃው በቶሎ ካላወጣናቸው ውሃው ወደ ስልኩ የውስጠኛ ክፍል ድረስ ዘልቆ ሊገባ ይችላል ።
በየትኛውም አጋጣሚ የሞባይል ስልክዎ ውሃ ውስጥ ቢወድቅብዎ ፈጥኖ ከውሃው ውስጥ ማውጣት ፦ ስልኩ በውሃ ውስጥ በቆየ ቁጥር የሚደርስበት ጉዳት እየከፋ ይመጣል።
በመቀጠል
1• ስልኩን ፈጥኖ መዝጋት
2• ከስልኩ መለየት የሚችሉ ለምሳሌ ባትሪውን እና ሲም ካርዱን ፈጥኖ ማውጣት።
በሞባይል ስልኩ ውስጥ እርጥበት ስለሚኖር ይህ ካልተወገደ ስልኩ መስራት አይችልምና፥ እርጥበቱን ለማጥፋት ፦
1• በደረቅ እና ነፋስ ሊያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ፣
2• ከ100 እስከ 110 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት እንዲያገኝ በሚችል ስፍራ ማስቀመጥ።
ስልኩ የአፕል ምርት ከሆነ ደግሞ፥ ኩባንያው እስከ 115 ዲግሪ ፋራናይት ሙቀት ሰጥቶ እርጥበቱን ማስወገድ ይቻላል።
የሞባይል ስልኩ እስከሚደርቅ ድረስ ጥቂት ቀናት ማቆየት ይኖርብናል ።
ስልኩን በሩዝ ውስጥ ማስቀመጥ ሌላኛው አማራጭ ነው።
ለዚህም ውሃ ውስጥ የወደቀውን የሞባይል ስልክ በጥሬ ሩዝ ውስጥ በመክተት ማቆየት።
ይህ ደግሞ ሩዝ በተፈጥሮው እርጥበት የመሳብ ባህሪ ስላለው በስልኩ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመምጠጥ እንዲደርቅ ያደርገዋል።
T.W
@Amesi_Tech
@Amesi_Apps
@Amesi_Tech_Group
@Amesi_Tech_Bot
▬▬▬▬▬▬ sʜᴀʀᴇ ▬▬▬▬▬▬
2.1K views14:27