Get Mystery Box with random crypto!

በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ጥቃት መሆኑን | ᴀᴍᴇsɪ ᴛᴇᴄʜ ✅

በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ጥቃት መሆኑን የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።

በዋናነት ለጥቃቱ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀመጡት ዋና ዳይሬክተሩ አንዱ የዋልታ የፌስቡክ ገጽ ዋና አድሚን ሃገር ዉስጥ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሁለተኛዉ ምክንያት ደግሞ የሚዲያዉን የፌስቡክ አካዉንት አክሰስ እንዲያደርጉ ሃላፊነት በወሰዱ አካላት ስህተት በተለይም አንዱ የፌስቡክ ኤዲተር የተላከለትን አጥፊ ተልእኮ ያለዉን ሊንክ ያለ ጥንቃቄ በመክፈት ለመረጃ ጥቃቱ መፈጸም ሚና እንደነበረዉ ተናግረዋል።

ከ7 ቀናት በፊት የፌስቡክ ገጹ የተጠለፈበት ዋልታ እስካሁን ማስተካከል አልተቻለም። አሁን ላይ ገጹ በጊዜያዊነት ከፌስቡክ ገጽ ላይ እንዲሰወር ተደርጓል።

tikivah

   |  - @Amesi_Tech - |