Get Mystery Box with random crypto!

'ናፊባ' ክፍል ~ ሠማንያ ሠባት በአምባዬ ጌታነህ @Adwa_1888 'መኖር የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ድ | የዮቶር ልጅ - አምባዬ ጌታነህ

"ናፊባ"
ክፍል ~ ሠማንያ ሠባት
በአምባዬ ጌታነህ @Adwa_1888
"መኖር የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ድርሻው ብቻም ሳይሆን
ኃሴት እንዲያገኝ የሚያደርገው እጣ ፈንታው ነው።
ረሀብና በሽታ ብቻ ሰውን አይገለውም።
ቤት የሌላቸው በርካታ ሰዎች ቢኖሩም አንተ ግን....."
የምትል ቆፍጣና ሀሳብ ከያዘች የአራት መስመር ሀሳብ ጋር ተሰናኝቶ ልቡን በአንዳች ስሜት እየነጠቀ ይረብሸው ጀመር።ደጋግሞ አነበበው ነገር ግን ወደውስጡ ሊነግረው የሚችል ተዛማጅ ትርጉም አጣ። የሚተነተኑ ሳይሆን የሚያጠራጥሩም ሳይሆን የሚታመኑ፣ የሚያሻሙ ሳይሆን ግልፅ የሆኑ ሀሳቦች የተቀመጡበት ነው።" መኖር የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ድርሻው ብቻም ሳይሆን ኃሴት እንዲያገኝ የሚያደርገው እጣፈንታው ነው።ይሄ ምን ማለት ነው? ምን አይነት ሀሳብ ነው። ትንሽ እንኳ የሚያሻማ ቢሆን ችግር የለውም ነበር ነገር ግን ምን የሚሉት አገላለፅ ነው? አለ ሸዋንግዛው ምሬት ና ስልቹነት ፊቱ ላይ በሚገባ እየተቀየረ።ተሕሚድ የሸዋንግዛውን ሁኔታ በትዕግሥት እየተመለከተ "ይቅርታና በድጋሚ አሁንም ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንክ ምንም ልትረዳው አትችልም በቅድሚያ አእምሮህን ነፃ ማድረግ ይጠበቅብሀል!"የሚል ምክረ ሀሳብ ለመጨረሻ ጊዜ አቀረበለት።
**********
"የሸዋንግዛው መኖሪያ ቤት ብረት በለበሱ ሰዎች ተከቧል።አሁን ላይ ባለን መረጃ እርሱና ተሕሚድ በመኖሪያ ቤት ውስጥ እንዳሉ ናቸው። የእኛ ሀይሎች ከመንግስት ሀይል ጋር ሲነፃፀር ምንም ነው። ስለዚህ ሌላ መንገድ ስለሌለ አባላቶቻችንን እንዲመለሱ አዘዝኳቸው" አለ በሀፍረት አንገቱን እያቀረቀረ። "እና እንደ ጀብድ አድርገህ ታወራኛለህ።ብቻውን እንዲጋፈጥ አድርገነዋል ማለት እኮ ነው።የሆነ ነገር እንዲያደርጉ እንኳ ማዘዝ ነበረብህ!" "ለምሳሌ ምን ማድረግ ነበረብኝ? እኔ እኮ አንተን ሳላማክርህ ብዬ ነው።ያው ባለማወቅ ስህተት እንዳልፈፅም ብዬ ነው እንጅ። እዛው አካባቢ ሆነው ኢንስፔክተርን የከበቡትን የመንግስት ቅልብ ምልምሎች ላይ ከእርቀት የተኩስ ድምፅ በማሰማት አካባቢው ላይ አንዳች ነገር እንደተፈጠረ ማመላከትና ለማንቃት አስቤ ነበር። ግን በዚህ ጊዜ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ወይ መሳሪያ ይዞ ሊወጣ ይችላል። ወይም ደግሞ ለፖሊስ መኮንኖቹ ደውሎ በገዛ ፈቃዱ ቀለበት ውስጥ ሊገባ ይችላል ብዬ ስላሰብኩ ነው!" በማለት ጥርጣሬዎቹን በሙሉ አንድ በአንድ ዝርግፍ አድርጎ ተናገረ።"በርግጥ ቸኩለህ ውሳኔ አለመወሰንህ ጥሩ ነው። በል ለማንኛውም ለልጆቹ ደውልና በቅርብ እርቀት ሆነው ምን ያህል ፖሊስ እንደከበበው በቁጥር ደረጃ እንዲያጣሩ አድርግ። እኔ ደግሞ ለኢንስፔክተር ሸዋንግዛው በመደወል ያለውን ነገር አሳውቄው ቅድሚያ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ላድርገው።
"ሀሎ ጤና ይስጥልኝ" "አብሮ ይስጥልኝ ማን ልበል?" አለ ሸዋንግዛው "ይቅርታ ማንነቴን እንኳ አታውቀውም ግን አንድ መረጃ ልነግርህ ነው። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው በአሁኑ ስአት ቤትህ ከመንግስት በተሰጣቸው አንተን የማፈን ልዩ ኦፕሬሽን ከበባ ውስጥ ነህ! ምን አልባት ይሄን ስልህ ልትገረም ትችላለህ። ወይም ደግሞ እኔን ላታምነኝ ትችላለህ። ግን በእርጋታ ቀስ ብለህ በመውጣት መመልከት ትችላለህ! ለጊዜው እኛ እንረዳሀለን። ነገር ግን በተዘዋዋሪ እንጅ በቀጥታ አይደለም። ልጆችህንና የወንድምህን ልጅ በአስተማማኝ ቦታ እናስቀምጣቸዋለን።ይሄን የምናደርገው እንደነገርኩህ አንተን ለመርዳት እንጅ ለማስፈራራት አይደለም።እርግጠኛ እንድትሆን ያህል ራሴን ደብቄ የምስጢር ጥቅሎችን የማስቀምጥልህ ሰው ነኝ። ካንተ ጎን የምሆንበት ምክንያት እንጅ ከአንተ ተቃራኒ የምሆንበት ምክንያት እንደሌለኝ በመረዳት ሙሉ ትኩረትህን ከዚህ ከበባ ራስህንና ተሕሚድን የምታወጣበትን ሀሳብ አፍልቅ" ብሎት ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋው። ኢንስፔክተር ሸዋግግዛውጰየሰው ልጅ የመጨረሻ ደረጃ የሚባለውን ግራ መጋባትን በቅፅበት አስተናገደ። ሁሉም የሰማው ነገር እንግዳ ሆነበተ። ለአመታት በታማኝነት ሲያገለግለበት የነበረው ስራው ተጠያቂ እንዳደረገው ለማመን ተቸገረ። ለብዙ ጊዜ ወደስልጣኑ እንዲመለስ ግፊት ሲያደርግለት የነበረው መንግስት አሁን የሱ ጠላት መሆኑን ከማያውቀው ሰው እየሰማ ነው። "ምንድነው ያለህ ኢንስፔክተር"ተሕሚድ የተለመደውን ጥያቄ ሰነዘረ። ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ዝም።ምንም አይነት መልስ ሳይመልስለት ዝም ካለ በኋላ ብድግ አለና ቀስ አድርጎ በሩን ከፍቶ ወደ ግቢው በር አጮልቆ ያማትር ጀመር። ጊቢው ፀጥረጭ ብሏል። በእርጋታ ወደ ዋናው በር ጠጋ ብሎ በቀዳዳ ሲመለከት በርካታ ልዩ ፖሊሶች መሳሪያቸውን በተጠንቀቅ ይዘው ፊታቸውን ወደ ኢንስፔክተር ሸዋንግዛው ቤት መግቢያ በር ተኮልኩለዋል። ይሄኔ ነበር የሰማው ነገር እውን መሆኑን ያረጋገጠው።በፍጥነት ወደ ቤቱ ተመልሶ ገባና አንዳች መውጫ ዘዴ ያስብ ጀመር። ለረጅም ደቂቃ ካሰበ በኋላ ለስራ ባልደረባው ለሆነ አንደ የወንጀል ምርመራ ቡድን አባል ለሆነው ወዳጁ ለኮማንደር በርናባስ ይገዙ ደወለለት። በእርጋታና በዝግታ እያንሾካሾከ " እየውልህ በርና ቀስ ብለህ አናግረኝ።እኔ መሆኔን ለማንም እንዳትናገር ዝም ብለህ የምልህን አድምጠኝ በዚህ ስአት ከአንተ ውጪ ማንንም ላምን አልችልም። ተከብቢያለሁ። የቻልከውን ነገር አድርግ ግን ለማንም ሰው እንዳትናገር። ከቻልክ የተወሰኑ የእኛን ሀይሎች ይዘህ መጥተህ የሆነ አቅጣጫ ለማስቀየር እና ሀሳባቸውን ለመስረቅ ሞክር።"የሚል ሀሳብም ተማፅዕኖም የበዛበት የቃላት ድርድር እንደ በረዶ አወረደበት።
"ኧረ እባክህ ኢንስፔክተር የተፈጠረውን ነገር ንገረኝ በጭንቀት ገደልከኝኮ"አለ ተሕሚድ የሚጠይቀው ጥያቄ ምላሽ ሲያጣና ጭንቀቱ እየበረታ ሲሄድ "አሁን ምንም ልልህ አልችልም።ተከበናል።" "ምን?" አለ ተሕሚድ ሳያስበው ጮክ ብሎ "በቃ በጠዋቱ ድርጊቴ የተቆጡት ባለስልጣናት እኔ እንድታፈን ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።" "እና አሁን ምንድነው የምናደርገው?" ተሕሚድ ራሱን በሁለት እጁ እንደያዘ ጥያቄውን ሰነዘረ። "ምን እናደርጋለን ብለህ ነው። ነፃ የሚያወጣንን ፈጣሪ መለማመን ነዋ! ውጪ ላይ በተጠንቀቅ ቆመዋል። እስኪ ከሴራው ላይ ካልተካፈለ ጓደኛዬን ማለቴ የስራ ባሌደረባዬን የሆነች ትንሽ የማርያም መንገድ እንዲከፍትልን ጠይቄዋለሁ። ግን አማራጭ ስለሌለኝ ነው እንጅ ትክክለኛ ሰው አይደለም የጠየኩት"አለ ሸዋንግዛው በኮማንደር በርናባስ ይገዙ እምነት እንደሌለው ለተሕሚድም በሚገባ እያስረገጠለት።ተሕሚድ ምን ማድረግ እንዳለበት ይቅርና ምን ማሰብ እኖዳለበት ሁሉ ጠፋው። አንዳች ምስጢር ለማግኘት ከማነፍነፍ በመውጣት የራሳቸውን ነፍስ ስለማትረፍ ይጨነቁ ጀመር። ሕይወት ልክ እንደዚህ ገጠመኝ ነች። ብዙዎች በብዙ ነገር ይመስሏታል። ግን ከምንም በላይ በተላያዩ ድራማቲክ በሆኑ ገፅታዎች የተላበሰት ሰርክ አዲስ ትዕይንት ነች።

@amba88
@amba88