2022-08-28 21:53:37
┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
". #ፊትና ".
✎ፀሐፊ፦ ፎዝያ ፈይሳ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
. በ Islamic al faruq የተዘጋጀ .
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚
{ክፍል 13}
""ወደ አባቴ ቤት ሄድኩኝ አባቴ ቤት ስገባ ግን የማየዉን ማመን አቃተኝ ሳሎን ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣለች ገና ከመግባሄ ሀይ ጋይስ ብላ እንደምታቀኝ ሰዉ ተነስታ አጠገቤ ደረሰችና ልታቅፈኝ እጇን ዘረጋች እኔም ይቅርታ ሀጂ ነብይ ሴት አልጨብጥም ብያት ወደ አባዬ ክፍል አመራሁ አባዬ ሁሌ የራሱ ቤታችን ዉስጥ ባለዉ የራሱ ቢሮ ነዉ ቁርሱን የሚበላዉ ግፋ ቢል እስከ ዙሁር ሰአት ይቀመጣል እናም እኔ በቀጥታ ወደ ፎቅ በመዉጣት አባዬ ጋር አንኳኩቼ ገባሁ <<አሰላም አለይኩም አቡ
<ወአሌይኩም ወሰላም የኔ ልጅ መጣህ
<<አዎ እኔ ምልህ አባቴ ሳሎን ያለችዋ ሴት እዚ ለምን መጣች ምን ትሰራለች
<አይ ልጄ ወንድምህን አሞላቀን አሳደግነዉና ይህዉ ክርስቲያን ሴት አግብቶ አሰልማለሁ እያለ ነዉ እሷ ደሞ ያዉ ስርአት ቲኒሽ ይጎላታል
<<አባዬ የልጅህ ስህተት በጣም በዛኮ እንደዉም አንተ ዝም በል እኔዉ ከቤት አባራታለሁ ብዬ ስንደረደር ወደ ታች ወረድኩና የተቀመጠችበትን ስመለከት የለችም ወደ ወንድሜ መኝታ ክፍል ስገባ የለችም <አባዬ እኔን እየተከተለ ተዉ ባክህ ተረጋግተን እናዉራበት
<<አባዬ ምንም የምናወራዉ ነገር የለም አባቴ የልጅህ ስህተት የሰዉን ሂወት አደጋ ላይ እየጣለ ነዉ ብዬ ዉጪ መናፈሻዉን ሳየዉ ቁጭ ብላ ስልክ ታወራለች ሄድኩና ይቅርታ ስምሽ ማነዉ
<ብሌን
<<አድናን ምንሽ ነዉ
<ባሌ
<<ተጋባቹንዴ
<ያዉ የቀረን ሰርግ ብቻ ነዉ እኛ ከተጣመርን ቆይተናል
<<ምን ማለት ነዉ ይሄ ቆይ ሴት አይደለሽንዴ ክብርሽን አትጠብቂም ደሞ ካለ ጋብቻ እንዴት አታፍሩም
<ዋት ምን ማለት ነዉ ይሄ እኛ ከተዋደድን አይበቃንምንዴ በዛ ላይ እንዋደዳለን ይገባሀል ብላ አፈጠጠች ባልፈልግም እጇን እየጎተትኩ ከጊቢ ላስወታት በሀይል እጎትታት ጀመር አዎ መጎተቴ ትክክል ነዉ የሂባ የዛች የሚስኪኗ እህቴ ሂወት የተበላሸዉ በሷ የተነሳ ነዉ ወንድሜን ይቺ ልጅ ባታጠመዉ ኖሮ እንደዚህ ሊጎዳት አይችልም ብቻ ከበሩ ስደርስ ሰራተኛችንን የሷን ልብስ ከአድናን ክፍል እንድታመጣ አድርጌ ከጊቢ አሶጣዋት አባቴ በኔ ዉሳኔ አልተቃወመም እሷን አሶጥቼ በሩን በሀይል ወረወርኩትና አባዬ እኔን ልታጣኝ ካልፈለክ ይቺ ልጅ እዚ እንዳትገባ የገባች ጊዜ ግን አጠገብህ አልደርስም ብዬ አጠገቡ ከመቆሜ በሩ በሀይል ተንኳኳ ዘበኛዉ ሊከፍተዉ ሲል አይ ተወዉ ብዬ በሩን ስከት ወንድሜ ነዉ
<<እሺ ጎሮምሳዉ
<ትሰማኛለህ ሚስቴን የማባረር መፍት የለህም ገባህ ይሄ የአባቴ ቤት ነዉ
<<ብቻህን መግባት መፍትህ ነዉ አለበለዚያ ግን በፍፁም ይቺን ሴት ይዘህ አትገባም ገባህ
<እንደሳ ከሆነ አንተ ወንድሜ አይደለህም ብሎ ወደቤት ገባ ከደይቃዎች ቡሀላ ልብሱን በሻንጣ ሞልቶ ወጣ አባዬ ተመለስ ቢለዉም እናንተ ቤተሰቦቼ አይደላቹሁም ብሎ ወጣ እኔም አባዬን ፈጠን ብዬ ወደ ባንክ ወሰድኩትና ቡኩን እንዲያሳግድበት ነገርኩት አባዬም አላሳፈረኝም አሳገደበት
<<አባዬ በጣም ነዉ የማመሰግነዉ አሁን እጁ ላይ ያለዉ ገንዘብ ሲያልቅ ይመጣልሀል ብዬዉ ቲኒሽ አወራንና እኔ ወደ ቤት መጓዝ ጀመርኩ።
""ሂባዬ በሩን ክፈቺ እስቲ
<እሺ እከፍታለሁ ብላ እህቴ በሩ ጋር ብዙ ቆየች እኔም የመቆየቷ ሚስጥር ስላልገባኝ ወደ በሩ ሄጄ ከዋላዋ ቆምኩና እህቴ ማነዉ የመጣዉ ብዬ እሷ ዞር እስክትል ጠብቄ የእህቴ ቦታ ቆምኩኝ የቆመችዉ በጣም ቆንጆ ሴት ነበረች ፈገግ ብዬ አሰላም አለይኩም አልኳት
<ሰላም ሁስኒያ ማለት አንቺ ነሽ
<<አዎ እኔ ነኝ እና አንቺን ማን ልበል
<ፈልጌሽ ነበር
<<እሺ ወደ ዉስጥ ትገቢ ብዬ አስገባዋት ጊቢ ገብታ በጣም አንገቷ እስኪታመም ተዟዙራ ትመለከተዉ ጀመር እናም ወደ ቤት እንድትገባ ስጋብዛት
<ኖኖኖ አልገባም ከቻልሽ እዚህ እንቀመጥና እናዉራ ብላ ዉጪ የተሰራ መቀመጫ ነበርና ጊቢ ዉስጥ ተቀምጠን ሂባ ሻይ እንድታመጣ ነግሬአት ተስተካክላ እየተቀመጠች ይገርምሻል ከሀቢል ጋር የመረጣችሁት ቦታ አሪፍ ነዉ ሰፊ ግቢም አለሽ እድለኛ ነሽ ለእንዳንቺ አይነቷ ሰራተኛ ሊያደርገዉ እንደሚችል አዉቅ ነበር ግን ታዉቂያለሽ
<<ማለት ምኑን
<በኔና በሀቢል መሀል ገብተሽ እንደሰመጥሽ
<<አልገባኝም
<ይወልሾ ሁስኒ ሀቢል የኔ የብቻዬ ነበር ነገር ግን አንቺ መተሽ ለየሽን ካላመንሽ ፎቶ ላሳይሽ ብላ በስልኳ ከሀቢል ጋር የተነሱትን ብዙ ፎቶዎችን አሳየችኝ እረ ጉዴ ብዙ ነዉ ከነ በሀራም እየተሳሳሙም የተነሱት ነበር ምንም ሳልል ስልኳን መለስኩላት
ለማንኛዉም ሙሪዳ እባላለሁ ብላኝ ስላስተናገድሽኝ አመሰግናለሁ ብላ ከጊቢዉ ለቃ ወጣች።
"""ኡፍ ዛሬ ደሞ ምን ሆነዉ ነዉ ብዬ ከመኪናዬ ወርጄ በሩን ባንኳኳ የሚከፍት የለም ግራ ገባኝ ትርፍ የጊቢም የቤትም ቁልፍ ስለነበረኝ ከፍቼ ገባሁ ወደሳሎንም ስገባ ማንም የለም ለሁስኒ ስደዉል አታነሳም እንደምንም ብዬ ወደ መኝታ ክፍል ልብስ ለመቀየር ገብቼ ቁምሳጥኑን ለመክፈት ወደ አልጋዉ ስሄድ ነጭ ወረቀት ተቀምጧል ሲመስለኝ መልእክት ያለዉ ይመስላል ስከፍተዉ__
ትሰማኛለህ አንተም ከወንድም የሚለይህ ምንም ነገር የለም እኔ የምትሻሻልና ግልፅ መስለህኝ ነበር ነገር ግን ሀቢል አንተም ልቤን ሰበርከዉ ሀቢል በቃ ከሂወቴ ዉጣ እህቴ በወንድምህ እኔ ደሞ በአንተ የተነሳ ሂወቴ ተመሰቃቀለ በቃ ተወኝና ከሙሪዳ ጋር ሂወትህን ቀጥል። የሚል አጠር ያለ ፅሁፍ ነበር ገባኝ በቃ ሄጄ ማስረዳት ስለሚኖርብኝ ብዬ በቀጥታ ወደ ሁስኒ ቤት አመራሁ ነገር ግን ቤት ሂባ ና ኡሚም አቢም አሉ ነገር ግን ሁስኒያ አልመጣችም አሉኝ ስደዉልላት ከነ ስልኳን አጠፋችዉ
በጣም ጨነቀኝ ብቻ ወደ ቤት ስሄድ ሙሪዳ በሬ ላይ ቆማ አየዋት በጣም እራሴን መቆጣጠር እየተሳነኝ መጣ ከመኪናዬ እንደምንም ወርጄ ሙሪዳ አጠገብ ሄጄ ቆምኩኝ እሷ እንደለመደችዉ ሰራሁልህ እያለች የፌዝ ሳቅ ትስቅ ጀመር ምንም ሳላወራ አንገቷን ከግንብ ጋር አጣብቄ አነኳት ልታስለቅቀኝ ብትሞክርም አልቻለችም ሰፈራችን ጭር ያለ ስለሆነ ማንም አላየኝም እኔ ግን ከሰከንድ ሰከንድ በሀይል እያነኳት መጣሁና ትንፋሿ እየተቋራረጠ በስተመጨረሻ እጄን ለማስለቀቅ መሞከሯን ትታ ፀጥ አለች.....
ክፍል አስራ አራት ይቀጥላል
https://t.me/Alfaruq_islamic
https://t.me/Alfaruq_islamic
278 viewsرب ٱشرح لي صدري ويسر لي أمري , 18:53