┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ ". #ፊትና ". ✎ፀሐፊ፦ ፎዝያ ፈይሳ ┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛ ┎━─━─━─━─━─━─━─━ . በ al faruq Islamic የተዘጋጀ . . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ┖━─━─━─━─━─━─━─━─━ {ክፍል 11} "አይ ልጄ ሀቢል ሁሉምኮ እንዳሰብነዉ ቀላል አይደለም ይቺ ልጅ ላይ የነበረን ተስፋ በጣም ትልቅም ነበር ልጄ ከመንገድ በእብደት አሰናከሉብኝ እንጂ ብላ እናቴ ምርር ብላ አለቀሰች ሀቢል አልቻለም ኡሚን ይዟት በጣም አለቀሰና እኔ ሁለቱንም አባበልኳቸዉ ሀቢልም በድጋሚ ወደ እህቴ ጋር ገባና ብዙ ቆየ እኔ ወደ ሀቢል ጋር ስሄድ እሱ ቁጭ ብሎ ቁረአን እየቀራላት እሷ ደሞ አንገቷን ደፍታ አሰየማትዉ ነበር ብቻ አልሀምዱሊላህ ዉስጤን ሲረጋጋ ይሰማኝ ጀመር ቀናቱ እየሄደ ሀቢልም ስራዉን ትቶ ወደ እኛቤት አብረን ከገባን አስራ አምስት ቀን ሆነን ሀቢል ሁሌ ከሱቢሂ እስከ እረፋድ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ለሂባዬ ቁረአን እየቀራ እሷ እንደድሮ የምታሳየዉን ባህሪ ተወች እናም እሱ እንደ ታላቅ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ማሟላት ጀመረና በስተመጨረሻም የስነልቦና ሀኪም ጋር ህክምናዋን እንድትከታተል አደረገ ከተጋባን አንድ ወር ከ20 ቀን ቢሆነንም ግን ሀቢል ግማሹን ቀን እኛ ቤት ነዉ ሳይሰላች በፍቅር የኖረዉ አሁን እሱም የሚፈልገዉ ነጥብ ላይ ስለደረሰ ወደ ቤታችን ተመለስን አልሀምዱሊላህ። ""ዛሬ ሀሱንም እህቴንም የሀቢልንም አባት እና የእኔ አባትና እናትንም ለእራት ጋብዘናቸዉ እኔም ባሌም ሽር ጉድ እያልን በመሀል እህቴ ስራ ይከብዳታል ብላ ስላሰበች ከሁሉም ቀድማ እቤት መጣችና የሚሰራራ መፈለግ ጀመረች ከሀቢል ጋርም በጣም እንደ ታላቅና ታናሽ እየተቀራረቡ ስለነበር ደስተኞች ሆነዉ ከኔ ጋር እየተፎጋገሩ ስራ እየሰሩ ነዉ ደስ የሚለዉ ምሽት ደረሰና ሀሱ መጣ ያዉ ሀሱ እህቴን የተወሰነ ተመላልሶ እየጠየቃት ስለነበር አዲስ ሰዉ አልሆነባትም አልሆነችበትም ገብቶ እየተጫወተ ግን ሀቢል የተወሰነ እኔን ስራ ሊያግዘኝ ተነሳ። ""አልሀምዱሊላህ ሂወት ደስ ከማለቷ በዘለለ የኔ ሚስትም እህቷም ደስታቸዉ ተመልሷል በነገራችን ላይ የሂባን ጉዳይ አረሳሁትም ልጁን በሆነ መንገድ እስከማገኘዉ በጣም ነዉ የጓጓሁት ምክንያቱም ሁስኒ ከልጁ ዉጪ ሰዉን ማፍቀር እንደማትችል እራሷን አሳምናዋለች ብቻ አለህ ገር ቢያረገዉ ሂባን ከሀሱ ጋር ቢጋቡ ብዬ አስቤ ነበር ብቻ አልሀምዱሊላህ።