Get Mystery Box with random crypto!

. ▷ ወንጌል ◁ . ተከታታይ ልበ-ወለድ Written by | Agape-True Love

. ▷ ወንጌል ◁
. ተከታታይ ልበ-ወለድ

Written by Bethlehem Dejene

. #ክፍል_3
- - - - - - - - - - - - - - - -- - - - - -
➟በሩንም ከፍታ ስታይ ማንም የለም፡፡ "ጆሮዬ ነው ማለት ነው"? ብላ ንግግሯን ቀጠለች " እናም ወንጌል ከዚ በሇላ ትልቅ እንደሆንሽ ስለሚሰማኝ ዛሬ ትልቁን ስጦታሽን ሰጥሻለሁ፡፡ ብላ በነጭ ስጦታ ወረቀት የተጠቀለለውን ስጦታ ሰጠቻት ወንጌልም ደስ ብሏት ተቀበለች፡፡ ሁሉም የተለያዩ ስጦታ ሰጧት ኬክ ቆረሰች፡፡

የሚያምርም የልደት ጊዜ ካሳለፉ በሇላ ጓደኞቿ ወደ ቤታቸው አመሩ። ወንጌልም "እማ ደና "ደሪ ብላ ስጦታዎቿን ይዛ ወደ ክፍሏ አመራች፡፡ ወንጌል የመስታወት ፍቅር አለባት! ከዚ ፍቅሯ የተነሳ ልብሷን ስትቀይር ሳይቀር መስታወት እያየች ነው።ይሄንንም የምታረገው ብዙ ጊዜ የክፍሏን መጋረጃ ከፍታ በመስኮቷ መስታወት ነው። እንደለመደችው የመስኮቷን መስታወት እያየች ልብሷን ስታወልቅ ክፍሏ የበራው መብራት ከውጭ ወደ ውስጥ ያሳይ ነበር፡፡ ናኦድ ማታ ማታ በክዋክብት ድምቀት ታግዞ የማንበብ ልማድ አለው፡፡ ቤታቸው ከነወንጌል ቤት ጎን ነው፡፡ የነ ወንጌል ቤት ባለ 2 ፎቅ ስለሆነ የነ ወንጌልን ቤት ማየት የሚፈልግ ሰው እነናኦድ ጊቢ ሆኖ ልይ ቢል ሁሉም ነገር ይታያል፡፡

ናኦድ ከናቱጋ ጅማ ነበር ሚኖረው ጅማን ትቶ ከመጣና የዩኒቨርስቲ ትምርቱን ከጀመረ 2 አመታት ተቆጥረዋል እናቱም ያላንተ ማንም የለኝም ብቸኝነት ሊገለኝ ነው ብላ አሳምናው ጅማ ያለውን ቤቷን ሸጣ ናኦድጋ መታ አሁን የሚኖርበትን ቤት ገዛች ግን አዲሱ ቤቷ ብዙም አልቆየችም ምንም ግልፅ ሳታረግለት ይሄ ጥሩ እድል አይለፈኝ ብላ አሜሪካ ሄደች ናኦድ እናቱ ከሄደች ጀምሮ ብቸኝነቱን ሊረሳ ሚሞክረው በመፃፎቹ አማካኝነት ነው የዛን ቀንም እንደለመደው መፃፉን ይዞ ከቤት ሲወጣ ድንገት ወደ ወንጌል ክፍል መስኮት አነጣጠረ የወንጌል ክፍልም ፎቁ ላይ ስለሆነ በደንብ ትታይ ነበር ናኦድም በወንጌል ውበት ተገረመ ሲያያት ደስ አለችው በፍጥነት ወደ መስኮቱ ተጠጋ..........

ይቀጥላል!

@agapetruelove
@agapetruelove