Get Mystery Box with random crypto!

. ▷ ወንጌል ◁ . ተከታታይ ልበ-ወለድ Written by | Agape-True Love

. ▷ ወንጌል ◁
. ተከታታይ ልበ-ወለድ

Written by Bethlehem Dejene

. #ክፍል_4
- - - - - - - - - - - - - - - -- - - - - -
➟ይህ ሁሉ ሲሆን ወንጌል አላስተዋለችም ግን ናኦድ እየተሰናከለባት ነበር ልብሷንም ቀይራ እንደጨረሰች የመስኮቷን መጋረጃ ዘጋችው፡፡ ናኦድ ተበሳጨና እዛው ቁጭ ብሎ መፃፉን ማንበብ ቀጠለ፡፡ ወንጌልም ስጦታዎቿን መክፈት ጀመረች፡፡

ቸኮሌት፣መፃፍ፣የፀጉርጌጥ፣ .....በስተመጨረሻም የመሰረትን ስጦታ ስትከፍተው ተለቅ ያለ አጀንዳ ነው፡፡ "አይ እማ ምን እንዳረግበት ነው ይህን የሰጠችኝ"? አለች የሚያምሩ ጥርሶቿን እያፈገገች ስትገልጠውም ተፅፎበታል፡፡ ቶሎ ብላም ወደ መጀመሪያው ገፅ አመራች እና ማንበብ ጀመረች፡፡ <ውቡ ከተማና መንገዶቹ ለልጄ ወንጌል ይድረስልኝ> ይላል፡፡ ሁለተኛውን ገፅ ከፍታ ማንበቧን ቀጠለች፡-
ልጄ በመጀመሪያ ከስሜ ልጀምር ፅጌሬዳ በርይሁን እባላለሁ ወላጅ እናትሽ ነኝ ፡፡

ይላል ወንጌልም ባነበበችው ነገር ግራ ተጋባችና የማዬ ስም መሰረት አደል እንዴ? የምን ፅጌሬዳ ነው? አለችና ንባቧን ቀጠለች ፡-
ውዷ ልጄ ይሄን ፁፍ እንድታነቢው 13 አመትሽን በጉጉት ነበር የጠበኩት፡፡ እናም ቀጣዩን ገፅ ከመክፈትሽ በፊት ለሚከተሉት መመሪያዎች ቃል ጊቢ- 1 የየቀኑን ንባብ በየቀኑ አንብቢ
2 የፅሁፉን ሀሳብ ተግባራዊ አርጊ
3 ጠንካራና ለተፈጠርሽለት አላማ ተገኚ ሁኚ ልጄ ለነዚ ትዛዞች ቃል ማትገቢ ከሆነ ቀጣዩን ገፅ እንዳከፍቺው፡፡አደራ እናትሽ ፅጌሬዳ ፡፡
ይላል ወንጌል ግራ ተጋባችና አጀንዳውን ዘግታ በፍጥነት ወደ መሠረት ክፍል አመራች ፡፡

መሠረት ክፍሏ የለችም ሁሉም ክፍሎች ፈልጋ አጣቻትና ወደሳሎን ሮጠች፡፡ ሳሎንም የለችም፡፡ የግርግዳ ሰአቱን ቀና ብላ ስትመለከት 3:40 ይላል፡፡ "የት ሄዳ ነው በዚ ምሽት?" አለች ጥልቅ በሆነ ግራ መጋባት "የዛሬው ሰርፕራይዝ ደሞ አያልቅም እንዴ? ብላ ወደ በሩ ስትጠጋ በሩ ክፍት ነው፡፡ ስትወጣም ጥቁሩ ረጅሙ ሰውዬ ፊት ለፊቷ ቆሟል.......

ይቀጥላል!

@agapetruelove
@agapetruelove