Get Mystery Box with random crypto!

. ▷ ወንጌል ◁ . ተከታታይ ልብ-ወለድ Written by | Agape-True Love

. ▷ ወንጌል ◁
. ተከታታይ ልብ-ወለድ

Written by Bethlehem Dejene

. #ክፍል_2
- - - - - - - - - - - - - - - -- - - - - -
➟መሰረት ድንጋጤ በተሞላ ንግግር " ወንጌሌ ምንም እንዳደብቂኝ አድርጌ አደል ያሳደኩሽ እስኪ የሆነውን ሁሉ ሳደብቂ ንገሪኝ" አለቻት በተማጽኖ ወንጌልም " እማ እኔ ቅድም ከነገርኩሽ ውጭ ምንም ምነግርሽ ነገር የለም" አለች "መሠረትም በይ ተነሺና ኮት ደርቢ ሆስፒታል እንሄዳለን" ብላ ብድግ አለች ወንጌልም ብድግ ብላ "እማ ግን ምንም አለመሆኔን ብዙ ሊያረጋግጡ የሚችሉ ነገሮች አሉ 1ኛ እግ/ር ከኔጋ ነበር ለዛም ይመስለኛል ከድንጋጤ ውጪ ሚሰማኝ ምንም አይነት ስሜት የሌለው ከተጠራጠርሽ ግን ሆስፒታል ለመሄድ ዝግጁ ነኝ ምክንያቱም ለኔ ያለሽ እምነት እንዲጓደል አልፈልግም " አለቻት መሠረትም "

አመሰግናለሁ ልጄ እግ/ር ካንቺጋ በመሆኑ ውስጥ ክፉ ባንቺ ህይወት እንደማያሸንፍ ስለተረዳሽ ግን ማረጋገጡ
አይጎዳም "አለቻት ወንጌልም "እማ የእምነታችን ማረጋገጫ እራሱ እግ/ር ነው አይተንና ዳሰን ያረጋገጥነውን ነገር እንዴት እምነት ብለን ልንጠራው እንችላለን? አለቻት መሠረትም ፈገግ ብላ "እሺ የኔ ውድ ልጅ ተስማምቻለሁ አሁን ልጆቹ አይምሽባቸው ነጬን ቀሚስሽን ልበሺና ልደትሽን እናክብር " አለቻት

ወንጌልም በትዛዝዋ መሠረት ረጅም ነጭ ቀሚሷን አርጋ ያንን ውብ ፀጉሯን ለቃ በአንፀባራቂ አይኖቿና ውበትን በተሞላው ፊቷ ታጅባ ከመሠረትጋ ወደሳሎን አመሩ ሁሉም ቆመው ሀፒ በርዝ ዴ እያሉ ተቀበሏት ሄዳም በተዘጋጀላት ቦታ ተቀመጠች መሠረትም ፊት ለፊቷ ቆማ ንግግር ማረግ ጀመረች "ዛሬ የወንጌል 13ተኛ አመት የልደት በአሏ ነው። የልደቷም ሴርሞኒ ብሎም እሷና እናንተ በነጭ ልብስ እንድትዋቡ ያረኩት ያለ ምክንያት አደለም ነጭ የንፁ ነገር ምሳሌ ነው፡፡

አሁን ያላችሁበት እድሜ ደሞ የወጣትነታቹ ጅማሬና አዳዲስ የተፈጥሮ ክስተቶች ወደናንተ ሚመጡበት እድሜ ነው ለምሳሌ ከዚ እድሜ ጀምሮ የፍቅር ስሜት ብሎም ፣አዳዲስ ተፈጥሮዎች.. ወደናንተ ይመጣሉ እና ወሳኙ ነገር እኝን ስሜቶች ለምን መጣቹ ማለት ሳይሆን እንዴት በስርአት ልምራቸው የሚለው ነው፡፡

እናም በዚ እድሜያቹ ነጭ ከሆናቹ ነገ ብቆሽሹ እንኳን ብዙ አመነችኩም ምክንያቱም የታነጻችሁበት መሠረት ወሳኝ ስለሆነ።ስለዚ "ብላ ንግግሯን ሳጨርስ የኮቴ ድምጽ ከውጭ ይሰማ ጀመር...........

ይቀጥላል......
SHARE SHARE SHARE SHARE
@agapetruelove
@agapetruelove