Get Mystery Box with random crypto!

. ▷ ወንጌል ◁ . ተከታታይ ልብ-ወለድ Present by #agap | Agape-True Love

. ▷ ወንጌል ◁
. ተከታታይ ልብ-ወለድ

Present by #agapetruelove

Written by Bethlehem Dejene

. #ክፍል_1
- - - - - - - - - - - - - - - -- - - - - -
➟ቀኑ እሮብ ነበር ገና ከለሊቱ 11:30 የክፍሏ በር ተንኳኳ፡፡ ወንጌል ከ12 ሰአት በፊት የመነሳት ልምድ ስለሌላት የበሯ መንኳኳት አስደንግጧት በርግጋ ተነሳችና"ማነው"? አለች "ወንጌልዬ እኔ ነኝ" አለቻት ተነስታም በሩን ስትከፍት መሰረት ነጫጭ አበባዎች ታቅፋ ከበራፏ ቆማለች "እንዴ እማ ምንድነው የያሽው"? አለቻት በግርምት፡፡"ልጄ ላንቺ ዛሬ ትልቅ ቀን ነው መልካም ልደት ጣፋጯ ወንጌል"!ብላ ግንባሯን ስማ አበባውን ሰጠቻት፡፡ ወንጌልም በፈገግታ "አመሰግናለሁ እማ ዛሬ ለካ ልደቴ ነው ረስቼው ነበር" ብላ አበባውን ካስቀመጠች በሁዋላ ወደ መታጠቢያ ቤት አመራች::

12 አመታትን ልጅ የሚያስፈልገውን ሁሉ አጊንቶ እንዲያድግ አርጋ ስላሳደገቻት ያለ እድሜዋ እንደ ትልቅ ከመሆኗም ባሻገር የየቀን ህይወቷም በእቅድ የተሞላ ነበር፡፡ እናም ወንጌል ከመታጠቢያ ቤት ወታ የጠዋት ክንውኗን ከጨረሰች በሁዋላ ወደ ት/ቤት አመራች፡፡ ከትምርት ቤትም ስትመለስ የጊቢውም የቤቱም በር ክፍት ነው መሠረት ግን ያለ ወትሮዋ አልነበረችም። እማ የት ሄዳ ነው በሚል ሀሳብ ትንሽ ከተብሰለሰለች ወዲ ሮብ 11 ሰአት የቸርች ፕሮግራም ስላላት ወደዛው አመራች፡፡

ስትመለስ አምሽታ ነበር ጊቢውስጥም ያለወትሮው መብራት አልበራም ወደ ቤትም ስትጠጋ ጨልሞ በሩ ተዘግቷል ብዙ አንኳኳች መልስ የለም ከትንሽ ቆይታም በሁዋላ የጊቢውን በር ከፍታ ስትወጣ ከሁዋላዋ ትከሻዋ ሲያዝ ተሰማት ዞር ስትል አይታ የማታቀው ጥቁር ጺሙን ያንጀረገገ ረጅም ሰውዬ አፈናትና እጁ ላይ ወደቀች።

በዚያው ቅስፈት ነበር የጊቢው መብራት የበራው መሰረት ነጩን ክሬም ኬክ በሳህን ይዛ በሩን ከፍታ ስትወጣ ማንም የለም፡፡ ወደቤትም ተመልሳ "ልጆች ወንጌልን ሰርፕራይዝ እንደምናደርጋት ገብቷታል እንዴ?"አለች ሁሉም "ኧረ" አሉ አንገታቸውን እየነቀነቁ፡፡ ቤቱ በጣም አምሯል! ነጭ ምንጣፍ፣ ክሪስማሱ ላይ ያለው ነጭ የሚያበራው ዲምላይት፣ ነጬ ኬክ ላይ የተቀመጡት እንጆሪዎች፣ በነጭ ሽፍን የተጠቀለሉት ቸኮሌቶች....ብቻ የልደት ሴርሞኒው እንከን አቷል!

መሠረት በድጋሚ ተመልሳ ወጣች አሁንም ጊቢ ውስጥ ማንም የለም መጣራት ጀመረች መልስ የለም እናም ለልደቷ የተሰበሰቡት የወንጌል ጓደኞች ከመሰረትጋ አብረው ይፈልጓት ጀመር ዮዶት አሰብ አርጎ"ምን አልባት ሰው ስታጣ ተመልሳ ይሆን?" አለና ወደ ጊቢው በር አመራ በሩንም ሲከፍተው ወንጌል ዝርግት ብላ ወድቃ ተመለከተ ወዲያው የድንጋጤ ጩኸት ጮኸ፡፡ ሁሉም ተሰበሰቡና ወደቤት አስገቧት፡፡ መሠረትም አረጋግታቸው ፀለዩላትና ብዙም ሳይቆይ ነቃች፡፡

ገና አይኗን ከመግለጧ "ሰርፕራይዝ" አለች ሊና " ሰርፕራይዝ ነበር እንዴ? ይሄ ሁሉ" አለ ዮዶት ሊና ላይ አፍጦ " አረ ጌታን እኔ ማንም ሳይቀድመኝ ልበላት ብዬ እንጂ ከናንተ የተደበቀ ሰርፕራይዝ የለኝም" አለች ሁሉንም በዙር እያየች፡፡ ወንጌልም እራሷን አረጋግታ ስትመለከታቸው ሁሉም በነጭ ልብስ አጊጠዋል ቤቱም በልደት ሴርሞኒ አሸብርቋል፡፡"ሰርፕራይዝ ነበር እንዴ "? አለች በንዴት " ምኑ አሏት ሁሉም አፈናው ነዋ አለቻቸው "አፈና አለች መሠረት እቅፍ አድርጋት ወንጌልም "እራሴን ከመሳቴ በፊት የሆነ ደስ ማይል ሰውዬ አፍኖ እንደጣለኝ ትዝ ይለኛል ግን ምንም ሳያረገኝ ይሆን የሄደው?" አለቻቸው መሠረትም በጣም ተደናግጣ እጇን ይዛ መኝታ ክፍሏ አስገባቻት...

#ይቀጥላል....


@agapetruelove
@agapetruelove