Get Mystery Box with random crypto!

በሀገረ እግዚአብሔር / በቅድስት ምድር / በእመቤታችን ርስተ ምድር በሆነችው በኢትዮጵያ የሰው ልጅ | 💠 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው።

በሀገረ እግዚአብሔር / በቅድስት ምድር /
በእመቤታችን ርስተ ምድር በሆነችው በኢትዮጵያ የሰው ልጅ ደም እየፈሰሰ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ሹሙ እንደ ጠፋበት ንብ ህዝቡ ከተበታተነ ሰነበተ። የሰው ሕይወት የውሻ ሕይወት ያክል ተቆጥሮባታል ፡፡
አምላክ ከ 22ቱ ፍጥረታት ለይቶ አምላካዊ ክብሩን
የሰጠው የሰው ፍጡር እየሞተም እየገደለም ነው ፡፡ ሰው ሠውን እያደነ ነው ፡፡
ከሰው ሕይወት ይልቅ ስንዝር መሬት ትልቅ ከበሬታ አግንታለች። ሁሉም ነገ ጥሎት ለሚሄድ መሬት እየተስገበገበ ነው። በዚች ሀገር የጥይት
ባሩድ እየሸተተ ነው ፡፡ ህዝቡ ደስታውን ሳያጣጥም ጥቁር ደመና እየመጣበት ነው ፡፡ በዚች ሀገር ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው አስታራቂ ሽማግሌ ይፈለጋል፡፡
ቅዱሳን የመነኑበት ምድር በእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እስራኤላውያን ቤተ መቅደስ እንዳትሆን እንፈራለን፣የሙሴ ጽላት ያለባት ምድር የሶረያን እጣ እንዳታገኝ እንፈራለን። ምንግዜም ሰው ሲያጠፋ ሀገር ባድማ ትሆናለች፡፡
በፈረሱ የተማመነ ይጠፋል ይላል ነብዩ ዳዊት።
የፈርዖን ታሪክ እንዳይደገም እንፈራለን ፡፡ የሰው ደም ከባድ ነው። ትልቅ መከራ ያስከፍላል ፡፡ ሳጥናኤል ክፉ
ነው። ከላይ ከትዕቢት ተራራ ላይ ሰቅሎ ወደ ውርደት ሸለቆ ይፈጠፍጣል፡፡
ምን ይሁን ኢትዮጲያውያን እርስ
በርስ አዳኝና ታዳኝ ሆነው በደማቸው ይራጫሉ ፡፡
አንደበቱ ቅባ ቅዱስ የተቀባ መሪ እቺ ሃገር ትፈልጋለች።


ለበለጠ join and join

@ETIOPIA_Hagerie


@Afe_Werk