Get Mystery Box with random crypto!

። የነብዩ ”ﷺ” አመጋገብ 1~ነብዪ ሰ ዐ ወ መብላት ከመጀመራቸው በፊት እጃቸውን ይታጠቡ ነበር | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

። የነብዩ ”ﷺ” አመጋገብ

1~ነብዪ ሰ ዐ ወ መብላት ከመጀመራቸው በፊት እጃቸውን ይታጠቡ ነበር የሚበሉትም በቀኝ እጃቸው ሲሆን ከፊታቸው ካለው ምግብ ነበር የሚበሉት ፡፡
2>" ነብዩ ሰ ዐ ወ ተደግፈው በልተው አያውቁም ፣
ምግብ ሲበሉ የተለያየ አቀማመጥ ነበራቸው
ሀ/ልክ ተሽሁድ ላይ እንደሚቀመጡ አይነት አቀማመጥ ነበር
ለ/ልክ እንደዚሁ ይቀመጡና የአንድ እግራቸው ጉልበት ደረታቸው ጋር ይደርስ ነበር
ሐ/የውስጥ እግራቸው መሬት ላይ ተለጥፎ ቁጢጥ ይሉ ነበር
3> ነብያችን ሰ ዐ ወ በጠረቤዛም ተደግፈውም ሆነ ወንበር ላይ ተቀምጠው በልተው አያውቁም(ቆዳ ወይም ጨርቅ )መሬት ላይ አንጥፈው ይመገቡ ነበር
4> አብዛኛው ጊዜ ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው (አውራ ጣት ጠቋሚ ጣት እና የመሃል ጣታቸው) በመጠቀም ነው ፡፡ ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ግን የቀለበት ጣታቸውን ጨምረው ይመገቡ ነበር ፡፡
5~ ተመግበው ሲጨርሱ ጣቶቻቸውን አፋቸው ውስጥ ከተው ያፀድዋቸው ነበር ከመሃል ጣታቸው ጀምረው አውራ ጣታቸው ላይ ያቆማሉ ፡፡
6~በገበታው ላይ ያለው ምግብ ከመሃል ጀምሮ የተደረደረ ከሆነ ከፊታቸውና ከስር ካለው ይጀምሩ ነበር
የምግብ በረካ ወደ መሃል እየቀነሰ ይሄዳል ብለዋል ፡፡
7~የነብዩ ሰ,ዐ,ወ በብዙ ሳህን የሚቀርብ የተለያየ አይነት ምግብ አይወዱም ነበር ፡፡
8~የነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሃላዋ (ጣፋጭ)ማር፣ቆምጣጤ፣ተም
ር፣ሀብሀብ፣ኪያር እና
ዝኩኒ ይወዱ ነበር፡፡
9~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የሽንጥ ፣የአንገት አና የትከሻ ስጋ ይወዱ ነበር ፡፡
10~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ከንዳንድ ጊዜሁለት ምግቦችን ይመገቡ፡ነበር ሀባብ እና ተምር ኪያር እና ተምር ..
11~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገቡን ይተውት ነበር፡፡
12~ነብዪ ሰ,ዐ,ወ ያልበሰለ ነጭም ቀይም ሽንኩርት ተመግበው አያውቁም ፡፡
13~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የተነፋ ዱቄት አይበሉም ነበር (ግን
አልከለከሉም )
14~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ተምር ወይም ዳቦ፡ንፁህ ቦታ ላይ ከወደቀ ጠርገው ይበሉ ነበር ፡፡
15~በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም መጀመሪያ ያቀዘቅዙት ነበር አላህ እሳት፡አይመግበንም ይሉ ነበር፡፡
በጣም የሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል ፡፡
, , ,
16~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግብ አሽትተው አያውቁም ጥሩ ያልሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል ፡፡
17~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ሲበሉም ሆነ ሲጠጡ ተቀምጠው ነው ፍራፍሬዎችን ቆመውም እየተራመዱ በልተው ነበር፡፡
18~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ አንዳንዴ የበሰለ ስጋን በቢላዋ ቆርጠው ይበሉ ነበር፡፡
, , ,
19~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግብ የያዘን እቃም ሆነ መጠጥ የያዘ መጠጫን ይከድኑ ነበር ፡፡ የሚከድኑት ነገር ካጡ ከላዩ ላይ ስንጥር ያስቀምጡ ነበር፡፡
20~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ማታ የተሰራን ምግብ እስከ ጠዋት ጠዋት፡የተሰራን ምግብ እስከ ማታ፡አያቆዩም ነበር፡፡
(ለሚቀጥለው ምግባቸው በአላህ ይተማመኑ ነበር፡፡)
21~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ስጋ ወደ ቤት ሲያመጡ ለጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያዙ ነበር ፡፡
22~ ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ምግብም ላይ መጠጥ ላይ ተንፍሰው (እፍ) ብለው አያውቁም፡፡ ምግብ ላይ መተንፈስ መጥፎ ልማድ አድርገው ይቆጥሩት ነበር፡፡
23~ነብዩ ሰ,ዐ,ወ የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር ፡፡
* ሼር ይቀጥላል
https://t.me/Adnan567mh