Get Mystery Box with random crypto!

ምንኛ ልብ የሚነካ ሀዲስ ነው !!! ---------------------------------- | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

ምንኛ ልብ የሚነካ ሀዲስ ነው !!!

------------------------------------------------------
-------------------------------------------------------

አቡዘር አል-ገፋሪ በዘገበው ሓዲስ ነብዩ (ﷺ) ከጌታቸው ሲዘግቡ እንዲህ አሉ፡-

አላህ እንዲህ አለ “ እናንተ ባሮቼ ሆይ! እኔ በደል መፈጸምን በራሴ ላይ እርም አድሪጌዋለሁ። በናንተ መካከልም በደልን መፈጸም እርም አድርጌዋለሁ። ስለዚህ አትበዳደሉ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመራሁት ሲቀር ሁላችሁም ጠማሞች ናችሁ። ስለዚህ ቀጥተኛ መንገድ እንድመራችሁ ለምኑኝ እመራችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመገብኩት ሲቀር ሁላችሁም ረሃብተኞች ናችሁ። እንድመግባቹህ ጠይቁኝ እመግባችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ ያለበስኩት ሲቀር ሁላችሁም እርቃናችሁ ናችሁ። እንዳለብሳቹህ ጠይቁኝ አለብሳችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ ቀንና ለሊት ትሳሳታላችሁ እኔ ደግሞ ወንጀሎችን ሁሉ እምራለሁ። ስለዚህ መሃርታን ጠይቁኝ እምራችኋለሁ።

---------------------------------------------------

-------------------------------------------------------

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተኮ እኔን የመጉዳት ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጉዳት አትችሉም ደግሞም እኔን የመጥቀም ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጥቀም አትችሉም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ጌታን ፈራሂ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይጨምርም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያቹህ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ወንጀለኛ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይቀንስም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ አንድ ሜዳ ላይ ቆመው ቢጠይቁኝና ሁሉንም የጠየቁኝን ብሰጣቸው፥ ይህ ስልጣኔ ላይ ልክ መርፌ ባህር ላይ ገብቶ ከባህሩ እንደሚያጎድለው ቢሆን እንጂ ምንም አያጎድልም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!ስራችሁን ነው የምቆጥርላችሁ ከዛም በስራችሁ መሰረት እከፍላችኋለሁ። መልካምን ያገኘ አላህን ያመስግን ከዚህ ውጭ ሌላን ነገር ያገኘ ግን ራሱን እንጂ ሌላን አይውቀስ።”

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።


=========
=====================

አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን !!!!!!
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN

@Adnan567mh