Get Mystery Box with random crypto!

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

የሰርጥ አድራሻ: @addismaleda
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.49K
የሰርጥ መግለጫ

ዜና ከምንጩ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-05-09 11:10:33 #ማስታወቂያ

ታላቅ ቅናሽ

በ80,400 ብር በካሬ
በ10% ቅድመ ክፍያ፣

በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት

ባለ 1 መኝታ
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ

ይደዉሉልን 0974388888
10.0K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-09 11:10:02
8.8K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 19:40:01 የአዲስ ማለዳ ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዕለታዊ ዜናዎች

• "የህወሓት ወታደሮች" በሱዳን ውጊያ
• የመንግስት ሰራተኞች ይደራጁ!

በዩትዩብ ቻናላችን ተመልከቱ፦


9.6K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 15:39:52 “የህወሓት ወታደሮች” በሱዳን ግጭት ውስጥ ተቀጥረው እየተዋጉ ነው መባሉን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ

ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኮማንደር መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ታጣቂዎች ለጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በማገዝ እየተዋጉ ነው ቢልም ህወሓት ሀሰተኛ ትችት ነው ብሏል።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ካወጣው መግለጫ አዲስ ማለዳ እንደተመለክተችው የጀነራል አል ቡርሃን የሱዳን ታጣቂ ኃይል የውጭ ቅጥረኞችን ይቀጥራል የተባለ ሲሆን “ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ ጭካኔ ፈጽሟል” የተባለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ኃይሎች አሁን ከአል ቡርሃን እና አጋር ታጣቂዎቹ ወግነው እያጠቁን መሆኑን በማስረጃ አረጋግጠናል ብሏል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ትላንት ባሰራጩት መግለጫ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወቀሳ “መሰረት ቢስ” ነው ያለ ሲሆን፤ ታጣቂ ኃይሉ በእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት አቅዶ ያዘጋጀው ትርክት ነው መባሉን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር መግለጫ እንደጠቀሰው ህወሓት “አንድ የፖለቲካ ድርጅት እንጂ የትጥቅ አደረጃጀት በፍጹም የሌለው እና የሚያዛቸው ታጣቂዎችም የሌሉት ስብስብ” ነው። የትግራይ ሕዝብ ከሱዳን ሕዝብ ጋር ያለው የጠበቀ ወዳጅነትም ይህን እንድናደርግ አይገፋንም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ መግለጹን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
9.0K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 15:39:48
7.1K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 14:39:01 ኢትዮጵያ በሚዲያ ነጻነት ከ180 አገራት 141ኛ ደረጃን ይዛለች
ካለፈው ዓመት 11 ደረጃዎችን አሽቆልቁላለች


ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ የብዙኀን መገናኛ/ ፕሬስ ነጻነት ከተከበረባቸው አገራት 141ኛ ደረጃን ይዛለች።

ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች (reporters without borders) ዓለም አቀፍ ተቋም ባወጣው የ2024 ይርፕሬስ ነጻነት ሪፖርት ባለፈው ዓመት 130ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ፤ በዚህ ዓመት 141ኛ ደረጃን ከ180 አገራት ይዛ መገኘቷን አዲስ ማለዳ ከሪፖርቱ ተመልክቷል።

ከስድስት ዓመታት በፊት የታየው የሚዲያ ነጻነት አውድ የማንነት ግጭቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ሳቢያ ተቀልብሶ አሳሳቢ ሁኔታ መፈጠሩን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ተቋም አስታውቋል።

በወቅታዊነት ደግሞ በአማራ ክልል የቀጠለው በትጥቅ የታገዘ ግጭት የጋዜጠኞችን ስራ ጫና ውስጥ እያስገባ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ከሪፖርቱ ተገንዝባለች።

ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 15 ጋዜጠኞች እስካሁን መታሰራቸውንም ተቋሙ ገልጿል። በዓመታዊ ሪፖርቱ ኤርትራ በፕሬስ ነጻነት የመጨረሻውን ደረጃ ስትይዝ ኖርዌይ የጋዜጠኞች ነጻነት የተከበረባት አገር ሆናለች።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
8.3K viewsedited  11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 14:35:03
6.2K views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 13:59:51 የመንግስት ሰራተኞች እንዳይደራጁ መከልከሉ ከደመወዝና ግብር ጋር የተያያዙ እንግልቶች እየገጠሟቸው ነው ተባለ
ኢሰማኮ ከአቅሜ በላይ ነው ብሏል

ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ የመንግስት ሰራተኞች እንዳይደራጁ በአዋጅ መከልከሏ ሰራተኞችን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን እንዳስታወቀው የመንግስት ሰራተኞች እንዳይደራጁ የሚከለክለው የኢትዮጵያ የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ እንዲሻሻል በተደጋጋሚ ለመንግስት ጥሪ ቢያቀርብም ምላሽ ባለማግኘቱ ጉዳዩ ከተቋሙ አቅም በላይ ሆኗል።

ይህ ክልከላ የመንግስት ሰራተኞች ለወራት ደመወዝ ባለማግኘት እና ከከፍተኛ ግብር እንዲሁም መሰል ችግሮች እየተንገላቱ ተደራጅተው መብታቸውን እንዳያስከብሩ አድርጓል መባሉን አዲስ ማለዳ ከኮንፌዴሬሽኑ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ሕጉን እንዲያሻሽል በአሁኑ ሰዓት በዓለም ስራ ድርጅት በኩል ጥሪ እየቀረበ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ሰምታለች። ኮንፌዴሬሽኑም ይህ ሕግ እስከሚሻሻል ድረስ ጥያቄያችንን እናቀርባለን ሲል አስታውቋል።

አዲስ ማለዳ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች አንዳንድ ዞኖች ላይ የመንግስት ሰራተኞች በደመወዝ መቆራረጥ እና ሙሉ ለሙሉ መቋረጥ መቸገራቸውን መዘገቧ አይዘነጋም። በዚህ ሳቢይ የተዘጉ ትምህትርት ቤት መኖራቸውም ተሰምቷል።

ኢትዮጵያ የአገሪቱ እንደ አውሮፓዉያን አቆጣጠር በ1963 የፈረመችው የዓለም ስራ ድርጅት ስምምነት የመንግስት ሰራተኞች መደራጀትን ቢደነግግም የኢትዮጵያ አሰሪ እና ሰራተኛ ሕግ ይህንን ይከለክላል።

አዲስ ማለዳ ከኮንፌዴሬሽኑ ባገኘችው መረጃ የአገሪቱ ሕግ አካል ሆኖ ተፈጻሚ መሆን የሚገባው ጉዳይ ከመሆኑ ባለፈ ሰራተኞችን ለችግር እያጋለጠ ነው።
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
7.5K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 13:59:47
6.2K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-07 10:42:18
ያለመከሰስ መብት በሽግግር ፍትህ ሂደቱ ላይ አይሰራም
(የፖሊሲው ዋና ይዘቶች)


ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የሽግግር ፍትህ በመላው አገሪቱ ተፈጻሚ ይደረጋል። የጸደቀውን ፖሊስ የፍትሕ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገ ሲሆን አዲስ ማለዳ ተመልክታዋለች።

በኢትዮጵያ ዘመን የዋጁ በደሎች ፍትህ እንዲያገኙ፣ ቁርሾዎች እንዲቀንሱ እና የቀጠሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማቆም... https://addismaleda.com/archives/37962
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!

Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141
7.2K viewsedited  07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ