Get Mystery Box with random crypto!

Abisiniya Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniyans — Abisiniya Media A
የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniyans — Abisiniya Media
የሰርጥ አድራሻ: @abisiniyans
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 353
የሰርጥ መግለጫ

@abisiniyans
እንኳን ወደ አቢሲኒያውያን ቤት በደህና መጡ!
በዚ ቻናላችን *የዓለምአቀፍ ዜናዎች
*ጤና-ነክ ጉዳዮች
*ኪነ-ጥበባዊ ስራዎች
*ስፖርታዊ መረጃዎችን ያገኙበታል
ሃሳብ አስተያየቶቻችሁን በ @AbisiniyaMediaBot ላይ አድርሱን!
ፈጣሪ ህዝቦቿን ይጠብቅ!

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-26 18:04:16 አዲሱን Money heist :korea JEA ስመለከት ወደ አዕምሮዬ የመጣው ነገር ቢኖር' ሰሜን ኮርያ እና ደቡብ ኮርያ ዛሬ ላይ አንድ ላይ ቢሆኑ ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር' የሚለው ነው

ፖለቲካ ጫፍ እና ጫፍ ተወጥሮ አንድ የነበረችው ሀገር ለሁለት ተከፈለች።ምናልባትም ከ 60 አመት በላይ የትውልድ ክፍተት ተፈጥሮዋል።አንደኛው ስለ አንደኛው ምን ተነግሮት እንደሚያድግ አይታወቅም።እድል ካለው ጥሩ ነገር ይሰማል ከሌለው ደግሞ ምንም ጥሩ ነገር አይሰማም።ደቡቦቹ አለ በተባላ የአሜሪካ ኢምፐርያሊዝም ቅኝት በደንብ የሾሩ ፣ኢኮኖሚያቸው በደንብ የሳለ ነው።ሰሜኖቹ ግትር በሆነ የኒውክለር አቋማቸው ዛሬም አሉ።ግልፅነት በጎደለው እይታ አሜሪካንን ወይም ምዕራባዊንን በጠላት ይፈርጃሉ።አሜሪካን ጠል ከሆኑ ሀገራት ጋር የጋራ አላማማ ግብ የላቸው።ሚሳኤል ይሞክራሉ ፣ ያስወነጭፋሉ።'አምባገነን' በሚባል መሪ ይመራሉ ።

እዚህ ፊልም ላይ ልዩነቶቻቸውንም ለማሳየት ይሞክራሉ።ከታሪኩ መዋቅር ጋር እርስ በእርስ የመፈታተሽ ስሜቱን በጉልህ አስቀምቶዋል። በአንፃሩም ደግሞ ታሪኩ ሲጀምር ሁለቱን ሀገራት ያዋሀደ እይታን ያሳያል።የራሳቸው የሆነ የጋራ የሆነ የመገበያያ ገንዘብ እስከማዘጋጀት ድረስ ...ሁለቱ ሀገራት ውህደት ቢጀምሩ የአለም የፖለቲካ ከባድ ሚዛን ወደ ምስራቁ አለም ዘንበል ብሎ የጎደለውን ኪሎ ይሞላል ብዬ አሰብኩ።ለምን አሰብክ አይባልም .....እንደ ሀሳብ ነው።

ሀሳባችሁን እፍታ 𝙧𝙚𝙘𝙖𝙥 የመወያያ መድረክ ላይ አካፍሉኝ

𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆

@abisiniyans @efetarecap1
109 viewsEliyas, edited  15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 11:59:11
ለፈገግታ ያህል

በአንድ የጫማ መሸጫ መደብር ዉስጥ የተቀጠረ አሻሻጭ ለአለቃዉ በጉራ <<ለአንድ ታዳጊ ህፃን አንድ ቡኒ ጥንድ ጫማ በስድስት ዶላር ሸጥኩላት ሴትዮዋ የነበራትን አንድ ዶላር ከሀምሣ ሣንቲም ስለነበር እሱን ቀብድ ተቀብዬ ሸኘኋት >> አለዉ።
<< ዳግመኛ እንደዚህ አታድርግ ሴትዮዋ ተመልሣ አትመጣም >> ሲል አለቅየዉ በንዴት ተናገረ ።
<< የለም ትመጣለች ። ሁለት የግራ እግር ጫማ ነዉ የሰጠኋት >> አለ አሻሻጩ ።

እየሳቃችሁ ዋሉ !!

Like & share
Subscribe

@abisiniyans
99 viewsBiniyam, edited  08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 16:21:18
# የፊልም ጥቆማ

ሳንኮፋ

የፊልሙ ዘዉግ ፦ ሰስፔንስ ድራማ

የፊልሙ እርዝመት ፦ 124 ደቂቃ

እአአ 1993 ለዕይታ የበቃዉ ሳንኮፋ ፊልም አፍሪካዊ ይዘት ያላቸዉን ፊልሞች በመስራት የሚታወቀዉ ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ዳይሬክት አድርጎታል
ሳንኮፋ የሚለዉ ቃል የወሰደዉ ከ ጋና ከአማካን ቋንቋ ሲሆን ቃሉም አንድ ሰዉ ወደፊት ለመራመድ ካለፈዉ ታሪክ በጣም ርቆ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ያጎላል ።

በፊልሙ ላይ ሳንኮፋ በወፍ እና በመለኮታዊ ከበሮ ዝማሬ ተመስሏል
ሞና የተባለችዉ ገፀ ባህሪ ጉዞ ተጠቅሞ አፍሪካዊ የማንነት ግንዛቤ ሥሩን ማወቅ እና " ወደ ምንጭ መመለስ " እንዴት እንደሚጨምር ያሳያል ።

በጥቁር የፊልም ባለሙያዎች የተሰሩ ፊልሞችን በማዘጋጀት እና በማከፍፈል የሚታወቀዉ አሬይ በኔትፊሊክስ በኩል ለተመልካቾች ለእይታ አቅርቦታል ።

የእረፍት ቀናችሁን እንድታዩት ጋበዝናችሁ !!

Like & share

Subscribe

@abisiniyans


አቢሲኒያ ፊልሞቻችን
102 viewsBiniyam, edited  13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 18:47:26 ልዩ ልዩ አቢሲኒያ

በአቢሲኒያ ሚዲያ የቴሌግራም እና የዩትዩብ ቻናል ላይ ብቻ!


አመስጋኝነት

በዚህ ሳምንት በልዩ አቢሲኒያ ዝግጅታችን ስለ አመስጋኝነት በስፋት እናነሳለን። አመስጋኝ መሆን በ ህይወታችን ስለሚኖረው አስተዋፅኦ
ስብሀት ገ/እግዛብሄር የተናገራቸውን ንግግሮች እንዲሁም ሰዓሊ ብሩክ የሺ ጥላ ስለ ማመስገን ያለውን በማካተት ስለምስጋና እናነሳለን ።
"At the end everything will gone be alright ,if not you are not at the end."
መልካም ቆይታ።

አዘጋጅና አቅራቢ፦ፀጋ ገብረ ሚካኤል

◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤
ABISINIYA MEDIA

LIKE &SUBSCRIBE
◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤

     ╚»★ቤተሰብ ይሁኑ★«╝
            𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑
       ︎ @abisiniyans ︎

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
     @AbisiniyaMediaBot ሀሳብ እና አስተያየታችሁን ብትሰዱልን ይደርሳል።     
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
96 viewsTesfsh, edited  15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 11:38:12
ብሄራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት 400 ደረጃዎችን አፀደቀ።

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት(ኢደኢ) ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት የተውጣጡ ብሄራዊ የደረጃ ዝግጅት ቴክኒካል ኮሚቴ ጋር በመሆን ያዘጋጃቸውን የኢትዮጵያ ደረጃዎች እንዲያፀድቅ ሥልጣን ለተሰጠው የብሄራዊ ደረጃዎች ምክር ቤት አቅርቦ ፣ ምክር ቤቱም ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 33ኛው የምክር ቤት ስብሰባ እና ሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባው በአምስት ዘርፎች ተዘጋጅተው የቀረቡለትን 400 ብሄራዊ ደረጃዎች አፅድቋል።

በዚህም መሰረት
•በኮንስትራክሽንና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፍ 6 አዲስ ፣ 1 የተከለሰ ፣ በድምሩ 7 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

•በአካባቢና ጤና ደህንነት ዘርፍ 28 አዲስ ፣ 9 የተከለሱ ፣ 23 በማስቀጠል በድምሩ 60 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

•በኤሌክትሮ ሜካኒካል የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 16 አዲስ ፣ 22 የተከለሰ ፣ 36 በማስቀጠል ፤ በድምሩ 74 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

•በግብርና ምግብ የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 11 አዲስ ፣ 61 የተከለሰ ፣ 73 በማስቀጠል በድምሩ 145 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

•በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች 8 አዲስ ፣ 32 የተከለሱ ፣ 74 በማስቀጠል ፣ በድምሩ 114 ደረጃዎች ፣...በጠቅላላው ከአምስቱ ዘርፎች ለካውንስሉ ቀርበው ከነዚህ መካከል 400 ደረጃዎች ብሄራዊ ደረጃዎች እንዲሆኑ ፀድቀዋል። ከነዚህ ውስጥ 69 አዲስ (New) ፣ 125 የተከለሱ (Revision) ፣ 206 በማስቀጠል (Reaffirmation) የፀደቁ ናቸው። ከህዝብ ጤናና ደህንነት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ የተገናኙ 9 ደረጃዎች አስገዳጅ ሆነው እንደጸደቁ አቢሲኒያ ሚዲያ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቶታል።

[ተስፋወርቅ ልዑልሰገድ]
89 viewsTesfsh, edited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 08:13:01
እፍታ recap

በ 2022 ከተጠናቀቁ ተከታታይ ፊልሞች መሃል አንዱ ነው።ከሚያነሳው ሀሳብ ጀምሮ ብዙዎች ወደውታል።ከታሪኩ ፍሰት እና ከገፀባህሪ አሳሳል አንፃር የተዋጣለት ነበር።ጠጋ ብለን ከፊልሙ ጀርባ ያሉ ታሪኮች እንቃኛለን

በ semu audio books ላይ በዚህ ሳምንት ስለ ታዋቂው Money heist ፊልም ጥቂት ነገር ብለናል።በዚህ ከታች ባስቀመጥነው ሊንክ የሞባይል መተግበሪያውን ያገኙታል።

Google Play Store:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.semu.app.prod&hl=en&gl=US

Apple Store: https://apps.apple.com/us/app/semu-audiobooks/id1509423149

ሀሳብ እና አስተያየት ካላችሁ @WhoisEliyaz ላይ ብትልኩልን ይደርሰናል።

የእፍታ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀላሉን @efetarecap1
87 viewsEliyas, edited  05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 23:05:36
#በቃ
#ቀይ_አሻራ
#የዜግነት_ክብር
#amharagenocide
89 viewsTesfsh, 20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ